ለፓርቲው የክልል/የብሔር ቅርንጫፎች የተሰጠው ኮታ ‹‹ክልሎቹ/ቅርንጫፎቹ ባላቸው የሕዝብና የአባላት ብዛት›› ነው፡፡ ኦሮሚያ ክልል ከ3 ሚሊዮን በላይ፣ ሱማሌ ክልል ከ2 ሚሊዮን በላይ ደቡብ ክልል ከ2.1 ሚሊዮን በላይ፣ ሲዳማ ክልል 2 ሚሊዮን አባላት አለን ብለው አስመዝግበዋል፡፡ የዐማራ ክልል/ዐማራ ብልጽግና ደግሞ 1.9 ሚሊዮን አባላት አሉኝ ብሎ ከጠቅላላ ጉባዔው ተሳታፊዎች መካከል 15% ድርሻ ብቻ ተሰጥቶታል፡፡ አዲስ አበባ ራሱን የቻለ ውክልና የለውም፡፡ አስገራሚው ነገር የአባላቱ ቁጥር የተወሰነው ገና ባልፀደቀ የፓርቲው ደንብ ነው፡፡
ይህ የሚያሳየው የጉባዔተኞቹ ቁጥር የኦሮሞ ብልጽግና የሚፈልገውን ውሳኔ ለማስወሰን እንደሚያስችለው ነው፡፡ የኦሮሞ ብልጽግናና እሱ የሚያዝዛቸው ሌሎቹ የክልል ፓርቲዎች (የአፋር፣ የጋምቤላ፣ የደቡብ፣ የሲዳማ፣ የቤ/ጉሙዝ …) በድምሩ ከዐማራ ብልጽግና የበለጠ ቁጥር ስላላቸው የኦሮሞ ብልጽግና የሚፈልገውን ውሳኔ በድምጽ ብልጫ ያስወስናል ማለት ነው፡፡
ዐቢይ አህመድ ባለፈው ‹‹ሃሳቡን ተወያይተንበት የማይስማማ ካለ በድምፅ ብልጫ ይወሰናል›› ብሎ የተናገረው ይህንኑ ተማምኖ ነው፡፡