ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 21, 2025

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል]

(https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/)

ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ  ብቻ የተመሠረተ መሆኑን እየገለጽኩ፣ በትችት መልክ ባቀረብኩት አስተያየትም ሆነ በወሰድኩት አቋም ግን እንደማልፀፀት ለመግለጽ እወዳለሁ።

ትዝታ በላቸው የዛሬ አሥራ አምስት ዓመት ገደማ በተደጋጋሚ በቮይስ ኦፍ አምሜርካ ራድዮ ላይ ስለ አፍሪቃ ቀንድና፣ በተለም በመካከለኛው ምሥራቅ ይካሔድ የነበረውን  የፖለቲካ ትርምስ በተመለከተ ሁለታችንን፣ ጃዋርንና እኔን  በቃለ ምልልስ ግምገማ እንድናቀርብ አገናኝታን ነበር። ከዚህ ውጪ እኔ የግለሰቡን የሕይወት ታሪክ ለማወቅ ፈልጌ፣ ያገር ፖለቲካ ሒደቱንም ሆነ የውዝግብ ቦርሳውን ተከታትዬ አላውቅም 

ፕሮፌሰር መረራ የላከለትን ስለ እሱ ያቀረብኩትን ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ የተባለ አዎንታዊ ችችት ካነበበ በኋላ  “ጃዋር ኦሮሞዎች በአብላጫ ሙስሊም ናቸው” ብሏል ስል ያቀረብኩት ዘገባ  ትክክል አይደለም ብሎ ከመካድ በስተቀረ በግምግማዬና በምሁራዊ አስተዋፅኦዬ እጅግ አወድሶኛል። 

ከያቅጣጫው ግን፣ ‘ጃዋር ሀገሪቷ አሁን ያለችበትን  ግጭት፣ ወታደራዊ አለመረጋጋትና የፖለቲካ ውዥንብር ለማራቅ፣ ሚዛናዊ ግንዛቤና ወሳኝ ምክሮችን መስጠት የጀመረ ቅን ኢትዮጵያዊ መሆኑን አስመስክሯል‘  ይምትለልው ያሁኑ የጃዋር የመታደስ ጨዋታ፣ በጥበብ  የተሸመነ ማላገጫ ትርኢት መሆኑን ባታውቅ ነው፣ ምክንያቱም የዛሬ ፲፩ ዓመት ገደማ፣ እንደዚሁ የኦሮሞን ጠባብ ብሔሔርተኝነት አቋም አሽቀንጥሬ ጥያለሁ፣ ከዛሬ ጀምሮ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ቆራጥ ጠበቃ ነኝ ብሎ ስለ ዛተ ቅንና ከልቡ ተቀስቅሶ የተነሳ መስሎን፣ ብዙዎቹ  አገር ወዳድ ዜጎች በምስጋና ላይ ምስጋና አከናንበነው  ነበር። ሌላው ቀርቶ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን ዋና ስብሰባ  ሲደረግ በሊቀ መንበርነት ይመራ ዘንድ ሾመነው ነበር።  ጃዋር ግን ሳይውል ሳያድር ሾኬ ተጫውቶ  አክሮባቲክስ በመሥራት   ግልብጥ ብሎ ወደ ቀድሞው አቋሙ ተመለና በኢትዮጵያ ላይ ዛቻ በመሰንዘር ቪዲዮ ቀርጾ በያለበት በተነ።  ይህንን ድርጊት አስከፊ የሚያደርገው፣  እሱና የሱ ተከታዮች የሀሰት ወሬ እንዲነዛ በማድረግ  በአዲስ አበባ አካባቢ የነበሩትን የቄሮ ጀብደኞች አደፋፍረው በመቀስቀስ የብዙሃን ዜጎችን ሕይወት ሰለባ አድርገዋል።    

ጃዋር አሁን ወደ ፖለቲካው የተመለሰው የሥር ነቀል ለውጥ መንፈስ አፍጦ መምጣቱን ስለተገነዘበ ነው። ይኸን እቅዱን ሥራ ላይ ለማዋል ተዛማጅም ለመሆን ከአማራ ልሂቃን የተወሰነ ድጋፍ ማግኘት እንዳለበት ያውቃል፣ የሚል ትችት ከአምስት እማኞች ነን ከሚሉ ከድያስፖራና ካገር ነዋሪ ምሑራን በተለያየ አጻጻፍ፣ መልዕክቱ ግን ተመሳሳይ ከሆነ ኢሜይል መልዕክት ደረሰኝ። ከዚህ በኋላ ነው ነቅቼ እንደ ተግባረኛ የፖለቲካ ሳይንቲስት ስለ ጃዋር የፖለቲካ ሒደት ለመመርመር ኢንተርኔትን ማሰስ የጀመርኩትና ወደ መጨረሻ ላይ ያያያዝኩትን የቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም ያገኘሁት።  

