እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

January 29, 2025

ከቴዎድሮስ ሃይሌ

የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

ክቡር ጀነራል በአሁኑ ወቅት በፉኖ ትግል ውስጥ ያለውን የመለያየት ግንብ የሚንድ ለማንም የማይወግን የመፍትሄ ሰው በሚል ይጠበቁ ነበር:: በግንባር በመዋደቅ ላይ ላሉት ሁሉም ሃይሎች አሰባሳቢ መካሪና ዘካሪ የውጊይ መሃንዲስ እና የእስትራቴጂ ቀያሽ ሆነው ይመጣሉ በሚል በጉጉት የሚጥብቆት አያሌ ወገን ነበር:: በቅርቡ የሰጡት ቃለመጠይቅ ግን ታሪኮን የሚያጎድፍ ስብዕናዎን የሚያበላሽ ከእርሶ ፈጽሞ የማይጠበቅ ንግግር ሆኖ አግኝተናል::

በአሁኑ ዘመን እንደ ዜጋ የደረስንበት የሞራል ደረጃ ያሳስባል:: መጽሃፉ “ክብራቸው በነውራቸው…” እንዲል በዚህ ዘመን ስም ያለውን መዘርጠጥ ቀን የጎደለበት የመሰለንን ያለ አንዳች እውነትና ምክንያት ስም ማጠልሸት መግፉትና ማውገዝ የመታወቂያና የመከበሪያ መስፈርት ሆኗል:: የሶሻል ሚድያ መንጋ ያነገሰውን : ማወደስ : ግሪሳው የሚያወግዘውን መንቀፍ : ትልልቅ የሚባሉት ሰዎች ጭምር ተቀብለው የሚያቀነቅኑበት መሆኑ ያሳዝናል:: ጥፉት ያጠፉ ሊተኝ : ወንጀል የሰራ ሊወገዝ : የሰነፈ ካለ ማበረታታት ተገቢም አስፈላጊም ነው:: ጀማው በጎጥ ተቧድኖ : በቅጥረኞች ሴራ ተጠልፎ : በደም ነጋዴ ሚድያዎች ተሰብኮ የሚያራምደውን ውዳሴና እርግማን እንደ ወረደ ተቀብሎ ማስተጋባት ብዙ የሕይወት ልምድ ካለው ወታደርና ሽማግሌ የሚጠበቅ አይደለም::

ክቡር ጀነራል አደባባይ ወጥተው የሚያውቁትን ወታደራዊ እውቀት ማጋራቶ : በተረዱት ልክ ፖለቲካውንም መዳሰሶ ተገቢም አስፈላጊም ነው:: ነገር ግን የአንድን ታጋይ ስብዕና ባልተገባና በማይመጥን ቋንቋ መግለጽ ነውርም ወንጀልም ነው::

ጀነራል ተፈራ አርበኛ እስክንድርን የገለጹበት መንገድ የአያሌ ታጋዮችን መስዋዕትነት ያረከሰ አነጋገር ከእሳቸው አይጠበም :: “ድል ለዲሞክራሲ” በሚለው መፈክር ስር ለእውነት እና ለአርነት ሕይወታቸውን ያጡ : በእስርቤት ብዙ ስቃይና እንግልት የደረሰባቸው : አካላቸውን ያጡና ለአዕምሮ መታወክ የተዳረጉ በርካታ የሰላማዊ ትግል አርበኞች ዋጋ የሚታወስበት ብራንድ ነው:: ድል ለዲሞክራሲ የሚለው የትግል መፈክር ጀነራል ተፈራ ተዋግተው ለስልጣን ያበቁትን የሕወሃትን አፓርታይዳዊ አገዛዝ የናደ ታላቅ የትግል መሰባሰቢያ አጀንዳም ነበር::

