የጅማው ስብሰባ – የሚኒሊክ ቤተመንግስት የሚባል የለም፥ የሚኒሊክ ሀውልትም ይነሳል፥ ገና እናራግፋለን</p>
የጅማው ስብሰባ – የሚኒሊክ ቤተመንግስት የሚባል የለም፥ የሚኒሊክ ሀውልትም ይነሳል፥ ገና እናራግፋለን
የጅማው ስብሰባ – የሚኒሊክ ቤተመንግስት የሚባል የለም፥ የሚኒሊክ ሀውልትም ይነሳል፥ ገና እናራግፋለን</p>
የጅማው ስብሰባ – የሚኒሊክ ቤተመንግስት የሚባል የለም፥ የሚኒሊክ ሀውልትም ይነሳል፥ ገና እናራግፋለን
አዳመጥኩት። ግን ይህን ሁሉ ዝርዝር ሁኔታ እንዴት አገኘኸው? ነው ወይስ የፈጠራ ወሬው ከእውነቱ ይልቅ ይጣፍጣል? በቅርቡ ከአንድ የፓለቲካ ትራፊ ሰው ጋር ስናወራ አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ አወጣ በማለት ንግግሩን ሊቀጥል ሲል ተው ወንድሜ አሳና ዘንዶ አንድ ባህር ውስጥ አይኖሩም። ተረቱ ውሸት ነው ስለው። ቱግ ብሎ እንዲህ ያላችሁት ናችሁ የሃገራችን ባህልና ወግ የምታጠፉት በማለት የስድብ መርጉን ሲለቀው በቃ በማለት ስልኬን ዘጋሁ። ስለ ጅማው ስብሰባ እዚህ ላይ የተዘገበልን ወሬ ምናባዊነት ባህሪ ይታይበታል። የሚያሳዝነው መንግስትንም ሆነ ታጣቂ ሃይሎችን ለማጥላላት ወይም ስኬታቸውን አጋኖ ለመናገር የምንጠቀምባቸው ቃሎች ሁሉ ከእውነት የራቁ መሆናቸው ነው። በእኔ እምነት እንኳን ዋሽንግተን ላይ ሆኖ በስማ በለው የሚሰማው ዘጋቢ ቀርቶ በስብሰባው ላይ የተገኘም ጉምቱ ጋዜጠኛም እንዲህ አቀናብሮ የስብሰባውን ጭብጥ መያዝ አይችልም። ብቻ ስንፋለም፤ ስናፋልም፤ ስንወጋ፤ ስናዋጋ ዓለም ጥሎን እያለፈ ነው። የሚኒሊክ ቤተመንግስትም ሆነ የሚኒሊክ ሃውልት አይፈርስም። ደግሞስ ቢፈርስ ምን ያስደንቃል? ጊዜ ጠገብ የሆኑ ሃውልቶችና ቤተመንግስቶች ታሪክን በረሳ ትውልድ ሲደረመሱ አይናችን አላየም እንዴ? ለገባው መፍረስ የነበረበት እንድንከፋፈል ወያኔና ኦነግ ያቆሙት የአኖሌ ሃውልት ነበር። ያም አይሆንም ውሸትን ሰው ተግቶታልና! እንደ እንቁራሪት አንድ ሲጮህ አብሮ መጮህ። አታድርስ ከማለት የተሻለ መድሃኒት ለሃበሻ ፓለቲካ አይገኝም።
የጠ/ሚሩ መንግስት ኢትዮጵያን ወደኋላ ጥሎ ለኦሮሞ ብቻ ቢቆም የሚጎዳው መንግስቱንና የኦሮሞን ህዝብ ነው። በምንም የፓለቲካ ስሌት ቢሆን የኦሮሞ ህዝብ ብቻዬን ልብላ፤ ብቻዬን ልኑር ብሎ አያውቅም። እናውቅልሃለን የሚሉ ተምረናል የሚሉ ጥቂት የኦሮሞ ስብስቦች ግን ልክ እንደ ወያኔ በኦሮሞ ህዝብ ስም እየነገድበት ኑረዋል ዛሬም ይነግድበታል። እነዚህ የፓለቲካ ጽፈኞች የኦሮሞ ህዝብን አይወክሉም። የዓለማችን የፓለቲካ ንፋስ ሳይታስብ አቅጣጫ እየለወጠ ሃገራትን እየናጠና እያፈረሰ ህዝብን ለመከራ እየበተነ እንደሆነ አፍጠን እያየን ነው። ልብ ገዝተን ተቻችለን መኖር እስካልቻልን ድረስ የኢትዮጵያም እድል ፈንታ መናድና መበተን ነው። ስለዚህ ዘገባ ስናወጣ፤ ወሬ ስናካፍል፤ በድህረ ገጾች ነገርን ስናሰፍር ሽራፊ ሳንቲም ለመልቀም ይዘትና ቁመቱ የማይገናኝ ወሬ ከማናፈስ ይልቅ እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደሩ ተገቢ ይመስለኛል። ለዚያውም የሚያሳድር ወይም ማደሪያ ከተገኘ!
