በ
ህወሃት መዳፍ ስር የነበረው መጅሊስ ህዝባዊ እንዲሆንና የመንግስት ጣልቃ ገብነት እንዲያበቃ የተቻለንን ሁሉ አድርገናል። ያኔ በዘመነ ህወሃት ከመንግስት ጋር በመተባበር ሙስሊሙን ሲያስመቱ የነበሩ ሁሉ «የብስራት ዜና ተሰማ» የሚል መውጫ ቀዳዳ ተሰጣቸው።ለሐጢዓታቸው ማስተስረያ «እርቅ» ላይ መሰረት ያደረግ አንድነት እውን ይሆን ዘንድ ይሰራሉ ተብሎ ሲጠበቅ ‹የለመዱት ልማድ ያሳድዳል ከማእድ› ሆነና ነገሩ በኢህአዴግ ቁጥር ሁለት (ብልጽግና) እየታገዙ ሙስሊሙን ማሀረሰብ ማተራመሱን ቀጠሉ።
ችግሩን መሸፋፈንና በአንድ አዛውንት ላይ መጫኑ አያዋጣም።ችግሩ የመዝሃብ ጉዳይ አይድለም።ችግሩ የድሜ ባለጸጋ የሆኑ ግለሰብ (ግለሰቦች) በብቃት የሚተውኑት አይደለም።ችግሩ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለዘመናት በማሽመድመድ እንደ ብዙኋንነቱ በአገሩ ሁለንተናዊ የዲሞክራሲ መዋቅር ውስጥ ተጠቃሚ እንዳይሆን የሚፈተል ሴራ መሆኑ ነው።ችግሩ ሲሶ መንግስትን ተቀራምተው የነበሩ የቢሮክራሲው አካላት ዛሬም ሁለተኛ ዜጋን ለመፍጠር የሚያደርጉት መፍጨርጨር ነው። ሙስሊሞች በበዙባቸው ክልሎች በውጭ እርዳታ መስፋፋት የሚሹ ሐይሎችና ይህንን ለማስፈጸም የሙስሊሙ ማህበረሰብ አካላትን ተባባሪ (Trojan horse) በማድረግ እየተቅለሰለሰ የሚሰራው Abiy Ahmed Ali ነው ችግሩ።
ወደ ስልጣን ከመጣበት ግዜ ጀምሮ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማናገር ፈቃደኛ ያልነበረው አብይ «ድምጻችን ይሰማ» የሚለውን ቃል ከአፉ ያወጣው ዘንድ ብዙ ትችት ደርሶበታል።ዱባይ ላይ «ሱኒ ሰለፊ» ብሎ ከቀላቀለ በሗላ ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ሔዶ «ድምጻችን ይሰማ» የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ግዜ መተንፈሱ የሚዘነጋ አይደለም።( https://tinyurl.com/52uxmz7s ) ብልጽግና በዘንድሮው ጉባኤው ላይ ለውጡን አስመልክቶ ሲዘግብ ለትግሎች ሁሉ መሰረት የሆነውን «ድምጻችን ይሰማን» ነጥሎ መተው ምንን ያሳያል?
ሙሲባው አብይ አህመድ አለም በአድናቆት የሚዘክረውን የሙስሊሙ ትግል አምኖ ከሚቀበል የሙስሊሙን ትግል ሲመሩ ከነበሩ የመስዋ እትነት ተምሳሌቶች ጋር ከፊት ለፊት እየተቅለሰለሰና እየተቃቀፈ ከኋላ በጩቤ ቢወጋ ይመርጣል።ስለዚህ የመጅሊስን ችግር ስናስብ አብይ አህመድ ተልእኮውን ለማስፈጸም የሚጠቀምባቸውን የዋሃን እናስተውል።ችግሩን ለእድሜ ባለጸጎች ትከሻ ላይ መቆለል ሳይሆን እነዚህን የእድሜ ባለጸጎች መጠቀሚያ በማድረግ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ መከፋፈል የሚፈጥረውን
የትላንትናውን ሙስሊም ተጠያቂ ማድረጉ ግድ ይላል።
አብይ አህመድ የፈተለውን ማሰሪያ ገመድ በአንድ የስልክ ጥሪ ወይም በመልእክተኛ ይፈታዋል።ግን አብይ የመጅሊስን ጉዳይ ከሚፈታ፣ድምጻችን ይሰማን አምኖ ከሚቀበል የፎቶ አጋጣሚ የሚፈጥርለትን ማንኛውንም ትርኢት ከመተግበር ወደ ኋላ አይልም።ምን አልባትም የሸረባቸው ሴራዎች ሁሉ ካልሰሩለት የመጅሊሱን ችግር የፈታ መስሎ «የብስራት ዜና ተሰማ ቁጥር ሁለትን» ከመተወን ወደኋላ የማይል አይን አውጣ መሆኑን ልብ እንበል።ነገሮች አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዳይመስሉ ጣቶች ወደ ሙሲባው አብይ አህመድ ይጠቆሙ።
ልብ ያለው ልብ ይበል!