አሸባሪው ሕወሓት ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በማይካድራ ከ1 ሺሕ 200 በላይ ንፁሃን ዜጎችን በግፍ የጨፈጨፈበት 1ኛ ዓመት ዝክረ መታሰቢያ በባህርዳር ከተማ ሻማ በማብራት እና የኅሊና ፀሎት በማድረግ በሚሊኒየም አደባባይ ተከብሯል።
በመርኃግብሩ የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፣ የባህርዳር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ የኔሰው መኮንን እንዲሁም ሌሎች የከተማዋ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና በርካታ የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።