አንድ ነገር እንደምሳሌ ልውሰድ። ጠ/ሚሩ የትግራይን የፓለቲካ ውጥንቅጥ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ የተለያዪ ድህረገጾች ያሰፈሩትን ስመለከት በጣም ተገርሜአለሁ። ሁለቱን ብቻ እጠቅሳለሁ። በቅድሚያ ግን ጠ/ሚሩ ለለቀቀው መግለጫ የራሴን እይታ መስጠት እፈልጋለሁ። መግለጫው ልመና አይሉት ማስጠንቀቂያ ዝም ብሎ ቃልን ያባዛ ቀደም ሲል በቃልም ሆነ በጽሁፍ ትግራይን አስመልክቶ ከለቀቃቸው ሃሳብ ጋር የሚያያዝ ነው። ሲጀመር የትግራይ ህዝብ ያለፈ ታሪኩን አልረሳም። እንዲህ ነበር እንደዛ ነበር ማለቱ ቃላት ለማራባት ካለሆነ በስተቀር ጠቃሚነት የለውም። የትግራይ ህዝብ ችግሩ ወያኔ ነው። ጠ/ሚሩ call a spade a spade የሚለውን መርህ ተከትሎ የትግራይ ህዝብ ጠላቱ ወያኔ ነው ቢል ተቀባይነት በኖረው። ዝም ብሎ እንደ ደመራ ተኳሽ ዙሪያውን መዞር ግን ጠቃሚነት የለውም። ለተረዳ ሰው እኮ ራሱ ብልጽግና ከእስር ፈቶ፤ ባህርማዶ ያሻገራቸውና በመቀሌ የተወሸቁት የእድሜ ልክ ፓለቲከኞች አይደሉም እንዴ የትግራይ የመከራ ዝናብ አዝናቢዎች? ስለዚህ ብልጽግናም ተጠያቂ ነው። ህግ አላስከበረምና! ስለሆነም የጠ/ሚሩ የጽሁፍ ዲስኩር የትግራይን ህዝብና ወያኔን ለያይቶ ማየት መቻል ነበረበት። አብይ ለወያኔ ስስ ልብ አለው። ሁልጊዜ የወያኔን ሁኔታ በ”Kiddy Gloves) አያያዝ ነው የሚይዘው። ግራ ያጋባል። ስለዚህ የጠ/ሚሩ ለትግራይ ያቀረበው ጥሪ ድብስብስና ተበዳይና በዳይን ያለየ በመሆኑ ፍሬፈርሲኪ ነው። ወያኔ መቀሌ ላይ ተቀምጦ ይስቅበታል!