ጃዋር ከዚህ ጋር ተያይዞ ካለው ቢቢሲ በቀረፀው የቪዲዮ ስረጭት ላይ ሲናገር፣(https://www.youtube.com/watch?v=ahlyH8YEFs0) “እኔ በምኖርበት አካባቢ ዘጠና ዘጠኝ ከመቶው ሕዝቡ ሙስሊም ነው። ማንም ከተተናኮሰን ያን ሰው በሜንጫ ከማጥቃት ወደ ኋላ አንልምብሎ ሲናገር ይደመጣል። ቢቢሲ በመቀጠል ባለፈው ሰሞን ብዙ የአማራ ህዝብ በጭካኔ ተጨፍጭፏል ይልና ከሁለት ሚሊዮን ተኩል ሕዝብ ባላይ ተከታይ ያለው ኤም ኤን የተባለው የጃዋር ሚዲያ ቅኚ በአማራው ሕዝብ ላይ ጎጂ ፕሮፓጋንዳ  በመንዛትና ብሔር ተኮር ጥቃትን በመቀስቀስ ለፈፀመው የግድያ ወንጀልና የዘር ማጥፋት ድርጊት ተጠያቂ ያደርገዋል። ይህነኑን የጃዋር ሚዲያ ቅኚ በጎርጎርዮሳዊ የቀን መቁጠሪያ መሠረት 1994 የሩዋንዳን የዘር ጭፍጨፋ  ጭካኔ መንገድ በመጥረግ ስምንት  መቶ ቱትሲዎችንና ለዘብተኛ ሁቱዎችን ካስፈጀው የአክራሪ ሑቱ ወሬ ማሰራጫ አር ኤል ኤም ጋር ያወዳድረዋል።

እኔም ወዲያው የዘሐበሻ ግምገማዬ በተናጠል መሆኑ ገባኝ። ለዚህም ስሕተት አንባቢዎቼን ከፍ ያለ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ይህ ሲባል ግን፣ በኔ አስተያየት ጃዋር በስብዕናው ስለተገለባበጠና የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ አድርጓል ተብሎ ስለተከሰሰ ብቻ ክዛሬ ጀምሮ ጠባብ ብሔርተኛ አይደለሁም ካለ እምነት ሊጣልበት አይችልም ማለት ትክክል አይደለም የሚል አቋም አለኝ። እራሱን እንዲያረጋግጥ እድል ሊሰጠው ይገባል። የቀድሞ ዳራው ምንም ቢሆን ሰው  ሊለወጥ ይችላል። ይኽን አቋም ከታዋቂው የፖለቲካ ኢኮኖሚ ተንታኝ ከዶክተር ዮናስ ብሩ ጋር እንደምጋራ ከሞገስ ዘውዱ ተሾመ ጋር ካደረገው  ቃለ ምልልሱ ተረጅቻለሁ።  

ለዚህ አቋም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ምንም እንኳ ጃዋር የተከሰሰበት ጥፋት በምኑም ደረጃ ባይመስለውና ባይመጣጠነው፣ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ግብፅ አገር ውስጥ ኢትዮጵያዊው ሙሴ የተባለ  ነፍሰ ገዳይ፣ ሰው መግዳል ብቻ ሳይሆን አመንዝራ፣ ወንበዴ፣ ቀማኛ ሽፍታና ወሮ በላ ሆኖ ሲኖር ነበር።  የኋላ ኋላ ግን መጥፎ ግብሩ ፀጽቶት ከንግዲህ ወዲያ በሕግ ተገዝቼ እኖራለሁብሎ ቃል በገባ ጊዜ ያኔ የነበሩት የሃይማኖት አባቶች ዕድል ሲሰጡት የገባውን ቃል አሟልቷል። እና በመጨረሻም ይኽ ሰው አለግዛንድርያ አጠገብ ኤልባራሙስ የተባለ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገዳም አቋቁሞ ብዙ ሰው በማስተማሩ ብቻ ሳይሆን፣ በቅድስና ኑሮው ምክንያት በሁሉም የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ቅዱስ ሆኖ እስከ ዛሬ እንደተዘከረ ይኖራል።

Prof. Paulos Milkias
Concordia University 

 

 

 

 

4 Comments

  1. ፕሮፌሰር ጳውሎስ

    እንደ አለመታደል በወሬ በመደልል ከሚታለሉት ምሁራን አንዱ ነዎት፡፡ በፊት በሙሴው አሁን ደሜ በጅዌው! ያሳዝናል፡፡

  2. ፕሮፌሰር ጽሁፎ አላለቀም መሀል ላይ ተጎምዷል። በእውነት “የተለወጠ መስሎኝ” ነበር ያሉት አንቀጽ ትንሽ ግር ይላል። እንዲህ ያለ በዘረኝነት ያበደ ማሰብ የማይችሉትን መንጋዎች እየመለመለ መተዳደሪያውን ያደረገ ቀጣፊ ሀገር ወዳድ ሁኖ ለአንድነት ሊሰራ ይችላል የሚለው እምነት ከየዋህነት በላይ መሰለኝ።

