ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
እንዲህ ያቅነዘነዛቸው ለደግ እንዳልሆነ አውቃለሁና “ለደግ ያድርግላቸው” ብዬ ነገሬን ብጀምር ምፀት ይመስልብኛል፡፡ ስለሆነም መጨረሻቸውን በቶሎ እንዳይ ያብቃኝና እነዚህ ጉዶች እንደጉድ እሽቅንድር እንዳደረጋቸው በመጠቆም ለዛሬ መተንፈስ የፈለግሁትን ልተንፍስ፡፡ ሰዎቹ እጅግ ተቅበዝብዘዋል፤ አበቅቴያቸውም ከደጃቸው የደረሰ ይመስላል፡፡ ከእንግዲህ ግፋ ቢል ከአንድ ወቅት (season) የሚዘል ጊዜ ያላቸው አይመስሉም፡፡ ለቀብራቸው የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም፡፡ በነሱ ቤት ሰማይ ምድሩን ተቆጣጥረው የሚቃዡባትን የኦሮምያ ኢምፓየር ለማወጅ ጫፍ ደርሰዋል፡፡ ድንቄም ኦሮምያ፡፡ “ከሣሽ የተከሣሽን መልስ ቢያውቅ ኖሮ ከቤቱ ባልወጣ” ይባላል፡፡ በቅርቡ ልናይ ነው ኦነግ/ኦህዲድን ቅዘን በቅዘን የሚያደርገውን የመጨረሻውን ምዕራፍ፡፡
የመንጋ ዕብደት መጥፎ ነው ተብሎ ብቻ አይታለፍም፡፡ የመንጋን ዕብደት በእኔ ዕድሜ ለሁለተኛ ጊዜ ማየቴ ነው፡፡ እናም መጥፎ ብቻ ሣይሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ነፍሣትን የሚያስገብርና ለዘረኞች ጣዖታዊ የነገድ አምልኮ ጭዳ የሚያደርግ እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ቀዳሚው የመንጋ ዕብደት የሕወሓቱ ሲሆን ተከታዩ ደግሞ የወያኔን የዘር ፍጂት ጉድለቶች አሻሽሎና አጠናክሮ የመጣው የኦነግ መራሹ ብል.ግና ቡድን ነው፡፡ ለነገሩ ብል.ግና ፓርቲ የሚባል ከመነሻውም የለም፡፡ የአንድ ቁጭ በሉ በሻሻ ዱርዬ የግል መጫወቻ ስብስብ እንጂ የፓርቲ ሽታም ሆነ ወዝ የለውም፡፡ እንኳንስ ፓርቲው ሀገሪቷና 130 ሚሊዮኑ ሕዝብ የዚህ ወፈፌ ልጅ ጢባጢቤ መጫወቻ ሆነናል፡፡ ንግርት አይቀርም፤ እንዲያጥርና ጉዳቱ እንደዲቀንስ ግን በጸሎትና ምህላ ፈጣሪን መጠየቅ ይቻላል፡፡ አቢይ ራሱ ወዶና ፈቅዶ ልማራችሁ ቢል እንኳን አይችልም፤ ዕዝ ነዋ! አቢይ ያልታዘዘውን አያደርግም፥ ከታዘዘውም ድምቡሎ አያስቀርም፡፡ አእምሮ ያለውና ማሰብ የሚችል ደግሞ ለቅጣት አይላክም፡፡ … በነገራችን ላይ ይህንን ዘመን ታሪክ እንዴት እንደሚዘግበው አላውቅም፡፡