ከላይ ወደ አልኳቸው ሁለት የድህረ ገጽ/ ዪቱቭ ቱልቱላዎች ልመለስና ሃሳቤን ልዝጋ።
አንደኛው የወያኔ የቅርብና የሩቅ አዳሪ የሆነው ያየሰው ሽመልስ ነው። “የአብይ አዲስ የጦርነት ጥሪ – ትግራይን አሁንም አሰለቅሳለሁ” በሚል ርዕስ ያለ የሌለውን ቀባጥሮ ይህንም ያንም ጥላሸት ቀብቶ ያለፈና የአሁን የትግራይን መከራ እያነሳና እየጣለ ትረካውን ለዝግጅቱ ከሰጠው ርዕስ ጋር ለማዛመድ ሞክሯል። በየትኛውም የጠ/ሚሩ መልዕክት ላይ “ትግራይን አስለቅሳለሁ” የሚል ቃል በጭራሽ ሽታውም የለም። ይገባናል እንዲህ ያለው ያለነደደ እሳት እንዲነድ ነዳጅ ማርከፍከፍ የሚጠቅመው ማንን እንደሆነ። ይህ ጋዜጠኛ “የሴራ ርካብ የደም መንበር” በሚለው መጽሃፉም ላይ ተራ ሃሜት ሳይቀር መጻፉ ቦጅቧጃነቱን ያሳያል። ግን ለምን ሰለ ወያኔ በ 27 ዓመት የግዛት ዘመኑ በሃገራችን ስለ ፈጸመው በደልና መከራ አይጽፍም? ሌላው ቱልቱላ ይህኑ የጠ/ሚሩ የጽሁፍ መልዕክት ተመርኩዞ “የአብይ ዘረፈጅ ደብዳቤ” በማለት በቃላት ሲጫወት መስማት የሃበሻ የፓለቲካ ህመማችን ጽኑ መሆን ያሳያል። ሚዛን የደፋ፤ እውነትን የታከከ፤ በዘርና በቋንቋ እንዲሁም በሃይማኖት ያልተመነዘረ ዘገባ መቼ ይሆን የምንሰማው ወይም የምናነበው? ያ ጊዜ ይናፍቀኛል። ሌላው ሁሉ አሻሮ ፓለቲካ ነው! በቃኝ!
አቦይ ተስፋይ ሰላም ነዎት? እርሶስ ሃሰት መሆኑን በምን አወቁ? ስንት አዋቂ በሚመሳከርበት መድረክ በቅጡ ያልተብላላ ጽሁፍ እየላኩ ክፍሉን መደበሪያ አያድርጉት፡፡ ብዙ ምሁራን በሚጽፉት መጣጥፍ ቀለም እይደፉበት እነሱም የለፉበትን እንደገባዎት ሁሉ ላርም ሲሉ ምሁራኑ ሽሽትን መርጠዋል፡፡ ጽሁፎ ሁሉ ኮፒ ፔስት የሚሉትን አይነት ሁኗል ተመሳሳይ ነው፡፡ የሚወረወርሎት ምናምን ነገር ካለ ይቅርብዎ በዚህ መልኩ የሚመጣ ክፉ እከክ ይለቅብዎታል፡፡ እርሶ የጥራት መለኪያ ሁነው የሚላከውን ጽሁፉን ሁሉ አቆሽሸውታል ኢትዮጵያም ውስጥ በእርሶ አረዳድ ሰው እየሞተ አይደለም፤ ነገሮች በስርአት እየሄዱ ነው አይበሉን እርሶ ባለስልጣን ጋር ግንኙነት ቢኖሮትም እኛ ደግሞ መከራ የሚበሉ ዘመዶች አሉን ይተው ብለናል፡፡ እርሶ ጋቢ ለብሰው ሂተር ከፍተው የሚላክሎትን ፖስታ እየመነዘሩ ይኖራሉ ህዝቡ ግን በስቃይ እየኖረ ነው አያላግጡ ብያለሁ አይቼዎታለሁ በተደጋጋሚ ውርድ ከራስ፡፡ ወይም ደግሞ የሚነበብ ሃሳብ አለኝ ካሉ እራሱን ችለው ጽሁፍ ያስነብቡን፡፡
ገለባ ከአንተ ጋር ማን ይዳረቃል።እሳት ታቅፈህ ተኛ!
አቦይ እናመሰግናለን ስለ ምሁራዊ ግብረ መልስዎ እንዲህ ነው በእውቀት የታሸ ምሁር።