ከቴዎድሮስ ሐይሌ
“እርስ በእርሱ ስጋን በኩበት ጠበሱ” በሬው በእራሱ እዳሪ የእራሱን አካል ተጠብሶ መብልም ማገዶም ሆኖ ተበላ ይላል ሸዋ ሲተርት:: መለስ ዜናዊ ቀልድ ይሁን ቁም ነገር የሸዋ ተረትና የሱማሌ በጀት አድክሞና አለ ይባላል:: የሱማሌው በጀትን ጉዳይ አህመድ ሽዴ የመመርመር እድሉ ስላለው ለሱ ሰጥተን የሸዋ ተረት ግን ግቡን የሚመታ የሚያነቃና ከሺ ገጽ ጥራዝ መጽሃፍ ይልቅ በአንድ መስመር የሁኔታዎችን መነሻና መዳረሻ በግልጽ አስቀምጦ ያስተምራል ያስጠነቅቃል ያነቃል::
ሰሞኑን የምንሰማውን አሰቃቂና አደገኛ ሁኔታ የየዋሁን በሬ አይነት ሆኖብኛል:: ለአንድ አላማ ; ለአንድ ሕዝብ ; ለአንድ የጋራ ግብ ; የተሰለፉ የፉኖ ሃይሎች አንዱ ሌላው ላይ እርምጃ ለመውሰድ መሞከሩን ሰምተናል:: ጉዳት መድረሱም ተዘግቧል:: የደም ነጋዴዎች ; ተረፈ በአዴኖችና ; የብልጽግና ተከፉዮች ; ታጋይ መሳይ ባንዳዎች ; በሰሜን አሜሪካና በኡጋንዳ ከትመው “በአንድ ቀጥና አንድ አደረጃጀት ከዛ ውጭ ያለውን በሃይል ማስወገድ ” የሚል ግዙፍ የጥፉት መፈክራቸውን በአደባባይ ካሳወቁን ሳምንት ሳይቆይ ይሄ የወንድማማቾች የእርስ በእርስ ግጭት መከሰቱ ስምሪት ሰጭው አካልና ተልዕኮው የሚያቀናብረው ቡድን መሬት የረገጠ እና መናከስ የሚችል ጥርስ ማብቀሉን ያሳየናል::
የብሄር ፖለቲካ አስቀያም ባህሪው በሩ ለሁሉም ክፍት መሆኑ ነው:: አዋቂውም ደንቆሮውም ጋለሞታውም አውደልዳዩም ለመታደም ከልካይ የለውም:: በማንኛውም ጉዳይ እንደፈለገ ሲዘባርቅ አይሸማቀቅም::አሁን አሁንማ ብዙ አወቁ የሚባሉት ምሁራን ጭምር የዚህ ጀብራሬ መንጋ ምርኮኛ ሆነዋል:: ድንቁርና የከፉ ጭለማ ነው:: አላዋቂው መንጋ ልጏም ሊብጅለት አለመቻሉ መከራችንን እጅግ አክብዶታል:: በ70ዎቹ የርዕዮተ ዓለም ጎራ ለይቶ ተተራምሶ ያለቀው ያ ትውልድ እንደዛሬው ፖለቲካ ሳይሆን የሚያነብ የሚተነትን የሚጽፍ ሃገራዊና አለም አቀፉዊ እውቀትና ንባብ ያለው ለገረዶችና ለቀላዋጭ ጎልማሳ ፖለቲከኛ ነን ባዮች የማይመች አዋቂዎችን ብቻ የሚያሳትፍ የፖለቲካ አውድ ነበር:: ዛሬ ላይ ማንበብ ብርድ ብርድ የሚለው የፖለቲካን ትንተና ማሰብ የማይችለው ወሬ ቧልትን አሉባልታን እንደ ትግል የሚቆጥር ነው ያለው:: አለኝ ለሚለው መረጃ ምንጭ ጥቀስ ብትለው መጽሃፍትን የሚጠራ ባለሙያን የሚያማክር ወይም ባለጉዳዮቹን አናግሮ ምላሽ የሚሰጥ ሳይሆን በየጏዳው ከፈሉት ትቦዎች (YouTube) የሱ ብጤ አንዱን በምንጭነት ሲጠቅስልህ በኩራት ነው:: ትግሉ አደጋ ውስጥ ወድቋል ሲባል ዝም ብሎ አይደለም:: እውነታው ይህንን ስለሚመስል ነው:: በጣም የሚያሳዝንና ተስፉችንን የሚያጨልመው የፉኖ መሪዎች ጭምር የዚህ ድንቁርና ያጠቃው ቅጠረኛ ሃሳብ ተጋሪ መሆናቸው ነው:: የጥላቻው ድቤ የእርስ በእርስ የማጋደያው አዋጅ ፊሽካው ከተነፉ ሳምንት ሳይሞላው በሁለት ቅርብ ወንድማማቾች መካከል ጦርነት መከፈቱ የአማራ ሕዝብ የገጠመው ፈተና አንዱ ማሳያ ነው::ይህ በአጭሩ ካልተቀጨ የፉኖ ትግል መዳረሻው የእርስ በእርስ እልቂት ለመሆኑ ሌላ ማስረጃ አያስፈልግም::