ጀነራል የንባብና የመረዳት እጥረት ከሌለባቸው በስተቀር እሳቸውና ጏዶቻቸው ከእስርና ውርደት እንዲወጡም የድል ለዲሞክራሲ ሰላማዊ ትግል ታጋዮችን ሚና ባወቁና ቢረዱት ኖሮ ይህን አይነት የወረደ ገለጻ እንደማይጠቀሙ እገምታለሁ:: ጀነራል ተፈራ እስክንድርን በጨዋ ደንብ ተችተው ጉድለቱን ቢያሳዩን ለመረዳት ባልከበደን ነበር:: እሳቸው ግን የሶሻል ሚድያው ማዕበል ከሚያግተለትለው ግባሶ ላይ አንስተው አርበኛውን በተራ ቋንቋ ሊያጣጥሉ መሞከራቸው ያስተዛዝባል:: አስነዋሪ ገለጻቸውም ሊነገራቸው ይገባል::

አርበኛ እስክንድር እያካሄደ ባለው ትግል እና በድርጅቱ ዙሪያ ሊገመገም ሊተች ይገባል:: ነገር ግን ስብዕናና ክብሩ የትግል ታሪኩና ተጋድሎው ፈጽሞ ማጠልሸት አይቻልም:: እስክንድር ታሪኩና ተጋድሎው ክብሩና ማንነቱ በመስዋዕትነት የደመቀ በክፍለ ዘመኑ በታሪክ ፊት ከታወቁት የኢትዮጵያ አርበኞች ከእነ እራስ አበበ አረጋይ እና ከእነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ተርታ የሚቀመጥ ከባድ ሚዛን ያለው የክፍለዘመኑ ጽኑ ታጋይ ነው::

ከወቅታዊው የፖለቲካ ንትርክ ወጣ ብለን ብንመዝን በተለይ በዚህ ዘመን በእስክንድር ተጋድሎ ልክ ክብረወሰን ያለው የጽናት የቆራጥነትና የታጋይነት ከፍታ ላይ ማን ነው ያለው? በእስክንድር ጫማ ውስጥ ለመቆም የተጋድሎ ታሪክ ያለውስ ማን ነው? እንኳን የታገለለት ሕዝብ ቀርቶ በእስርና እንግልት ያሰቃዩት የጀነራል ተፈራ የቀድሞ አለቆች ጭምር የሚያከብሩትና የሚፈሩት ጀግና ነው:: ይህን የመሰለ ታሪክ ያለውን ጀግና ለማጣጣል ጀነራል ተፈራ ሞራል የላቸውም::

ግዜ ቦታና ሁኔታ ይለዋወጣል:: ትላንት በሃሰትና በትዕቢት ያበጡ ዛሬ ተንፍሰዋል:: ዛሬ ላይ የጎጥ ግሪሳ የሳይበር ሰራዊት ያሳበጣቸው የሕዝብን ትግል መነገጃ ያደረጉ ፖለቲከኞች ሁኔታ ሲለወጥ ሕዝብ ፊት ሊቆሙ አይችሉም:: በደመነፍስ የሚከተል መንጋና ግሪሳ አንድ ቦታ ላይ እንደ ጤዛ ይተናል:: እውነት የአላማ ጥራትና ሕዝባዊነት ብቻ ነው ከታሪክም ከሕሊናም የማያስጠይቀው:: ጀነራል ተፈራ ዛሬ በአያሌ የክፉት መንጋዎች በአገዛዙ ጭፍራዎችና በደም ነጋዴ ዩቱበሮች ከመቼውም ግዜ በላይ ነግሰዋል:: ታሪክ እራሱን ይደግማል እንዲል ጀነራል ተፈራ ጀነራል አሳምነው ጽጌን እብድ ብለው አሳልፈው የሰጡ ሰድበው ለተሳዳቢ የዳረጉ ጥቁር ታሪክ እንዳላቸው አይዘነጋም:: በይቅርታ ታልፈው መሆኑን ሊዘነጉትም አይገባም::

