አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአማራ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ የአማራን ሕዝብ ከጠላት የሚከላከል፣ ከውርደት የሚታደጉና በልማትና በፖለቲካው መስክ ተጠቃሚ እንዲሆን ዋጋ የሚከፍሉ ሁሉ ፋኖዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም መንግሥት ለአገር ሕልውናና ለሕዝብ ነጻነት የተጋደሉና ጀብድ የሠሩ ፋኖዎችን የበለጠ ያደራጃል እንጂ ትጥቅ አያስፈታም ብለዋል፡፡
የአሸባሪው ሕወሓት ቡድንን ወረራ ለመቀልበስ ፋኖዎች ትልቅ ጀብድ ፈጽመዋል፤ የሕይወት መስዋዕትነትም ከፍለዋል ያሉት ቢሮ ኃላፊው፤ መንግሥት ለእነዚህ ሰዎች እውቅና ሰጥቶ ይሸልማል እንጂ ትጥቅ የሚያስፈታበት ምክንያት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
የመንግሥት ሃሳብ ለአገሩ ሲዋደቅ ጉዳት የደረሰበትን ፋኖ ለሌሎች ኃይሎች በሚደረገው አግባብ እንዲታገዝ ፣ ለአገር ክብር ለተሰዋውም ለሌላው እንደተደረገው ማድረግ እንጂ..