የወገኑ ሰቆቃ ውስጥ መውደቅ የሚያሳስበው ምንም አይነት ሌላ ፍላጎት የሌለው ሰው በምንም መልኩ የወንድማማቾችን መጋደል አይፈልግም:: ለጋራ አላማ በተለያየ እደረጃጀት ያሉ ሃይሎች ማታኮስ የጠላት ዓላማና ፍላጎት እንጂ በምንም መመዘኛ ከወገን የሚጠበቅ አይደለም::;
የፉኖ ተፈጥሮ እጅግ የተለየ ነው:: አደረጃጀቱ በብዙ መቶዎች ተበትኖ ከየወረዳና ሠፍሩ በጎብዝ አለቃ እየተሰባሰበና ከታች ወደ እላይ እየተደራጀ የመጣ ነው:: ይሄ የተበታተነ የፉኖ አደረጃጀት በአጭር ግዜ ውስጥ በጣት ወደሚቆጠሩ ተቋማት ተሰብስቧል:: ወደ አንድ አማራዊ ተቋም ለመምጣት እየተደረገ ያለው ጥረት የተሟላ ባይሆንም ቀላል የማይባሉ ቡድኖች ወደ ጋራ ትግል ተሰባስበዋል:: ወደ አንድ ላይ ለማሰባሰብ በጎ ተጽዕኖ መፍጠር የልሂቃኑም የደጀን ሕዝቡም ያንቂውም የሚድያ ባለሙያውም የተቀናጀ ጥረትን ይጠይቃል:: በፉኖዎች መካከል ይህ ነው የሚባል የተጨበጠ እርዕዮተ ዓለማዊ ይሁን የአላም ልዩነት የለም:: በእንደዚህ አይነት ተመሳሳይ አቋም ውስጥ ያለን ሃይል ለምን እንዲለያይ ስራዬ ተብሎ ይዘመታል:: እንዴትስ እንዲጋደሉ በምቹ ሃገርና ሁኔታ ላይ ተቀምጦ የመጠፉፉት አቅጣጫ ይጠቆማል:: ይህ የጠላትን አላማ ካልሆነ የአማራን ሕዝብ አይጠቅምም:: እውነታው ይታወቅ ትግሉ ተጠልፏል::
አውሬው አብይ አህመድ ሾርት ሚሞሪ ብሎ ያላገጠብን ያለ ምክንያት አይደለም:: እይታችን የእለቱን ; አስተውሎታችን በአሉባልታ አቀባዮቻችን ትቦዎች (Youtube) በመጋረዱ ስንዴውን ከእንክርዳድ መለየት ተስኖናል:: ያ ባይሆን በትግል ስም የተካሄደብንን ክህደት ግምት ውስጥ ያስገባ ለመሪዎችና ለታጋዮች የሚኖረን ክብርና እይታ ዛሬ ላይ የሚታየው ባልሆነ ነበር:: በትግል ታሪካቸው ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉ ጥቅም ስልጣንና ምቾት ከመስመራቸው ያላስወጣቸውን ጀግኖች ዛሬ የማንም ምናምንቴ ሲስድባቸው ብሎም እንዲገደሉ በአደባባይ ሲያውጁ ዝም ባልተባለ ነበር:: አማራ በዚህ አካሄዱ አስቀድሞ የመታው እንቅፉት ደግሞ እንዲያደናቅፈው ካልፈለገ በስተቀር በስሙ የሚነግዱትን ማስቆም አለበት::
