የሊቢያው አምባገነን መሪ ሙሀመድ ጋዳፊ የጉዲፈቻ ልጅ የሆነው አብደላህ ሞኔ ሙሳ ሙማሬ በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ አስቸገረ፡፡ ይህን የዘገበው የዚምባቡዌው ሄራልድ ጋዜጣ ነው፡፡
የዚምባቡዌ ሴኔት ትላንት የተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ፣ የህግና የፓርላማ ጉዳዮች ሚኒስትሩን ሪፖርት ባዳመጠበት ወቅት ሚኒስትሩ ዚያምቢ እንደተናገሩት የጋዳፊ ልጅ በአዲስ አበባ ከአውሮፕላን አልወርድም ብሎ አስቸግሮ ነበር፡፡ አባቱ በ2011 አ.ም ከተገደሉ ከሶስት አመታት በኋላ በ2014 የዚምባቡዌ ዋና ከተማ ሀራሬ የደረሰው ሙማሬን ወደአገሩ ለመውሰድ በተሞከረበት ወቅት ይህ ድርጊት መፈፀሙን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በዚምባቡዌ ስደተኞችን ማስተዳደር እንደማይቻል የገለፁት ሚኒስትሩ ለተወሰነ ጊዜ አቆይተው ወደመጡበት አገር የመመለስ አሰራር እንዳለ አስረድተዋል፡፡ ይህንን ልጅም ወደሊቢያ ለመመለስ በኢትዮጵያ በኩል ባለው ትራንዚት በረራ አዲስ አበባ ላይ ወደሊቢያ የሚጓዘው አውሮፕላን ላይ ሊያሳፍሩት ሲሉ ከአውሮፕላን አልወርድም ማለቱን ለሴኔቱ አስታውቀዋል፡፡ ወደሊቢያ ከሄደ እንደሚገደል በመናገሩም ወደዚምባብዌ ለመመለስ መገደዳቸውን አስታውቀዋል ሚኒስትሩ፡
https://www.youtube.com/watch?v=3DhpJfLazkE&t=397s