ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ዐማራ ጨቋኝ ነው አለች (ዘ-መቀጣዋ)

March 27, 2022
የሚገርመው ዳግማዊት ሞገስ የብልጥግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ መህኗ ነው። በሰሞኑ ቃለመጠይቋ ቃል በቃል ከዚህ በታች የተቀመጠው ተናግራለች።
“በኢትዮጵያ ከተማሪዎች አብዮት ጀምሮ ሦስት ያልተመለሱ ጥያቄዎች ነበሩ። እነሱም የመሬት፣ የብሔር እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ናቸው። እስካሁን የመሬት እና የብሄጸሔር ጥያቄዎች ተመልሰዋል። ያልተመለሰው የዴሞክራሲ ጥያቄ ብቻ ነው። ብልጥግናም ግቡ ያልተመለሰውን የዴሞክራሲ ጤያቄ መመለስ ነው።” በማለት ነው ቀድፍረት የተናገረችው።
በ2012 ጅማ በተካሄደው የኦዴፓ ጉባኤ የኦዴፓ መግለጫ በተቃራኒው “በኢትዮጵያ የብሔር ጭቆና አልነበረም። የነበረው የመደብ ልዩነት ነው” ማለታቸው ይታወሳል።
የወያኔ ፈጣሪ አባት አቶ ስብሓት ነጋ በበኩላቸው አንድ ጊዜ “የብሔር ጭቅና አለ ያልነው ለማታገያ ፈልገነው ነው” ብለው ነበር።
ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ኦነግን ለማስደሰት ከኦነግም በላይ ሆና ቀርባለች። እንግዲህ ልበ በሉ፣ የዐማራ ሕዝብ ጥያቄ የሚፈታው በእነ ዳግማዊት ምገስ ነው¿¿
(ዘ-መቀጣዋ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“በኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ አደገኛና አስፈሪ የሆነ፣ የሀገራዊ ቀውስ ምክንያት መሆን የሚችል ጉዳይ ቢኖር የፖለቲካ አቋምን ከእምነት [ጋር] የመቀላቀል ጉዳይ ነው” አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

Next Story

ሙሲባው አብይና የመጅሊሱ ችግር – ቢቢኤን

Go toTop