ትላንት የሆነው ይህው ነበር:: በለጠ ሞላና ጋሻው መርሻ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ትንታግ መሪዎች አማራን ሸጠው አራጆች ጫማ ስር ይውላሉ ብሎ ማን ጠበቀ::እንደ ጣሂር መሃመድ አንደበት ርዕቱ የአማራ ጠበቃ ባንዳ ይሆናል ብሎ ማንስ ገመተ የእኛ ናቸው ስንል ለተራ ስልጣንና ጥቅም ትግሉንም ሕዝቡንም ሸጠው ተንበረከኩ:: ዛሬም የጣሂር የክህደት መንፈስ የጋሻው መርሻ ባርነት የበለጠ ሞላ ተንበርካኪነት በፉኖ ትግል ውስጥ አይደገምም ብሎ መዘናጋት አያስፈልግም::
የብልጽግና ድሮን ታንክና መድፉ ሮኬትና ሚሳኤሉ በገፍ እየተጫነ የሚገባው ሠራዊቱ ምንም ያስገኘው ውጤት የለም:: ሰራዊቱ በከፊል ሲማረክ የቀረው ሲደመሰስ እድል የቀናው ጠመንጃውን ትቶ ሲኮበልል በዚ ሁለት አመት እስተውለናል:: ይህ ወታደራዊ ጋጋታ የሚፈለገውን ውጤት እንደማያመጣ ገዥዎቹ ሰፈር ታምኗል:: ይሄ በገንዘብ ደረጃም በቢሊዮን ዶላር የገባበት ጦርነት ለአንድ የድሮን ቅንቡላ 50 ሺ ዶላር በማውጣት የሚያደርገው ጦርነት 50 ሺውን ለአስር ሰዎች በመመደብ በሶሻል ሚድያ አክታቲቪስትነት በጋዜጠኛነት አማራ ነን በሚሉ የፕሮቴስታንት ጅሃዲስቶች በተቀናጀ ሁኔታ ፉኖን በመከፉፈል እርስ በእርስ ለማጫረስ የወጣው እቅድ የሰሞኑ ሁኔታ አንዱ ማሳያ ነው::
ውጤታማ ሃይል ቆጣቢ በአጭር ግዜ ፉኖን ለመበተን በሬው ስጋው በኩበቱ እንደተጠበሰው አማራውም ትጥቁን አይደለም ሙታንታውን ማስወለቅ የምንችለው እርስ በዕርሱ ስናጋጨው ነው የሚል እቅድ አውጥተው ወደ ትግበራ ተሰማርተዋል:: እስኪ ጎበዝ አንድ አፍታ ቆም ብለን አማራ ነን የሚሉ የሶሻል ሚድያ ገጾችን እንመልከት:: የዩቱብ ልሳኖችን እናዳምጥ ሰው በላው አብይ አህመድ ተረስቷል:: ስድቡ እርግማኑ ማንቋሸሹ አልፎም ተርፎም በቀጠናህ ካንተ ያልሆነውን ግደል የሚል አዋጅ የሚነገረው ወንድማማች ፉኖዎችን ለማጫረስ ነው:: አብይ አህመድ ከተሳካለት ሽመልስ አብዲሳን ባህርዳር ላይ ልኮ የቁማሩን ቀመር ሱሪ ያሶለቀበትን ሚስጥር እስኪያስረዳ የሚጠብቅ ብቻ ነው ይህንን የትግል ቅልበሳ ሴራ ዝም ብሎ የሚያየው::
በአርበኛ ምሬ አዝማችነት በኮሎኔል ፉንታሁን ሙሃቤ ላይ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ መሞከሩ በማንኛውም መመዘኛ ለአማራ ትግል አይጠቅምም:: ከዚህ በላይ ኮሎኔል ፉንታሁን ማለት ጀነራል አሳምነው በአካልም በአምሳልም በአቋምም በጽናትም አምሳያው የትግል ጏዱ የእስር ዘመን ሰቆቃው ተጋሪ ኮሎኔል ፉንታሁን ሙሃቤ ነው:: ሰማዕቱ አሳምነውና አርበኛው ፉንታሁን ለተገፉው የአማራ ሕዝብ በመቆማቸው የተሳደዱ ከምቾትና ተድላ ይልቅ ስለወገናቸው የተጎሳቆሉ ሁለት ሰዎች አንዱ ለወገኑ ሲል የተሰዋ ሰማዕት : ሌላው የጏዱን አርማ አንስቶ በዱር በገደል በማምሻ እድሜው የሚማስን ታጋይ:: የዚህ ጀግና የትግል ተምሳሌት የጦር ኤክስፐርት ከዛም በላይ በእድሜው መከበር ያለበት አውራ ላይ ቃታ አይሳብበትም:: አማራ ጀግናን ያከብራል በተለይ ወሎ ለአንጋፉዎቹ ያለው አያያዝ ልዩ ነው:: ታዲያ ምን በድሎ? ምንስ አጉድሎ? የትኛውንስ ጥፉት ፈጽሞ ነው? ሞት የታወጀበት:: ከጋለሞታ አጫዋቾቹ የአብይ ጀነራል ተብዬዎች በብቃቱም በእውቀቱም የላቀ ወታደር አሉባልተኞች እንደሚሉት በዲያስፖራ ዶላር ተገዝቶ?:: ለዚህ ለዚህ ብልጽግናን ቢቀላቀል ዶላሩም ቪላውም ልጃገረዱንም ቅጦትና ድሎቱንም እንደልብ ያገኘው አልነበር:: በዱር በገደል እንዲያ ተጎሳቁሎ የሚዋትተው ለአማራ ሕዝብ መብትና ነጻነት ብሎ ነው:: ኮሎኔሉ ሊሞት ነው የወጣው:: ለሱ ሞት ብርቁ አይደለም:: የሚያሳዝነው ግን ጏዱ ጀነራል አሳምነው የተጠቆመው የተገደለው በአብይ ተላላኪ ሆዳም አማሮች ነው:: ኮሎኔን ፉንታሁን ሊያመው ቢችል እንደ ትግል ጏዱ እንደ ወንድሙ አሳምነው ጽጌ አማራ በሆነ ያውም አርበኛ ነኝ በሚል ታጋይ ስም ክህደት የተፈጸመበት መሆኑ ነው:;
በታሪክ አጋጣሚ የፉኖ መሪ ለመሆን የቻሉ ወንድሞቻችን ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል:: ጠመንጃ ማንገብ ኢላምን አንጣጥሮ መምታት የተሟላ ወታደራዊ ቁመናን አያቀዳጅም:: የአያቶቻችን ልጆች ነን ይሄ ከቤተሰብ የወረስንው እሴት ነው::አባቶቻችን ከእኛ የሚለዩት ጠላትን በመቀነስ ወዳጅን በማብዛት ነው:: የአዋቂን ምክር የታላላቆችን አስተያየት የጀግኖችን ሃሳብ ማድመጥ ውጊያንም ሆነ እርቅን ለመፈጸም አስቀድመው የሚዘጋጁበት በሳል እሴት አላቸው:: ውትርድና ሙያ ነው:: ጦርነት ሳይንስ ነው:: ወታደራዊ እውቀት በቀላል ኪሳራ ብዙ ድል የሚገኝበትን መንገድ ነው::
ዘመኑን የዋጀ ወታደራዊ ስነልቦና ባህልና ዝግጅት የግድ ነው:: በታሪክ አጋጣሚ የሕልውና ትግሉ አስገድዶት ጠመንጃ የጨበጠ ሁሉ አወቂ ነኝ የሚልበትን የሽፍታ ስነልቦና በሕዝባዊ ሃላፊነት ልናርቀው ይገባል:: ፉኖ የሕዝብ ልጅ ነው:: ይህንን ደግሞ ባለፉት ሁለት አመታት አስመስክሯል:: በታሪክ አጋጣሚ ሕዝብ የሰጠንን ሃላፊነት እና ክብር በተገቢው ደረጃ የመጠበቅ ግዴታ እንዳለብን መዘንጋት የለበትም:: በሕዝባዊ ትግል ውስጥ ወደ ሃላፊነት ወደ ጦር አዛዥነት እና ወደ መሪነት የሚመጡ ግለሰቦች ክራይቴሪያ ወጥቶ ልምድና ችሎታቸው ተመዝኖ ሳይሆን በአጋጣሚ ሁኔታ ነው:: እንደምሳሌም በወሎ ቀጠና ወታደራዊ ሊቁና መስመራዊው መኮንኑ ኮሎኔክ ፉንታሁን ሙሃቤ እና በሌላ ጉኑ የምስራቅ አማራው የፉኖ መሪ ከሸቀጣ ሸቀጥ ንግዱ ወጥቶ የትግሉ መሪ ለመሆን የቻለው::