ሌላው በጣም የገረመኝ የጀነራል ተፌ ንግግር እስክንድር ትግሉ ደክሞታል ከዚህ ለመውጣት ነው የሚደራደረው ብለዋል:: እስክንድር ወዶና ፈቅዶ ከአሜሪካ ተመልሶ በርሃ የገባ አርበኛ ነው:: የተከበሩ ጀነራል እርሶ ከፍየል ጥበቃ ላይ በሕወሃት ሰራዊት ታፍሰው በአጋጣሚ ወታደር የሆኑበትን ታሪክ አይነት አይደለም:: እርሶ እኮ ዛሬ የአማራ ሕዝብ የገባበትን ገደል የቆፈሩ የጠላቶቹ መንገድ መሪና ለኢትዮጲያ አንድነት የተሰለፈውን ሰራዊት የጨፈጨፉ የግፍ አገዛዙ አዋላጅ ነበሩ:: እርሶም በኮታና የገዛ ወገኖን ለሕወሃት በማስገበር ለዋሉት ውለታ ጀነራልነት ተሹመው በሚደላቀቁበት ዘመን እስክንድር ነጋ በሰብዓዊ መብት ታጋይነቱ በእስር ይንገላታ ነበር::

እርሶ የአገዛዙ ጦር ኮማንደር በነበሩበት ዘመን አማራው በአርባጉጉ በወተር በአሰቦትና በተለያዩ የሃገሪቷ ክልሎች በግፍ ሲታረድ ሲፈናቀልና ሲሰቃይ ክቡርነቶ የአማራን ጠላቶች መንበር ጠባቂ ነበሩ:: በአማራው ሕዝብ ላይ መዋቅራዊ ጥቃት ሲፈጸም እርሶ ከገዳዮቹ ጋር ቆመው ውስኪ ሲራጩ ያን ግዜ እስክንድር ነጋ እዛው እርሶ አለቆች አጠገብ ሆኖ በድፍረት ” አማራ ታሪኩን ያድሳል” በሚል መሪ ቃል ስለ አማራ ይጮህ ነበር::

አዩ ክቡር ጀነራል ሸዌ ” ውሃን ድንጋይ ያናግረዋል ” እንዲል የአማራ ሕዝብ የፈጸሙበትን በደል ይቅር ብሎ አጀግኖና ተንከባክቦ ጉድለቱን እንዲሞሉለት ስብራቱን እንዲጠግኑለት መለያየቱን ፈተው አንድ እንዲያደርጉ እምነትና ጉጉት በእርሶ ላይ አሳድሮቦት ነበር:: እርሶ ግን የበረሃ አንበሳ የጦር ገበሬና የመሰብሰቢያ ማማ ይሆናሉ ተብሎ ሲጠበቅ የቲክቶክ ወሮበሎችን  ቋንቋ የደም ነጋዴዎችን አጀንዳ ይዘው ተከሰቱ:: በዚህም የበርካታ አማሮችን ልብ ሰበሩ:: በወንሞቻችን መካከል የገባውን ሽብልቅ የበለጠ አጠበቁት:: አውቀውም ሆነ ሳያውቁት ትግሉን አስር እርምጃ ወደሗላ በማድረግ የጠላትን ፍላጎት አስፈጸሙ:: አዩ ጀነራል በእጁ እሳት የታጠቀ በበርሃ ያለ ታጋይ ይቅርና በሰላም ቀጠና የሚደረግ ትግል ውስጥ ያሉ ተዋናዬች ቁጥሩ የበዛም ሆነ ያነሰ ተከታይ ያለውን ሃይል ማግለልና ማንጏጠጥ ውጤታማ አያደርግም:: እርሶ ግለሰባዊ ስብዕናውን እንኳ ከግምት ሳያስገቡ በነወረ መንገድ የገለጹት አርበኝ እስክንድር ነጋ በእራሱ ያለው ስም ክብደት ከአንድ እዝ የሚበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም:: ከእስክንድርም አልፎ አብረውት በሕዝባዊ ድርጅት ውስጥ ያሉትን ጀግና ታጋዮች እንደ ኮሎኔል ሙሃቤ እንደ ፕሮፌሰር አስራደ እንደ አርበኛ መከታው እና ሌሎች ጀግኖችን ጭምር ግምት ውስጥ ያላስገባ ውግዘትና ስድብ ማቅረቦን የተረዱት አይመስሉም::

