#በቃ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “መንግስት በሰላም ስልጣን እንዲለቅ” ጠየቁ!

June 24, 2022

https://www.facebook.com/100058666369421/videos/524086579456631/

በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ተከታታይ ጅምላ ጭፍጨፋ በመቃወም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ዛሬ አርብ ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም.በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
ተቃውሞውን የጀመሩት የፋሲል፣ ቴዎድሮስ እና ማራኪ ካምፓሶች በተመሳሳይ ጊዜ በመውጣት በጥምረት ነው።
ገዥው ፓርቲ እያካሄደ ያለውን የችግኝ ተከላ ዘመቻ በጎንደር ከተማ ውስጥ ለማስጀመር ቤት ለቤት ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያለ ነበር ተቃውሞው በድንገት የፈነዳው። ኗሪዎችም የችግኝ ተከላ የቤት ለቤት ቅስቀሳውን ባለመቀበል ተቃውሟቸውን ገልፀዋል።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየተደረገ ባለው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ “ፋኖ ዛሬም ነገም ወደፊት፣ ብልፅግና ወደ ኋላ፣ መንግሥት በሰላም ና በፍቅር ሥልጣኑን ይልቀቅ፣ እኛም ያልተገደልነው ወለጋ ስላልተገኘን ነው” የሚሉ መፈክሮች ተደምጠዋል።
ከአሻራ ሚዲያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“አብይ አህመድ በአማራ ክልል ፋኖን የማጥፋት እቅዱ 100 ፐርሰንት ግቡን ባለመምታቱ ነው ፊቱን ወደ ወለጋ አዙሮ፣ የበቀል እርምጃ የወሰደው።” – ፓስተር ደረጀ ከበደ

Next Story

አማራ የሆንክ ስማ??

Go toTop