
ከደቡብ አፍሪካው ስምምነት በፊት ባደረጉት ውይይት “ወልቃይትና ራያን እንሰጣችኋለን” ተብሎ ቃል ተገብቶላቸው ነበር። ሆኖም ለድርድሩ በየፊናው ዝግጅቶችና ስጋቶች ወዘተ ነበሩ። አማራ ብልፅግና ድፍረት ባይኖረውም እድሜውን የሚያሳጥር ነገር እንዳለ ግን ተነግሮታል። “በወልቃይትና ራያ ጉዳይ ህዝብ ይበላችኋል” ተብሏል። እናም አቋም ያዘ።
በድርድሩ ዝግጅት ደመቀ መኮንን የልዑክ መሪ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ ሬድዋን፣ ዶክተር ጌታቸውና ጌዲዮንን ጨምር አባል ነበሩ። በመሃል አንድ ሴራ መጣ።
“ህወሓትን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ አናወራውም” አሉ። ለልዑክ መሪ ሬድዋን ይበቃል ተብሎ ሁለቱ የአማራ ብልፅግና አመራሮች ሲቀሩ ዶክተር ጌታቸው ጀምበር አብሮ ተጓዘ።
ድርድሩ ወደ መጨረሻው ደርሶ ትህነግ ግን ቁልፉን ጉዳይ ሳያነሳ ቀረ። የወልቃይትና የራያ ጉዳይ። በደንብ ተጠንቶበት፣ ከእነ ሬድዋን ጋር ተነጋግረው ያደረጉት ነው። በስምምነቱ አንቀፆች “ትግራይ፣ ትግራይ፣ ትግራይ” እየተባለ የተጠቀሰውን ሁሉ “ወልቃይትና ራያም ትግራይ ተብሎ ነው የተፈረመው” ብለው ሊያነሱ ነበር የፈለጉት። በዚህ መንገድ ነው አሳልፈን የምንሰጣችሁ ተብሏል።
እነ ሬድዋን አላነሱትም። ዶክተር ጌታቸው ጀምበር ግን የቀረ ጉዳይ አለ ብሎ አነሳ። “ወልቃይትና ራያ ጉዳይ ላይ ውይይት መደረግ አለበት” አለ። እነ ሬድዋንና ጌታቸው ረዳ ተቃወሙ። እነ ጌታቸው ረዳ ምክንያታዊ ለመምሰል ሞከሩ። የሴራው አካል ነው።
እንዲህ አሉ። “ይህ ተራ ነገር ነው። መከላከያ መቀሌ ይገባል ብለን ተስማምተን የወልቃይትና ራያ ጉዳይ ሊያጨቃጭቀን አይገባም” አሉ።
እነ ሬድዋን ቀጠለ። “ችግር የለውም። እነሱ ባላነሱበት እኛም አናነሳም” አሉ። ጌታቸው ጀምበር “ይህ ጉዳይ በስምምነት ካልተጠቃለለ አቋርጨ ወደ ኢትዮጵያ እመለሳለሁ” አለ። ይሄ ከመሆኑ በፊት ተብሎ ለሬድዋን ተደወለለት። የተደራዳሪው ቡድን መሪ የነበሩ ሰዎች ቢደውሉለት ስልክ አያነሳም። ጠፋ! ጠፋ! የግድ ሲሆን በሰው መልዕክት ይድረሰው ተብሎ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የድርድር ቦታው ድረስ ሄዶ በአምባሳደሩ ስልክ ተገኘ። “ስምምነቱ ከሚፈርስ በልዩ ሁኔታ ይታይ ተባለ።
መጀመሪያ የተነሳው ወልቃይትና ራያ የአማራ መሆኑን ትህነግ እንዲያምን ቢሆንም እነ ጌታቸው ረዳም ህዝብ ይበላናል አሉ። በተጨማሪ ድርድር አከራካሪና ባሉበት ቆይተው ጉዳያቸው የሚታይ በሚል መንፈስ ስምምነት ተደረገ። ጉዳዩ ከዚህ የተሻለ ስምምነት ያስፈልገው የነበረ ቢሆንም እነ ሬድዋን ግን በዚህም አበዱ።
በቀጣይ በኬንያ በተደረገው ስምምነት ዶክተር ጌታቸው እንዳይገኝ ተደረገ። ደቡብ አፍሪካ ላይ አላማችን አምክኗል ብለው ነው። ኬንያ ላይ የጓዳ ስምምነቷ በስፋት ተጀመረች። ደቡብ አፍሪካ ላይ ትጥቅ መፍታት አለበት ተብሎ የነበረውን ትህነግ ሬድዋን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በሰጠው መግለጫ ሲጠየቅ ያ አስቦት የነበረው ስላልተሳካ “ስጋት ስላለባቸው ትጥቅ አይፈቱም” ብሎ ከስምምነቱ ውጭ በንዴት ተከራከረላቸው። በኬንያውና ሌሎች የጓዳ ስምምነቶች አማራው ላይ ዶልተዋል። ወልቃይትና ራያ ላይ ያሰቡት ሙሉ በሙሉ ስላልተሳካ ሌላ ዘዴ አመጡ። “አማራው ትጥቅ ይፈታል። እናንተ ትጥቅ አትፈቱም። ገብታችሁ ትወስዳላችሁ” አሏቸው። በዚህ መሰረት የአማራ ልዩ ኃይል ትጥቅ እንዲፈታ፣ እንዲበተን ተደረገ። በቀጣይ ፋኖን ትጥቅ አስፈትተን አማራን አብረን እንመታዋለን ብለው አስበው የተነሱበት ግን ሌላ የማይወጡት ጦርነት ውስጥ አስገባቸው።
አሁንም ያ ንዴት አለቀቃቸውም። ብስጭቱ እንዳለ መሆኑን ሬድዋን ምሳሌ ነው። ሬድዋን በድርድሩ ወቅት ፈተና የነበረው ብሎ ያነሳው የወልቃይትና ራያ ጉዳይ የተነሳበትን ነው። አላማውን ስላጨናገፈበት ነው። ይህ ብቻ ግን አይደለም። ሬድዋን የአማራን ጉዳይ ያነሱት “በመንደር ተደራጅተው” ሲል አማራውን ሰድቧል። የወልቃይትና ራያ ጥያቄ የአማራ መሰረታዊ ጥያቄ ነው። ሬድዋን ግን አማራን መንደር አደረገው። እሱ የተደራጀውኮ ጉራጌ ውስጥ ሙስሊም የሆኑትን “ብሔር” አድርጎ ነው። ይህ ስድቡ ግን ካልበረደው ንዴቱ የመጣ ነው። ሊያስፈፅመው ያሰበው በመኮላሸቱ ያደረገው ነው። ደግሞ አያፍርም። ምን ሞራል አለውና አማራን የጎዳ መስሎት “ትጥቅ አይፈታም” ብሎ የተከራከረለት ትህነግ ችግር ሊፈጥር ነው የሚለው። እነሱ በጓዳ ውል ያቆዩት ኃይል አይደለም ወይ?
በእርግጥ ሬድዋን ፖለቲካ ሲጀምር አማራን እያጥላላ ነው። ግን አሁንም ጥላቻው ትኩስ ነው።