እስራኤል የጦር ወንጀል የፈጸሙ ኢትዮጵያውያንን እመልሳለሁ አለች

November 10, 2021
ህዳር 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) እስራኤል የጦር ወንጀል የፈጸሙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንደምትመልስ ቃል መግባቷን ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘገባ አመለከተ።
እስራኤል ይህን ያለችው ወደ አገሯ በስደት ከገቡት ኢትዮጵያውያን መካከል አራቱ የጦር ወንጀል የፈጸሙ በመሆናቸው ኢትዮጵያ ቅር መሰኘቷን መግለጿን ተከትሎ ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከእስራኤሉ አቻቸው ናፍታሊ ቤኔት ጋር በስልክ መነጋገራቸው ታውቋል።
በኢትዮጵያ የጦር ወንጀል በመፈጸም መሪ ተዋንያን የሆኑ ወንጀለኞች ወደ ጎረቤት አገራት እንዳይወጡ መንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በተለያየ አጋጣሚ ወደ ውጭና ወደ ጎረቤት አገራት የወጡ ወንጀለኞች ሲገኙም ከአገራቱ መንግሥታት ጋር በመነጋገር ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።
በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ቀውስ ከተፈጠረ ወዲህ ማይካድራን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የጦር ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችና ቡድኖችን ተጠያቂ ለማድረግ መንግሥት በትኩረት እየተንቀሰቃሰ እንደሚገኝ ይታወቃል።
_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል

Next Story

ኦሮሞ ብልፅግና ውስጥ ያሉ ብዙዎቹ ከኦነግ ጋር የሚሰሩ ክኦነግ ጋር ድርድር እንዲደረግ የሚፈልጉ ናቸው – ግርማ ካሳ

Go toTop