በወታደርነት ያገለገለ እንደ አንድ የበታች ሹም ምክር ልሰጥ እወዳለሁ:: ወታደራዊ ክህሎት ብቻውን ሕዝባዊነት ካልታከለበት መፍትሄ አይሆንም:: አርበኝነት እና ሕዝባዊነትም ብስለትና አስተውሎት ከሌለበት ለውጤት አይበቃም:: በኮሎኔል ፉንታሁንና በአርበኛ ምሬ መካከል ሽምግልና በተደጋጋሚ ግዜ ተካሂዷል:: እንዳውም እርቁ ሰምሮ አርበኛ ምሬ በዋና አዛዥነት ኮሎኔል ፉንታሁን በምክትልነት አብሮ ለመስራት ስምምነት ተደርሶ ነበር:: በዛ ስምምነት የአርበኛ ምሬን አብሮ ለመስራት ያሳየው ዝግጁነት:: የኮሎኔል ፉንታሁን ችሎታ ልምድና እውቀቱን ለድርድር ሳያስቀምጥ ምክትልነት መቀበሉ ቅንነቱን እና በጋራ ለመታገል ያለውን ፍላጎት ያሳየ ነበር:: ያ ጠላትን ያስጨነቀ ወገንን ያኮራ የደም ነጋዴ ባንዳዎችን ለክፉት ያነሳሳ መልካም ጅማሮ ብዙም ሳይራመድ ጨንግፎ ይኽው አንዱ በሌላው ላይ ቃታ የሳበበት ሁኔታ ላይ ተደረሰ:: የብልጽግና ካምፕ የብአዴን ጎራ የደም ነጋዴው መንደር የበለጠ እሳቱን ለማቀጣጠል በየአቅጣጫው ተሰማራ:: አማራ ነኝ የሚል ይህንን ነውር ያስቁም እደባባይ ወጥቶ ያውግዝ:: በየጏዳው እየተልከሰከሱ የሚያቃጥሩ የደም ነጋዴ ቅጥረኞችን ያግልል እንደ በሬው በእራስህ ገንዘብ የኔ ናቸው በምትላቸው ሰዎች እንዳትሸጥ ተጠንቀቅ::
በመጨረሻም አርበኛ ምሬ ለትግሉ ባለህ ቀናይነት አድናቂዎችህ ነን:: ግን ወታደራዊ ስትራቴጂ ፖለቲካዊ ንድፈሃሳብ የማዘጋጀት ብቃቱና እውቀቱ እንደሌለህ እናውቃለን:: ያለህን ይዘህ መቅረብ ብቻ ከበቂ በላይ ነው:: ወታደራዊ እቅድና ፖለቲካዊ ትንተና አንተ እንደምታውቀው የሸቀጥ ንግድ እንደ ጨውና ዱቄት ተመዝኖ የሚሰፈር አይደለም :: ብዙ ንባብ ሰፊ ተሞክሮና ተጨባጭ በልምድ የታገዘ እውቀትን የሚጠይቅ ነው:: በሶሻል ሚድያ እያሾፉ ወደ ጥፉት ከሚመሩህ ገረዶች ይልቅ አጠገብህ ያሉትን ቅረብ:: ከደም ነጋዴ የፕሮቴስታንት ጅሃዲስት አማካሪህ ነን ከሚሉ የሰዶም ፈረሶች ይልቅ ወታደራዊ ኤክስፐርቱን ኮሎኔል ፉንታሁን የበለጠ ይጠቅምሃል:: እነ ጌታ አስራደ ጉድለትህን የመሙላት ምሁራዊ አቅም አላቸው:: እነ አርበኛ ዘመነን ጠይቅ ያግዙሃል እጅግ ካንተ እርቀው በአንድ ቀጠና አንድ አደረጃጀት ከሚሉህ የብአዴን ተላላኪ ገረዶች እራስህ አርቅ::አሜርካ የሚኖር ሁሉን የሚያውቅ ኑሮ የሞላለትና ለወገኑ የሚቆረቆር ከመሰለህ ተሳስተሃል:: በሕይወት ዘመናቸው ስራ ሰርተው የማያውቁ ፖለቲካን መነገጃ አድርገው በቅልውጥና እና በምጽዋት የሚኖሩ ለከፈላችቸው ቀሚሳቸውን የሚያወልቁ ጋለሞቶችና የሚንበረከኩ ጎልማሶች በሽ ናቸው:: እድል ከሰጠሃቸው አንተንም ይሸጡሃል:: ብልጽግና ደግሞ ቁማር ቆምሮ መሪዎችን ሲያጠፉና ፍርፉሪ ሰጥቶ ሙሉ ድርጅትን የማስገበር በቂ ልምድ አጎልብቷል :: ዛሬም በጋዜጠኝነት በአክቲቪስትነት በወንጌል አገልጋይነት ስም የተሰማሩ በርካታ በወገናችው መቃብር ላይ ኑሮአቸውን ሊያደላድሉ የተነሱ አውሬዎችን አሰማርቶብናል:: ይህንን አውቀንና ተጠንቅቀን በአስተውሎት ልንጏዝ ይገባል::
ፈጣሪ ማስተዋሉን ያድለን!!!
ህዝብ ዋስትናዎች :-