ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም በ1927 በዎላይታ በዳምታ ሶሬ ወረዳ የተወለደ በእናትም በአባትም ወላይታ ነው። ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ሀይለማርያም በወላይታ ተወልዶ ያደጉ የወላይትኛ ቋንቋ ጥሪት የሚናገሩ በሕይወት እያሉ አንዳንዴ አማራ ነው፣ አንዳንዴ ኦሮሞ ነው፣ ሌላ ጊዜ ከፋ ነው ይላሉ። ይሄ ሁሉ የኔ ነው የኛ ነው የሚል ሽሚያ ከምን የመነጨ እንደሆነ አይገባንም።
ማንም ምንም ብልም ይህ ምርጡ የዎላይታው ኮከብ በፊውዳል አገዛዝ ወደ ኋላ የቀረችውን ሃገር ኢትዮጵያ ፊውዳል አገዛዝን በመገርሰስ ሀገርቷ ወደ ፊት ጉዞ ያስጀመረ ምንም እንኳን ብዙዎች ቢሞቱ እና ቢጎዱም ሃገር የመራ የመላው አፍሪካውያንን የነፃነት ትግል የደገፈ የጥቁሮች መከታ የእኩልነት ቀንዲል የለውጥ አራማጅ አብዮተኛ ድንቅ መሪ ነው።
ኢትዮጵያ ያለ ዎላይታ ምንም ናት ነገር ግን ወላይታ ለኢትዮጵያ ነጻነት፣ ለሀገር ክብር፣ ለሉዓላዊነቷ እንዲሁም በሀገርቷ ሽግግር ፖለቲካ ውስጥ ቀዳሚ መሃንዲስ ዎላይታ መሆኑ ሰማይ ምድር የማይክደው ሀቅ ነው።
ዎላይታ ለዚህች ሀገር ብዙ ሥራ ሰርቷል፣ ብዙ ዋጋና መስዋዕት ከፍላለች። ኢትዮጵያ ለወላይታ የሚትከፍለው ብዙ ዕዳ አለባት።
ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ሀይለማርያም የኢትዮጵያ ዘውዳዊ አገዛዝ በመጣል በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲ ስርዓት በመዘርጋት ሀገሪቱን ከ1966 እስከ 1983 ድረስ ለ17 ዓመታት የሀገርቷን ሉዓላዊነት እና ክብር ሳያስደፍሩ የመሩ ለሁሉም አፍርካዊያን ምሳሌ የሚሆኑ ጀግና መሪ ናቸው።
ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም በ1927 በዎላይታ መወለዳቸውን እንኳን ታዋቂው የአለምአቀፉ ሚዲያ ቢቢሲ ከ18 ዓመታት በፊት በሰራው ዝርዝር ዘገባውን እያመለከተ እያለ የኛዎቹ ግን አንዴ አማራ ነው፣ አንዴ ኦሮሞ ነው፣ አንዴ ከፋ ነው እያሉ ገና ከወዲሁ ታሪክ ለመቀማት ይጣደፋሉ።
ሙሉ ዘገባው Link ከታች በአስተያየት መስጫ ተቀምጧል። በርግጥ ፕሬዚዳንት መንግስት ሀይለማርያም የሀገርቷ በሚመራበት ጊዜ ለአንድ ብሄር ያላዳላ፣ ማንንም በአንድ አይን የሚመለከት ደንቅ መሪ ስለሆነ የራሱን ብሄር መግለጽ አይፈልግም።
ለመሆኑ በኢትዮጵያ ለምንድነው ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች የወጡበት ብሄር እና አከባቢ ላይ የይገባኛል ሺምያ እና ክህደት የሚበዛው ይላሉ ?
ዜና ወላይታ
ዜና ወላይታ ወንድሜ ማንም አልተሻማህም አትስጋ ብሮ ያንተው ይሁን ብቻ ከላይ ዲሞክራሲ ያመጡ ላልከው ብዙዎቹ ከተስማሙበት እኔ ግድ የለኝም መቼም የማንሰማው ጉድ የለም እሱ ያደረሰው በቤትህ ይድረስ አልልም ምክንያቱም ረጋሚ ተደርጋሚ ይባላልና። ሓይለ ማርያም ደሳለኝም ነበረልህ እኮ ደምረህ ብትሰቅለው።
http://news.bbc.co.uk/2/hi/africa/6171927.stm
ያ የቢቢሲ መጣጥፍ በስህተት የተሞላ ነው።
ያም ሆኖ ግን መንግስቱ የወላይታ ጎሣ ናቸው አላለም።
መንግስቱ በወላይታ ተወለዱ ብቻ ነው ያለው።
Mengistu was part oromo and part Besketto
መንግስቱ የሚኮራበት ሰው አይደለም።
በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲል የንጹሃንን ደም አፍስሷል።
መንግስቱ ኃ/ማርያም ያሳደጉትን ሁለቱንም ጀነራሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል:: ሁለቱም ኤርትራዊያን ነበሩ። ጀነራል ሃይሌ ባይከዳኝ እና ጀነራል አማን ዓንዶም
ALEMU ኤርትራዊ ስለሆኑ ነው የገደላቸው? የገደለው ሁለቱን ብቻ ነው? ከሱ በላይ አንተ ጎሰኛ ሁነሃል? መንግስቱ ማን ቀረው ውብ አንችም በልጆቿ ተጸሎት ነው የተረፈችው፡፡ እንዲህ አይነት አስተያየት የመንግስቱን ደጋፊ ያበዛብሃል፡፡
መንግሥቱ ኃይለማርያምን ለወላይታ ሕዝብ ጋር ማጣመርና መንግሥቱን የወቀሰ ወላይታን ነካ የሚለው አካሄድ በጣም ያሳዝናል። ወጋችን ሆነና ሁሉን ነገር በትውልድ ሐረግ መተርጎምና መመልከት የዘመናችን ፈሊጥ ሆኗል። መንግሥቱ ኃይለማርያም ወላይታ ነኝ ብሎ አይደለም አንድ ትውልድ የጨረሰው። የራሱን ወላይታ ንጡር ልጆች በልቷል። በዚያ ጊዜ ደርግ ሆኖ ነው፣ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ነው ኢትዮጵያዊያንን የፈጀ። በምንም መመዘኛ እሱ በበጎ የሚታይ ገጽ ሊኖረው አይችልም። ይልቁንም ባለበት ሲጸጽተው የሚኖር የድሃ ልጆች ደም በጁ ይዟል። የዘመን አመጣሹ ሁሉን በብሄረሰቤ! አይስኬድም።
መንግሥቱ ኃይለማርያምን ለወላይታ ሕዝብ ጋር ማጣመርና መንግሥቱን የወቀሰ ወላይታን ነካ የሚለው አካሄድ በጣም ያሳዝናል። ወጋችን ሆነና ሁሉን ነገር በትውልድ ሐረግ መተርጎምና መመልከት የዘመናችን ፈሊጥ ሆኗል። መንግሥቱ ኃይለማርያም ወላይታ ነኝ ብሎ አይደለም አንድ ትውልድ የጨረሰው። የራሱን ወላይታ ንጡር ልጆች በልቷል። በዚያ ጊዜ ደርግ ሆኖ ነው፣ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ነው ኢትዮጵያዊያንን የፈጀ። በምንም መመዘኛ እሱ በበጎ የሚታይ ገጽ ሊኖረው አይችልም። ይልቁንም ባለበት ሲጸጽተው የሚኖር የድሃ ልጆች ደም በጁ ይዟል። የዘመን አመጣሹ ሁሉን በብሄረሰቤ! አይስኬድም። እኔ ግን ይቅር ብየዋለሁ
ይህ ጽሁፍ ባለማስተዋል የተላከ ቢሆንም የሚናቅ ግን አይደለም ብዙ ቁም ነገሮችን አጭቋል። ለዚህ መልስ መስጠት ለኢትዮጵያ ችግር መልስ መስጠት ሁኖ ታይቶኛል። እንደ ጸሀፊው አባባል የተወለዱት ወላይታ በመሆኑ ወላይታ አድርጓቸዋል። እዚህ ላይ ትግሬዎች በቦታ አጥር በረት ህዝብን ከትተው ስም ሰጥተውታል። ነገር ግን በዛ በረት ውስጥ የታጨቀው ህዝብ እነሱ የሰጡት ስም ይመጥነዋል ወይ? ለምሳሌ የፊት ስትራክቸራቸውን ከመመለከት ባሻገር በታሪክም የአሩሲ ህዝብ የከምባታና ሀዲያ ህዝብ ሁኖ ዛሬ ኦሮሞ ነህ ተብሎ ኦሮሞ ሁኗል። ወደ ወለጋም ወደ ጅማም ሲመጣ እንዲሁ ህዝቡ ማንነቱ በግድ የተለወጠ እንጅ ሁኖ የተፈጠረውን ጠብቆ የቆየ አይደለም ከባሌ በስተቀር። በቅርቡም የጅማው የኦሮሞ ስብሰባ ላይ ይህ አሰራር ውጤት ስላመጣ በስፋት እንዲቀጥል የኦሮሞ ባለስልጣናት ከስምምነት ደርሰዋል። እንደው ለናሙና ቢወሰዱ ብርሀኑ ጁላ፣አባ ዱላ ገመዳ፣አብይ መሀመድና ከፊት ለፊት ያየናቸው ስልጣናቸውን ለማስቀጠል ኦሮሞ ሆኑ እንጅ የደም ኦሮሞነት ያላቸው አይደሉም።
ማንነትን በተመለከተ ዛሬ በማያሻማ ሁኔታ ማን ምን እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ የ DNA ማሽን ስለተፈለሰፈልን በየወረዳው ተተክሎ ምርመራ ቢደረግ በሀሰት ትርክት ሲተላለቅ የሚውለው ጅል ህዝብ አደብ ገዝቶ ትግሉ ከረሀብና ድንቁርና ጋር ይሆን ነበር።
ዜና ወላይታ የኛ ናቸው ያላቸው መንግስቱ ሐ/ማርያምም ስማቸውን መልሰው ወደመጡበት ሀገር ተልከው በሳቸው ግፍ የደረሰበት ህዝብ ከጋናም ይሁን ቡርኪና ፋሶ ካሳ ሊያገኝ ይገባል። ስለዚህ የሀሰት ማንነት አንድ ሴንቸሪ ስላባላን በዚህ መንገድ ነገሮች ቢታዩ እልቂት በኢትዮጵያ ይቆማል የሚል እምነት ይኖራል። ነገ አቶ ዳንኤል ከወላጅ አባቴ ተሰርቄ እንጅ ኦሮሞ ነበርኩ ላለማለቱ ማረጋገጫ አይኖርም።
ግማሹን ጠጥቶ ነው ቀሪውን ቢኖ የደፋው