
አፋብሃ የአማራ ፋኖ ብጄራዊ ኃይል ተመስርቶ ይፋ ከተደረገ ሶስት ሳምንት ሆነው፡፡ ከ80% በላይ ፋኖዎችን ያቀፈው ይህ ትልቅ ድርጅት፣ እንዳይመሰረት ከፍተኛ ፈተናዎች ነበሩ፡፡ ከብዙ ትላልቅ አውደውጊያዎች የተገኝዑ ድሎች ቢደመሩ፣ ይህንን ድርጅት በመመስረት የተገኘው ድል ይበልጣል፡፡
ይህንንም የምለው በምክንያት ነው፡፡ ብዙ ወታደራዊ ድሎች ቢገኙም፣ ብዙዎቹ ወይም ሁሉም በሚባል መልኩ፣ ስትራቴጂክ ድሎች አልነበሩም፡፡ ታክቲካል ድሎች እንጂ፡፡ ስትራቴጂክ ድል ጦርነቱ እንዲቋጭ የሚያደርግ፣ ወሳኝና ጨዋታ ቀያሪ ድል ነው፡፡ ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ ነው፡፡ ታክቲካ ድል ከስትራቴጂክ ድል የሚለው፣ ጊዚያዊ መሆኑ ነው፡፡ ወደ ስትራቲጂክ ድል የሚወስድ ድል ነው፡፡ የአፋብሃ መዓከላዊ ኮማንድ አባል ጠበቃ ፋኖ አስረስ ማረ፣ የችርቻሮ ድል ያላቸው ማለት ነው፡፡
የአፋብሃ መመስረት ታክቲካል ድሎች ወደ ስትራቲጂክ ድሎች እንዲሸጋገሩ ወሳኝ ብቻ ሳይሆን ቁልፍ ሚና የሚጫወት ነው፡፡ ለዚህም ነው ከብዙ ታክቲካል ወታደራዊ ድሎች፣ ወደ ስትራቲጂክ ድል የሚወስደው የዚህ ድርጅት መመስረት ትልቅ ድል ነው የምለው፡፡
ይህ ድርጅት እንዳይመሰረት፣ አገዛዙ እጅግ በጣም ብዙ ጥረት አድርጓል፡፡ ቢሊዮን ብሮች አፍሷል፡፡ በገንዘብ የገዛቸውን ደካማ ሰርጎ ገቦችን አስገብቶ በፋኖዎች መካከል አለመግባባትና መከፋፈል እንዲኖር አድርጓል፡፡ የስልክ ንግግሮችን እየጠለፈ፣ ቆራርጦና መርጦ በማውጣት አለመተማመን እንዲኖር ለማድረግ ሞክሯል፡፡ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም፡፡
የፋኖ መሪዎች ያንን ሁሉ አልፈው፣ በቋራ የአንድነቱን ስነድ ለመፈርም ተገኝተው በነበረበት ወቅትም፣ ተበተኑ፣ ተጣሉ ወዘተ የተባለ ስንት ጩኸት ስንሰማ ነበር፡፡ እንደ ያሬድ ሙሉነህ፣ አዶናይ አባበ፣ ካሳሁን ነገረ አማራ ያሉ የ እስክንድር ጉጅሌ ካድሬዎች፣ እንደ ጌትነት ይስማው፣ አያሌው መንበር ያሉ፣ ጸረ ጎጃም ኃይሎችም ስንት ጉድ ሲጽፉና ሲናገሩ እንደነበረም ተመዝግቧል፡፡