ጅምሬ የመንጋ ዕብደት ነው፡፡ እንስሳት በመንጋ አያብዱም፡፡ ሌሎች ፍጡራን ካሉም እነሱም በመንጋ አያብዱም፡፡ አንበሦች አንድን ሰው ወይ ሌላ እንስሳ ሊያጠቁ ሲከቡ አንዱ ወይ አንዷ እያግባባቻቸው ትገላግላለች፡፡ ነብሮች ድኩላዎችን ይምራሉ፡፡ እነዚህ ግን አሥር ሆነው አንድ አማራ ይገድሉና – መግደል ብቻውንም አያረካቸው ይልና ይቆራርጡታል ወይ ያቃጥሉታል ወይ በመኪና ይጎትቱታል ወይ ዘቅዝቀው ይሰቅሉታል – ሲያሣዝኑ፡፡ የሞተውማ አንዴውኑ ተገላግሏል፡፡ እናልህ ለዚህ አስቀያሚ ድርጊት የሚጋለጡት ሌሎች እነንሰስሳት ሣይሆኑ በሰው አምሣል ተፈጥረው ሲያበቁ ሰይጣን የሰረራቸው ሰብኣውያን የማኅበረሰብ ክፍሎች ናቸው – እንደሕወሓት መራሹ የተጋሩ ጽሉላትና እነንደኦህዲድ መራሹ የኦሮሙማ ዕብዶች፡፡ ዘረኝነት ላይ የተመረኮዘ ዕብደት ድምበር እንደሌለው የምንረዳው የዐድዋን በዓል አስመልክቶ ኦነጋውያን እያሣዩን ያለው ጉድ ታሪክ ራሱ ሲዘክረው የሚኖር ትንግርት መሆኑን በማስታወስ ጭምር ነው፡፡
ለይቶላቸዋል፡፡ ሰው እንዴት ከዐፅም ጋር ትግል ይገጥማል? ሰው እንዴት ሞቶ ከተቀበረ መቶ ምናምን ዓመታትን ካስቆጠረ አጥንት ጋር ይፋለማል? ምን ዓይነት ዶንኪሾተታወዊ ጅልነት ነው? አፄ ምኒልክ የደመቁበትን በዓል ለማክበር የሙሶሊኒን ከናቴራ እንልበስ? በአፄ ምኒልክ የዓድዋ ድል ዕለት የሣቸው ምሥል ያለበትን ከናቴራ መልበስ ወንጀል ሆኖ ወጣቶችና ጎልማሦች ሲታሰሩ ዋሉ፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ጥለት ቀሚሣቸውና ነጠላቸው ላይ የተገኘባቸው እህት-እናቶች ልብሣቸው በመቀስ ሲቦጨቅ ዋለ፡፡ የፊጂና የማልታን ባንዲራ ብትለብስ ግን አያዩህም፤ ያሜሪካንን ባንዴራ ጃኬትህ ላይ ብትደርብ ምናልባት ይሸልሙሃል፡፡ ምኒልክንና ንጹኋን የኢትዮጵያ ባንዲራ እያሣዬ ኦሮሞን የገረፈ ሰው ካለ ልጅ አይውጣለት፡፡ እነዚህን ሲያዩ እኮ ይጨልላሉ፡፡ ጨርቃቸውን ጥለው ነው የሚያብዱት፡፡ አማራንም ሲያዩ ይነዝራቸዋል፡፡ በዚህ መልክ አብረን እንኖራለን ብዬ ማመን ይቸግረኛል፡፡ ደግነቱ በቃሉ መሠረት እግዚአብሔር በቸርነቱ ያስተካክለዋል እንጂ እንደነዚህ “ሰዎች” ዕብደት ከሆነ የሀገራችን ሁኔታ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ከነዚህ ጉዶች ጋር ነው ወይ ለዘመናት እየተጋባንና እየተዋለድን በአንዲት ሀገር ውስጥ አብረን የኖርነው ለመሆኑ? የውጭ ሀገር ሰው መብቱ ተጠብቆለት ሲኖር አማሮች ግን ከውሻም ባነሰ treatment ነው በመኖርና ባለመኖር መካከል እየተሰቃየን ያለነው፡፡ ይሄ የዝቅተኝነት መንፈስ የሚፈጥረው ጥላቻ ለካንስ ከሰውነት ተራ የሚያወጣና ሃይማኖትንና ሞራልን የሚፍቅ አደገኛ መርዝ ነው፡፡ ለነሱም አዘንኩ፡፡