አስገደ ገ/ስላሴ በባለስልጣናቱ ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰባቸው ገለጹ

February 24, 2015
አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

መጽሐፋቸው ላይ ስም አጥፍተዋል በሚል ተከሰው የህወሓት ባለስልጣናትን በመከላከያ ምስክርነት ቢጠሩም ባለስልጣናቱ በተደጋጋሚ በቀጠሮው ቀን ባለመገኘታቸው ለምስክሮች በሚያወጡት ወጭ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰባቸው አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

ጥር 10/2007 ዓ.ም አቶ አስግደ በምስክነት ከጠሯቸው የህወሓት ባለስልጣናት መካከል ጀኔራል ጻድቃን ሲገኙ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሃዬ፣ አርከበር እቁባይና ሌሎችም ባለስልጣናት ያልተገኙ ሲሆን ለየካቲት 13/2007 ዓ.ም በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ሲወሰን ጄ/ር ጻድቃንን ጨምሮ ሌሎቹም በትዕዛዙ መሰረት ሳይገኙ ቀርተዋል ብለዋል፡፡ ባለስልጣናቱ በዳኛዋ ትዕዛዝ መሰረት የካቲት 13/2007 ዓ.ም ባለመቅረባቸው ለሶስተኛ ጊዜ ለየካቲት 24/2007 ዓ.ም በፖሊስ ተይዘው ቀርበው እንዲመሰክሩ ታዟል፡፡

ባለስልጣናቱ በቀሩባቸው ቀጠሮዎች አቶ አስገደ ከትግራይ አውራጃዎችና ከአዲስ አበባ ድረስ ለመጡ ምስክሮች የትራንስፖርት ወጭ በመሸፈናቸው ከፍተኛ ኪሳራ ድርሶብኛል ብለዋል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ በተላለፈው ቀጠሮም ባለስልጣናቱ ላይመጡ ይችላሉ ያሉት አቶ አስግደ ‹‹በእነሱ ምክንያት ከፍተኛ ወጭ እያወጣሁ ነው፡፡ አሁንም ለሶስተኛ ወጭ ላወጣ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ አድርሰውብኛል፡፡›› ብለዋል፡፡

Previous Story

Hiber Radio: ወይንሸት “ከምርጫው ተወዳዳሪ ዕጩነት እኔን እጣ አልደረሰሽም ብለው አስወጥተውኛል” ማለቷ… እቴጌ ጣይቱ በታሪክ ሲታወሱ የሚኖሩ ታላቅ ሴት (ልዩ ጥንቅር).. አበበ ገላው የሀሰት ዲግሪ የሰበሰቡ የስርዓቱ ሰዎችን የተመለከተ ሰሞኑን አዲስ መረጃ እንደሚያቀርብ ገለፀ… አገዛዙ በኢትዮጵያ በሙስሊም ወጣቶች ላይ የከፈተው የእስር ዘመቻ የድል ዋዜማ ጠቋሚ ነው መባሉና ሌሎችም

Next Story

በደብረ ማርቆስ የሰማያዊ እጩ የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው

Go toTop