የሚገርመው ዳግማዊት ሞገስ የብልጥግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ መህኗ ነው። በሰሞኑ ቃለመጠይቋ ቃል በቃል ከዚህ በታች የተቀመጠው ተናግራለች።
“በኢትዮጵያ ከተማሪዎች አብዮት ጀምሮ ሦስት ያልተመለሱ ጥያቄዎች ነበሩ። እነሱም የመሬት፣ የብሔር እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ናቸው። እስካሁን የመሬት እና የብሄጸሔር ጥያቄዎች ተመልሰዋል። ያልተመለሰው የዴሞክራሲ ጥያቄ ብቻ ነው። ብልጥግናም ግቡ ያልተመለሰውን የዴሞክራሲ ጤያቄ መመለስ ነው።” በማለት ነው ቀድፍረት የተናገረችው።
በ2012 ጅማ በተካሄደው የኦዴፓ ጉባኤ የኦዴፓ መግለጫ በተቃራኒው “በኢትዮጵያ የብሔር ጭቆና አልነበረም። የነበረው የመደብ ልዩነት ነው” ማለታቸው ይታወሳል።
የወያኔ ፈጣሪ አባት አቶ ስብሓት ነጋ በበኩላቸው አንድ ጊዜ “የብሔር ጭቅና አለ ያልነው ለማታገያ ፈልገነው ነው” ብለው ነበር።
ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ኦነግን ለማስደሰት ከኦነግም በላይ ሆና ቀርባለች። እንግዲህ ልበ በሉ፣ የዐማራ ሕዝብ ጥያቄ የሚፈታው በእነ ዳግማዊት ምገስ ነው¿¿
(ዘ-መቀጣዋ)