ህወሃት በብዴኖች በኩል ስልጣናቸውን አስቀጥለው የነበረው፣ በዋናነት በአማራ ክልል እርስ በርስ በማናከስ ነበር፡፡ በተለይም በጎንደርና በጎጃም ወገኖች መካከል የእርስ በርስ ፉክክር፣ ጠብ አለመተማመን እንዲኖር በማድረግ ነበር፡፡ የኦሮሞ ብልጽግናዎችም ያንን ነው ሲይደርጉ የነበረው፡፡ የጎንደር ፋኖዎች፣ ከጎጃም ፋኖዎች ጋር ፣ በውሽት፣ ለመከፋፈል ሞክረዋል፡፡ የጎጃም ወጣቶች፣ ስለ ወልቃይት ሲሉ በጥይት መርገፋቸው ተረስቶ፣ የጎጃም ፋኖዎች ፣ ህወሃት ጎጃም ባትገባም፣ ወደ ወሎ በመዝለቅ፣ ከህወሃት ጋር በተደረገው ውጊያ የከፈሉት ስንት መስዋእትነት ተረስቶ፣ የብልጽግናን ውሸት ተቀብለው፣ ጸረ ጎጃም ፕሮፖጋንዳ በመንዛት፣ አንድነቱ እውነት እንዳይሆን ብዙ ተሞክሯል፡፡
ሆኖ ያንን ሁሉ በማሸነፍ ፣ አፋብሃ ተመስርቷል፡፡ በዚህ የህዝብ፣ የፋኖ ጠላቶች ተበሳጭተዋል፡፡
የፋኖ መሪዎች በአካል ተገናኝተው፣ ድርጅቱን ሲመሰርቱ፣ ተከራክረዋል፣ ተጨቃጭቀዋል፡፡ ቀላል አልነበረም፡፡ ከበስተጀርና የተለያዩ እጆቻቸውን የዘረጉ ነበሩ፣ ከመጡበት አካባቢ የተነሳ ፕራዮሪቲያቸው ሊለያይ ይችላል፡፡ የባህሪ ጉዳይ አለ፡፡ በየቲክቶኩ ምድረ ደንቆረና ያልበሰለ አፋን ሲከፍት መዋሉ፣ ምን አለፋችሁ ሂደቱ ከባድ ነበር፡፡
ድርጅቱ ሲመሰረት፣
አንደኛ ተጀመረ እንጂ አላለቀም፡፡ በዚህ በሶስት ሳምንታት ውስጥ ራኡ ብዙ የተሰሩ ስራዎች አሉ፡፡ የውስጥም የውጭም ስራዎች፡፡ እንደ ምሳሌ ብጠቅስ፣ ለፋኖ የቆሙ ሜድያዎችን በአንድ ቅኝት፣ ትግሉን ባገዘ መልኩ በፉክክር ሳይሆን በትብብር እንዲሰሩ፣ በመረጃ ቲቪ አመቻችነት የተደረገው ፎረም ቀላል ትልቅ ስራ ነው፡፡
ሁለተኛ በጥንቃቄ መጓዝ ካልተቻለ፣ የኮማንዱ አመራሮች ሃላፊነታቸውን ካልተወጡ፣ በተለይም አፍራሽ ሚና እየተጫወቱ ካሉ እንደ ዘመድኩን በቀለ ካሉ ጋር፣ ያላቸውን ግንኙነት በልክና ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ካላደረጉ፣ ብዙ ተደክሞበት የተገኘውን ድል ሊያበላሹት ይችላሉ፡፡ስለዚህ ይህን ድርጅት እንዲጠናከር የማድረግ ፣ የመጠበቅ ሃላፊነት አለባቸው፡፡ የተቀረነውም ይህ ድርጅት የሁላችንም እንደመሆኑ ድርጅቱ ከወሬኞች መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡
ከ13 የአፋብሃ ማዕከላዊ ኮማን አባል መካከል የአፋብሃ የጎጃም ቀጠና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ከጋዜጠና መልካም ሞላ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስም ይህንን ነው ያሳሰበው፡፡ ሻለቃ ዝናቡ፣ አሁን አብይ አህመድ አኝኮ ሲተፋቸው መሄጃ ላጡ፣ ስራፈት ብአዴኖች እቅጩን ነግሯቸዋል፡፡ ” የአማራን ሕዝብ በየትኛውም ጊዜ ያስጨፈጨፉ፤ የአማራን ሕዝብ ግድያ ያስተባበሩ ፤ መዋቅራዊ ጭቆና ሲፈፀምበት አስተዋፅኦ የነበራቸው እና የአማራ ሕዝብን እንዲመሩ እድል ተሰጥቷቸው እድሜያቸውንም መልካም አጋጣሚዎችን ያባከኑ ሰዎች በአማራ ፋኖ ትግል ተንጠላጥለው መሪ ካልሆንን ይላሉ፤ የዚህ ትግል ባለቤት ካልሆንን ይላሉ የዚህ ትግል ባለቤት ግን አዲሱ ትውልድ ነው” ሲል ነው የተናገረው፡፡
እነዚህ ግለሰቦች ከድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ፣ አፋብኃ፣ የአፋብኃ ደጋፊዎች እውነቱን አውቀው ከነዚህ ሰዎች እንዲጠነቀቁ ጠይቋል፡፡ አፋብሃ በጥንቃቄ፣ በሰከነ መልኩ አሁን እያደረገ ያለው እየሰራ እንደሚቀጥል የገለጸው ሻለቃ ዝናቡ፣ ወደ ኋላ ከተባለ፣ የአፋብህና ጥንካሬ የማይፈልጉ፣ እጆቻቸውን አስረዝመው ችግር የሚፈጥሩ ወገኖች አፋብሃ የሚያስታምም ከሆን ፣ ድርጅቱ ከሎጎ የተሻገረ ድርጅታዊ ቁመና ሊኖረው እንደማይችልም አሳስቧል።
በነገራችን ላይ በዚህ አጋጣሚ ትላንት ጸረ ጎጃም ፕሮፖጋንዳ ሲነዙ የነበሩ፣ አሁን ደግሞ የጎጃም ተቆርቋሪ ሆነው ሲቀርቡ ስናያቸው እየተዝናናን ነው፡፡ ትልቅን የጎጃም ፋኖዎችን ሲሰድቡ የነበሩ፣ አሁ የጎጃም ፋኖዎች ወታደራዊ አዛዥ፣ ሻለቃ ዝናቡን ፣ ጥንቃቋ ካልተደረገን ስራችንን በተክክል ካልሰራ አፋህድ ሎጎ ብቻ ይሆናል ያለውን፣ ቆርጠውና አጣመው በማውጣት፣ በጎጃም ወንድሞ ዘንድ ክፍፍል እንዳለ ለማሳየት እየሞከሩ ነው፡፡
በቀደም እለት ደግሞ ኢንጂነር ማንችሎት ከሃላፊነቱ ተነሳ በሚል አፋህዶች ሲንጫጩ ነበር፡፡ ኢንጂነር ማንሽሎት ተነሳ፣ አልተነሳ የማወቀው ነገር የለም፡፡ ጎጃም እኮ ተቋም ነው ያለው፤፡ ያንን እንዴት ይረሱታል፡፡ አንድ አመራር እኮ ሊያገለግል እንጂ በውርስ የያዘው ምንም አይነት ቦታ የለም፡፡ የአፋብሃ የጎጃም ቀጠና ፣ ተቋሙ ካመነበት ማንችሎት ብቻ አይደለም፣ አርበኛ ዘመነ ካሴም አስፈላጊ ከሆነ ይነሳል፡፡ ትግሉ ከግለሰቦች በላይ ነው፡፡ ጎበዝ፡፡
የተያያዘው ፎቶ፣ የማዕከላዊ ኮማንድ አባላት፣ ፋኖ ዘመነ ካሴ፣ ፋኖ አስረስ ማረ፣ ፋኖ ሻለቃ ዝናቡ እንዲሁም፣ የአፋብሃ የጎጃም ቀጣና ቃል አቀባይ ፋኖ ማርሸት ነው፡፡