የተከበሩ ጀነራል ከከፍታዎ ወርደዋል:: ታላቅ ስህተት ፈጽመዋል:: ድርጅት ለመመስረት የተደረገውን ጥረት በቅጡ ሳይፈትሹ አቋም ወስደዋል:: ተሳስተዋል አበላሽተዋል ያሏቸው የሕዝባዊ ድርጅቱን መሪዎች አናግረው ዋሽተው እንኳ ቢሆን ለማስታረቅ ሲገባዎ እራሶት አውጋዥ ሆነው ተገኝተዋል:: ይህ እንኳ ባይሳካሎት ከዚህም በላይ እርሶ በነበሮት ተደማጭነት በሕዝባዊ ግንባሩ ያልታቀፉትን አራት ሃይሎች አግባብተው ወደ አንድ ማምጣት ይጠበቅቦት ነበር:: ይህንንም አልተወጡም::

በዚህ ዘመን በዚህ ትውልድ ውዝግብ ውስጥ ዳኛ የሚሆን ለሽምግልና የሚታጭ ጨዋ መታጣቱ ያሳዝናል:: በሚድያና በስደት ያለው አንዳንድ ስብስብ የተለያየ አጀንዳ ስላለው ፍላጎቱን ከማስፈጸም በዘለለ የሕዝብ ስቃይና መከራ አይገደውም:: እንደ ጀነራል ተፈራ ያለ እዛው ሜዳ ውስጥ ያለ እለት በእለት የሚዘንበውን እሳት የሚያይ የሰቆቃውን ዋይታና እሪታ የሚሰማ የጦር ሜዳ ልምድ ያለው አንጋፉ ኮማንደር የሰከነ እና የሚያግባባ ሃሳብ ማጣቱ እንደ ሕዝብ ተረግመናል እንድል አድርጎኛል::

የሺ ዘመናት ቱባ የሽምግልና ባህል ካለበት ሕዝብ ውስጥ የወጣ እና እዛው አባቶቹ ቅዬ ላይ ያለ ሰው የሽማግልናን ወግና ስርዐቱን መዘንጋቱ እሴቱ እየወደመ እንደ ሕዝብ ያቆመው የሞራል መሰረት በመፈራረስ ላይ መሆኑን ቆም ብሎ ማየት ነበረበት:: በውጭ ሃገር ያለው በተለይ የተማረውና አንጋፉ የሚባለው ወገን ቅንነት ይቅርባይነትና በጎ አስተያየት በአብዛኛው የሌለው በቀለኛና ፍጹም አድመኛ መሆኑ አብረን ስንኖር እያየንው ነው:: ወጣቱ ዘመኑ ባመጣው ቴክኖሎጂ በመንጋ የሚነዳ እሴትና ባህሉን የማያውቅ ነውሩን በክብር የሚወስድ አልጫ ትውልድ ሆኗል:: በእርግጥ ቁጥሩ እጅግ በጣም ያነሰ ቢሆንም ማንነቱን ያወቀ የሕዝቡ መከራና ስቃይ የሚሰማው አስተዋይና ልበ ብርሃን አዲስ ትውልድ በሃገርም በውጭም ማየታችን ተስፉችን ተሟጦ እንዳይጠፉ ያደርገናል::