    ሲጀመር ጁዋር ማሰብና መጠየቅ የማይችል ግሩፕ አፈራ ያንን መጋለብ ያዘ ከተከታዮቹ ያልተሻሉ የሚዲያ ተቋሞች እየቀረበ መበጥረቅ ያዘ ፣ አፍ እፉን የሚጠብቁ ጋዜጠኞችም ሊሞግቱት ድፍረትን አጡ፣ ይህ እሳት የተባለውን የብርሀኑ ነጋን የፕሮፓጋንዳ ድርጅት ይጨምራል። ታዲያ በዚህ የተበረታታው ኦቦ ጁዋር በሐጅ ነጅብ ስብሰባ ላይ ክርስቲያኑን እረዱት ብሎ ፋታዋ ሲያስተላልፍ በራሱና በሌሎች ሚዲያ ቀርቦ የለውጡ ቀመር እኔ ዘንድ ነው የተሰራው ብሎን አረፈ፣ብዙ ሀገራትን በማማከር እረዳለሁ፣ከዚህ አልፎ የአረብ ስፕሪንግ ውስጥ ዋናው ሞተር እኔ ነበርኩ እያለ ፏለለ።

    ኦሮምያ ብለው ትግሬዎች ባካለሉት አጥር ለተበላው ፣ለተገደለው፣ለተገፈፈው የአማራ፣የደቡብ ፣ የሱማሌ ተወላጅ ጁዋር መሀመድ በዋናነት ተጠያቂ ነው። በእርግጥ ዛሬ ላይ ከወንጀል ወንድሙ ከበቀለ ገርባ ጋር ከሀገር እንዲወጡ ቢደረግም በሰው ወይም በአምላክ ፍርድ እንደሚወድቁ ጥርጥር አይኖርም። ባጠቃላይ ግልብነት ፣ወንጀል፣ቅጥፈት ጁዋር የተሰራበት ባህሪ በመሆኑ ከዚህ ሊለወጥ አይችልም ታሪኩም የሚያሳየው ይህንኑ ነው።

  3. Well, I do know and I do agree that every person has the right to interpret and reflect ideas or views in a way he or she understands !
    But this does not mean that he or she is always wise enough to reflect the very clear and hard reality based on the real meaning of intellectualism .
    It is from this perspective of mine that the above piece of writing about the very notorious and seriously deceiving political personality of Jawar Mehamed is so weak and misleading!
    I really do not know when and how our intellectuals will be willing and able to go beyond the very bookish type of argument and analysis!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

Next Story

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

Latest from Same Tags

አረንጓዴ ልብ፣ ጥቁር ልብ፣ ሰይጣናዊ መንፈስ!

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) (መስከረም 21፣ 2017) October1,  2024) በጀርመን፣ በፍራንክፈርት አማይን በሚባል የታወቀ የፋይናንስና የባንክ ከተማ በወጣት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሰራተኞች የተቋቋመ አረንጓዴ ልብ(Green Heart) የመረዳጃ፣ የባህልና ከዚህም በመሆን
1967-74: Ethiopia's Student Movement

የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴና የ1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት ዋዜማ – ፫ በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)

(ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እ.ኤ.አ. ከ 1950-1975 ‹‹… ጭንቅ ብሎኛል ኢትዮጵያዊ ማን ነው? ወጣት ሽማግሌው አገር ሲጠየቅ፤ አንዱ ጐጃም ነኝ ሲል ሌላው በጌምድር፤ አንዱ ኤርትራ ሲል ሌላው ተጉለት፤ አንዱ መንዝ ነኝ ሲል ሌላው ጋሙ ጐፋ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ ብፈልገው ጠፋ፤ እስቲ አዋቂዎች እናንተ ንገሩኝ፤ እኔን ያስጨነቀው ኢትዮጵያዊው ማን ነው…?!››   (በ1950ዎቹ በዛን ጊዜው ቀ.ኃ.ሥ ዩኒቨርሲቲ

❝እነርሱን ቀርቶ እነርሱን መሰል ቡድን በኢትዮጵያ ምድር ዳግም እንዳይበቅል መሥራት ይገባል❞ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው እና ለወገናቸው ቀናዒ ልቦናን የታደሉ ስለመሆናቸው የሀገር ውጭ ጸሐፍት ሳይቀር በድፍረት ይናገራሉ፡፡ ስለሀገራቸው ክብር፣ ስለወገናቸው ፍቅር ሲሉ የማይወጡት ተራራ፣ የማይወርዱት

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ! – ማላጅ

ኢትዮጵያ ….ኢትዮጵያ እያለ በቃላት  የሚጠሩት ዕልፍ አዕላፍ ናቸዉ ትናትም ኢትዮጵያ ሲሉ በልባቸዉ የጥላቻ እና የጥፋት ቋጠሮ ሸክፈዉ ለዉድቀቷ ከዉስጥ እና ከዉጭ ጠላት ጋር ህብረት
Go toTop

Don't Miss