ውድመት የደረሰባቸውን ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሥራ ለማስገባት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ!

January 15, 2022

ውድመት የደረሰባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሥራ ለማስገባት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።

የኢትዮጵያ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ ፥ ”በድህረ ግጭት ማገገሚያ ተግዳሮትና ዕድሎች” ዙሪያ ከሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፥ አሸባሪው ህወሓት ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።

ከ4 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው ፥ 1 ሺህ 90 ዎቹ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልጸዋል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደግሞ በአማራ ክልል ብቻ ቡድኑ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹን መልሶ ለማቋቋምና ወደ መማር ማስተማሩ ሥራ ለመመለስም ከፍተኛ ወጪ እንደሚጠይቅም ገልጸዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመዘጋታቸው የተነሳ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከትሉ በርብርብ ፈጥነው ወደ ስራ እንዲመለሱ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና መልሶ ግንባታውን በሃላፊነት ለመተግበር በዕለቱ ስብሰባ ጠቃሚ ሀሳቦች መገኘታቸውን ተናግረዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶክተር ሃብታሙ አበበ በበኩላችው፥ የወደሙትን ዩኒቨርሲቲዎች መልሶ ለመገንባት ቅንጅታዊ ሥራ ያስፈልጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የሕይወታቸው መጨረሻ ሰዓት እና የመቅደላ ዝርፊያ

Next Story

እኔም ስሰማ በጣም ደንግጫላሁ

Go toTop