ወገኖቼ ተምሳሌት እያጣን ነው:: ዋርካውን ሁሉ ጥለን የሞራል ምድረ በዳ ላይ ልንወድቅ ነው:: ታጋዮች በዘመናቸው የሕይወት ዋጋ ከፍለው ያኖሩትን አሻራ አንፉቅ:: በጀግንነታቸው ያገኙትን ዋጋ አናራክስ:: ክቡር ጀነራል ሕሊና ካሎት የተናገሩትን ነውር በይቅርታ አስተካክሉት:: ለግዜው የሚያዩት የመንጋ ጭብጨባ ሕሊናዎትን ጋርዶት በትዕቢት ከቀጠሉ መጨረሻዎ እመኑኝ ውርደትን አንገት መድፉት ይሆናል:: ነብስ ይማር ይባላሉ::አዩ “በመስታወት ቤት ያለ ድንጋይ አይወረውርም” የሚባለው ተረክ ሳይረዱ ድንጋዩን ቀድመው በመወርወሮ አንድ የበታቾ አስር አለቃ በዚህ ልክ የሃሳብ ናዳ እንዲያወርድቦ አስገድደውታል::ወደ ቀልቦ እንዲመለሱ እመኛለሁ::

ከወታደራዊ ሰላምታ ጋር!!!

7 Comments

  1. ወንድም ቲዎድርስ፦
    እኔ እስክንድርን በሩቁ፣ ወላጆቹን የተሻለ አውቃለሁ። ስመ ጥሩ ቤተሰብ ነበረው። በ 1997 ምርጫም ብዙ ድንቅ ሥራ እንደሠራ ምስክር ነኝ። በባልደራስም ከፍተኛ ሥራ መሥራቱን እረዳለሁ። የዕሥር ቤት መስዋዕት መክፈሉንም አውቃለሁ። ግን፣ ፈታኝ የሆነ ከባድ ኃላፊነት ተሸክሞ፣ የጎንዮሽ ውይይትና ድርድር ለምን ? ኢትዮጵያውያን፣ ቲዎድሮስም፣ አንድ ትልቅ ችግር አለን። ስንሳሳት ተሳሳትን ማለት፣ ስንዋሽ ዋሸን ማለት አንወድም። ትችትም አንቀበልም።

    በአንድ ወቅት አንድ ትልቅ የአሜሪካ ዩኒቬርሲቲ ውስጥ አስተማሪ ነበርሁ። በየሣምንቱ Seminar አለ፤ አስተማሪዎቹ ያደረጉትን ምርምር ለ 80 ያህል ከፍተኛ አስተማሪዎች ጉባዔ ያቀርባሉ። ታዲያ ባንድ ወቅት እኔም ከጎረቤቶቼ ምሁራን ጋር ወደ አዳራሹ ስወርድ ሁለት ነጭ ምሁራን እየተቀላለዱ አዳራሹ ደረስንና አንዱ ምርምር አቅራቢ ኖሮ ትንሽ ቆይቶ ወደ መድረኩ ወጥቶ ምርምሩን አቀረበ። አስተያየት በሚሰጥበት ሰዓት፣ ያ አብሮን ወደ አዳራሽ የገባው ሌላው አስተማሪ በጣም ሰፋ አድርጎ በመረጃ አስደግፎ ጓደኛውን ተቸው። ምርምር አቅራቢውም አስተካክላለሁ ብሎ እጅግ በጣም አክብሮና አመስግኖ፣ ትችቱን አምኖ ተቀብሎ ከሌሎችም አስተያየት ሰምቶና መልሶ ሲጨርስ ተቀመጠ።

    ከአዳራሹ ስንወጣ ሁለቱ እንደገና ተገናኙና፣ ምርምር አቅራቢው እንደገና አመስግኖ፣ እንደተለመደው እየተቀላለዱ ወደ ቢሮ ተመለስን። ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይኸ ባህል የለም። ቲዎድሮስ ወንድሜም በጀኔራል የተተቸኸው አንተ ባትሆንም ለጓደኛህም ወይም ለምታደንቀው ሰው ብለህም ያደረግኸው ከሆነም ትችት መልመድ አለብህ ።

