ፃነት ዘገዬ
አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪና ፋሶ የታደለች ናት፡፡ የተሰጣት መሪ ሀገሪቱን ከአፍሪካ ነቅሎ ወደ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ እየወሰዳት ነው፡፡ መሪው በጣም ልጅ እግር ነው፡፡ ሀገሩን ይወዳል፡፡ ስለሀገሩ ሌት ከቀን ይጨነቃል፡፡ ዛሬ ስለዚህ ሀገር ወዳድ መሪ የሰማሁት ደግሞ በመንፈሣዊ ቅናት ኅሊናን በሃሤት ይሞላል፤ በሱ ስደሰት የኛው ደደብ ፊቴ ላይ ድቅን እያለ አልቅስ አልቅስ ይለኛል – ግን ዕንባ አለቀና ከየት ይምጣ? እንዲህ ነው መታደል፡፡ እግዚአብሔር ሲክስ እንደዚህ ነው፡፡ የልጅ ዐዋቂ መሪ ሰጣቸውና ይሄውና ትንሣኤያቸው ፍሬ ማፍራት ጀምሯል – አትሩጥ አንጋጥ ነው፡፡ “የሀገሬ ሕዝብ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይታረዝምም” ብሎ በግብርናውና በኢንዱስትሪው ከሚያደርገው ጥረት በተጨማሪ ቡርኪና ፋሶ ውስጥ ቤት የሌለው ዜጋ እንዳይኖር ዐዋጅ አፅድቆ ቤት ለሌላቸው መንግሥት በነፃ ቤት ሠርቶ ሊሰጥ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና ይስጠው፡፡ ሰይጣንንም ከአጠገቡ ያርቅለት፡፡
 ወደኛው ጉድ ስንመጣ ”ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” እንደምንለው ቤት ሠርቶ መስጠቱ ቀርቶብን በላብ በወዛችን የሠራነውን ቤት ማፍረሱንና ወደጎዳና መጣሉን በተወን፡፡ የፈጣሪ ሥራ ግን ግርም ይላል፡፡ ለሕዝቡ የሚጨነቅ ኢብራሂም ትራኦሬን የመሰለ ግሩም ሰው በፈጠረባት ምድር በቀን አንዴ መቅመስ ከሚያቅታቸው ምሥኪን ዜጎቹ እየዘረፈ ለራሱ ትሪሊዮኖችን የሚፈጅ ቅንጡ ቤተ መንግሥትና መናፈሻዎችን የሚሠራና ድሃውን ከመኖሪያ ሥፍራውና ከሠራው ቤት የሚያፈናቅል የሥነ ልቦና ህሙም (psychopath) ላከብን፡፡ በዚህም ሳያበቃ የኦሮሞ ኢምፓየር የምትባል የቅዠት ሀገር ለመመሥረት ሲል ኢትዮጵያን በማፈራረስ ላይ ይገኛል – ሊያውም ራሱ ኦሮሞ ሳይሆን፡፡ በቡርኪና ፋሶ አንድ ጀግና ተወልዶ ሀገሩን እየገነባ ሳለ የኛው የአጋንንት ውላጅ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ጦር በየክልሉ እንደጫጩት ፈልፍሎ እርስ በርስ እያፋጀ ይገኛል፡፡ ያደለው ዜጎችን አስተምሮና አሠልጥኖ ለሥራና ለልማት ያሠማራል – እሱ ግን ሀገሪቱ ሌት ተቀን በጦርና በጦረኞች እንድትታመስ ሁኔታዎችን ሁሉ ያመቻቻል፡፡ ትልቅ መረገም ነው – ለኛም ለሱም፡፡ ይህ ቀልማዳ ውሸታም በቅርቡ ባደረገው የተሰለቸ ውሽከታው “ጅማ ውስጥ ከ15 ሺህ የማያንሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ቤታቸውን ያለካሣና ያለምትክ ለኮሪደር ልማት ሰጡ” ብሎ በተቀደደ ማግሥት የገዛ “አክስቱ” (የእንጀራ አባቱ እህት ላለማለት ነው) ሦስት ጎረቤቶቿ “ቤታቸው በመፍረሱ ምክንያት ራሳቸውን ሰቀሉ” ብላ በአደባባይ እንደነገረችውና እሱም በተናገረችው ነገር አፍሮ እንደተቆጣት ሰማን፡፡ ይህን የመሰለ ጭራቅ ለኢትዮጵያውያን ሰጥቶ ትራኦሬን የመሰለ መልዓክ ለቡርኪና ፋሶ ሰጠ፡፡ ለምን ሰጠ አልልም፤ እኛን ግን ለዚህ ዓይነቱ ዐረመኔ ደም መጣጭ አጋልጦ መቅረቱ እጅግ ያበሳጫል፡፡ ይህ አቢይ እያለ ደግሞ ኢትዮጵያ መቀመቅ መውረዷ በስፋትና በጥልቀት መቀጠሉ አይቀርም፡፡ የት እንሂድለት? ድሃ አደግ ሰው ወደ ሥልጣን ማማ አይድረስ፤ በበታችነት ኮምፕሌክስ የታጨቀ በመሆኑ ከራሱ ውጪ ሌሎችን የሚሰማበት ጆሮ የለውም፡፡ ኢንሳ ውስጥ እያለ ለጓደኞቹ “ድህነትን እንዴት አድርጌ እንደምጫወትበት አሳያችኋለሁ” እያለ በድህነት ላይ ሲዝት እንደነበር ከሁነኛ ሰው ሰምቻለሁ፡፡ ድህነትን ይጫወትበት – ግዴለም፡፡ በድሆች ላይ መጫወትና የሰው ደም አፍስሶ የሰው ሥጋም በልቶ አለመጥገብ ግን መድሓኒት የሌለው በሽታ ነው፡፡ የዚህን መሰሉ “ሰው” ኢትዮጵያ ውስጥ መፈጠሩ ደግሞ ከሁሉም የበለጠ ዕንቆቅልሽ ሆኖብኝ ዘወትር እጨነቃለሁ – መልስ-አልባ ዕንቆቅልሽ፡፡ በአክሊሉ ሀ/ወልድ አገር አብዮት አህመድ ይፈጠር? በጎሹ ወልዴ አገር ይህ ወፈፌ ተፈጥሮ ቤተ መንግሥቱን ይቆጣጠር? እርግማን ግን ለከት ወይም ወሰን የለውም እንዴ? ኧረ ግዴላችሁም ተያይዘን ሳናብድ ተያይዘን ወደፈጣሪ እንጩህ!! የሰውም ዝምታ ራሱ እኮ የሚያሳብድ ነው፡፡ የሚስቅ ሰው የሚያስቀናበት ጊዜ ላይ ደረስን፡፡