የቀለም አብዮት – አሁንገና ዓለማየሁ March 3, 2025 ግጥም Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የቀለም አብዮት ምንድነው ቢሏችሁ ጆርጂያ አዘርባጃን ዩክሬን ትላላችሁ? ወይስ ነጭ ዓለምን በኖራ ሸፍኖ ያፍሪካን ሥጋ ደም በሞራ አፍኖ በነበረበቱ በጨለማው ዘመን በተገመተበት ሰው በንብረት ተመን የኢትዮጵያ ጀግና ቀለሙን በጥብጦ ነጩን የብራና ገጽ በጦሩ ጫፍ ገልጦ በጥቁር ሲጽፈው ታሪክን ገልብጦ ታሪክን ገልብጦ ሲያኖር አዲስ ርዕዮት ያ ነው ትላላችሁ የቀለም አብዮት? ነው እንጂ! ጥቁር ሰው ምኒልክ አድዋ ተራሮች ላይ የነጭን ዝርያ በሾተል ሲያበራይ ጥቁር በነጭ ላይ ታላቅ ድል ሲመታ የደወለው ደወል የጮኸው እምቢልታ የነጻነት ድምጸት በዓለም ዙሪያ ሁሉ እስረኛን ቀስቅሶ ሰብሮ እንዲወጣ ጨቋኙን ደምስሶ በቀለም ጭቆና የታፈነን ሁሉ ከየታጎረበት ቀስቅሶ ደወሉ ታግሎ እንዲያሸንፍ አበርቺ የሆነው የቀለም አብዮት የአድዋው ጦርነት ነው! Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story እንደ ኦሮሙማ መንጋ እሽቅንድር ያደረገው የለም! Next Story ለመሆኑ የአደዋ መልዕክትና ዋና ዓላማውስ ምንድነው?