    እኔም ጀኔራል ማሞን፣ ባላውቃቸውም፣ የገለጽህበት መንገድ አሳዝኖኛል። ከአገር ሕልውና አኳያ ብዙ ያሰብህበት አልመሰለኝም። እስክንድር የማደንቀው ልጅ ነው። እንዲያውም ለአባቱም ልዩ አድናቆት ነበረኝ። ግን ከነምሬ ወዳጆ፣ ከነ ሻለቃ ተስፉ፣ ከነ መከታው፣ ከነዘመነና ከሌሎቹም የትግል ጓዶቹ ተለይቶ ለምን ድርድር ጀመረ ለሚለው ጥያቄ በቂ ምክንያታዊ ማብራሪያ አልሰጠህም። አላዳላህም ? አኩርፎ ወደ ድርድር የሄደው የተለያዩ ጓዶቹ የፋኖ መሪነቱን ስላልተቀበሉት ከሆነ፣ ትልቅ ስይሕተት ነው። ለሥልጣን፣ ለዝና ወይም ለገንዘብ ብሎ ፋኖነትም አይጠቅመንም። ይህ ዓይነት መሪማ ለዛሬው ውድቀትና ዕልቂት ያበቁን መለስና መንግሥቱስ ነበሩ አይደል ?

    ለሥልጣን፣ ለዝና ወይም ለገንዘብ ተብሎ የድሀ ልጅ በእሳት ውስጥ ሲማግድ ቆይቶ መሪ የሚሆን አይረባንም። የፋኖ መሪ አትሆንም የሚል ተቃውሞ ሲነሳ፣ ከሥልጣን ከዝናና ከገዘብ የላቀ ዓላማ ያለው ሰው “እሺ!” ብሎ በትግሉ ቢቀጥል ኖሮ እንደ እነ ማንዴላ የመሆንና የመደነቅ ዕድል ነበረው። ጉሮሮ የሚውጠውን እጅ ይመጥነዋል ሲባል አልሰማህም ? ደግሞ መሪ የሚመርጡ እንዳንተና እንደ እኔ ዳር ቆሞ ተመልካች ሳይሆን፣ የእሳቱ ወላፈን የሚገርፋቸው ናቸው። በአሜሪካ ወይም ሌላ አገር እየተምነሸነሹ፣ ለጦር ሜዳ መሪ እኛ እናውቅላችኋለን አያስሄድም። ይህን መቀበል ግዴታ ነው።

  2. I don’t think this is a fair assessment of General Tefera and Eskinder Nega. Both tried their best to bring about true change in Ethiopia. General Tefera tried to overthrow TPLF from within while Eskinder was doing it from outside. Both paid enormous price for daring that. Finally, Eskinder changed his view and joined the armed struggle. That was a wise decision.

    General Tefera said that he tried several times to bring the Fano leaders together but Eskinder made it impossible. According to the General assessment Eskinder is using the armed struggle to negotiate for power rather than arrive to fundamental change.

    I agree with the General assessment after listening Eskinder’s several interviews for the last few months. Especially the one he gave to Jeff Pearce was eye opening as he brought himself as the only accepted leader. It is time Eskinder give up the leadership position.

  3. ቴዎድሮስ ኡጋንዳ ነህ የት ነው ያለኸው? መቼም የእስክንድር ጉዳይ ሰው ሁሉ ግራ ገብቶት ማንሳት መጣል ከጀመረ ቆየ አንተም በእስክንድር አላመንኩበትም ካለው ሁሉ ጋር ተላትመህ አትችለውም። ቢያንስ ጀነራሉን ለመተቸት ከሱ በተሻለ ቁመና ላይ መገኘትን ይጠይቃል ስለ እስክንድር አካሄዱ ያልተመቻቸው ብዙ ስለዘከሩ ወደዛ አልመለስም አንዱም ከክሱ መሃል ዲያስፖራው በሚሰበስበው ገንዘብ ስራ ፈቶችን እያደራጀ ህዝብን አያሳክር ነው የተባለው ጀነራሉ በዚህ እድሜው ሰጠ ያልከው አስተያየትን ያልሰጠ የለም ትንሽ ዳረጎት ቢጤ ከሚሰፈርላቸው በስተቀር። አይዞህ በለው ስትገናኙ።.

  4. Thank you for being a balanced voice of reason. Hullum negher mizan linorew yigebal. Yetinantun wuleta gedel yemiket aqerareb metarem allebet. Tebarek.

  5. A Call for Unity and Strategic Action:

    In these challenging times, let us choose our words with wisdom—not to divide, but to unite. Every statement we make should serve to strengthen the bond between the people of Gonder, Gojam, Wello, and Shewa, and ultimately, all of Ethiopia. Our true power lies in unity, and our words must always reflect that greater purpose.

    Theodros, I understand your respect for the good general, but your criticism could have been expressed in a more constructive manner. Let us remember that our words should guide and uplift, not dwell on the past in ways that weaken our cause.

    I stand with Eskinder, but I do not claim he is without fault. However, when we speak of his mistakes, let it be with wisdom and dignity—criticism should be constructive, not destructive. It should refine and strengthen, not break and divide. Division is a weakness we simply cannot afford, especially now.

    As for the so-called prime monster, both locally and internationally, it is clear that he lacks the capacity to lead a nation. We have witnessed unthinkable atrocities—people burned alive, begging for death to escape their suffering. We feel sorrow even when slaughtering a sheep, yet we watch as human beings are massacred without mercy. This is beyond political failure—it is a humanitarian catastrophe. Abiy and his inner circle are nothing short of evil in human form.

    Abiy has survived not because of his strength, but because of Fano’s division. The only reason he remains in power is our inability to unite. Anyone who challenges him should be welcomed, as the real battle is not among us but against a regime that has brought destruction upon our people. Right now, the focus must be on unity and on strategizing to checkmate Abiy and his cronies. Internal conflicts only serve our enemies—we must rise above them and work together for a greater cause.

    The reckless behavior of this boy-king, his mockery, and his insensitivity are not just personal flaws—they symbolize the suffering of a nation. We cannot afford to waste our energy on outrage alone. Instead, let us channel our focus toward unity, strategic action, and the power of collective resistance. Now is the time to think ahead, to organize, and to act with precision.

    Let every word we speak be a step toward a stronger, more united Amhara and, ultimately, a stronger Ethiopia. Let us inspire, mobilize, and act with purpose. The future is in our hands—let’s build it together.

  6. ቴዎድሮስ ሃይሌ ግብረ መልሱን አየኸው? እንዲህ ቸኩለህ አለእውቀት የምትጽፈው ከወገን ጋር ያላትምሃል ትንሽ ሽርፍራፊም እኛ ከሰበስብነው የሚሰጡህ ከሆነ ይቅርብህ፡፡ ክፉ እከክ ይለቅብሃል ወገን ላይ መከራውን አታብዛበት መቼም ካሁን በኋላ ሰው መክሮህ ከመንገደህ የምትወጣ አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ ሰው አክብር ስውየው አሽቃባጭ ቢሆኑ ቢያንስ ቢያንስ የአረጋዊ በርሄን፤ብርሃኑ ነጋን፤አገኘሁ ተሻገርን፤የብርሃኑ ነጋን፤ የግርማ ሰይፉን፤የበለጠ ሞላን፤የደመቀ መኮንን፤እና ጄነራል ተብዬዎችን ቦታ አያጡም ነበር አገር ለማስቀጠል መሰለኝ በዱር በገደል ላይ ታች የሚሉት ይህንን አክብርላቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Next Story

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

Go toTop