በርካታ ትችቶች የሚሰነዘርበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማዕከላዊ ባንክነቱን ሚና በአግባቡ እንዲጫወት፣ ከማንኛውም የመንግሥት ተፅዕኖ ነፃ ሆኖ እንደ አዲስ እንዲዋቀር የተለያዩ ባለሙያዎች ሐሳብ ቀረቡ፡፡
ማክሰኞ ታኅሳስ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተከፈተው ሦስተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፖለቲካ ሹመኞች ሲመራ በመቆየቱና የመንግሥት ፖሊሲ አስፈጻሚ በመሆኑ የማዕከላዊ ባንክ ዋነኛ ኃላፊነቱን መወጣት እንደተነሳው ተናግረዋል፡፡
በጉባዔው ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ካቀረቡት በርካታ ምሁራን መካከል አንዱ የነበሩት የምጣኔ ሀብት ተንታኝ አቶ አብዱልመናን መሐመድ፣ ብሔራዊ ባንክ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት እንዳለበት በአጽንኦት መክረዋል፡፡ ‹‹ብሔራዊ ባንክ ገለልተኛ መሆን አለበት ስንል የተቋቋመበትን ዓላማ ማየት አለብን፤›› ያሉት አቶ አብዱልመናን፣ ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡ የፋይናንስ ሥርዓቱ ጤነኛና የተረጋጋ እንዲሆን ማድረግና ለኢኮኖሚ ዕድገት ድጋፍ ማድረግ፣ ባንኩ የተቋቋመባቸው ዋና ዋና ዓላማዎች እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡ (Reporter Newspaper)
–
በገቢዎች ሚኒስቴር በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 41 ሺ 693 የአሜሪካ ዶላር በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ግለሰቦቹ አረጋዊ ኪዱ፣ጽጌ ብርሃኔ እና ክብሮም ገብረ ሚካኤል የተባሉ ሲሆን ታህሳስ 10/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 አካባቢ በቶጎ ጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጉምሩክ ሰራተኞች መያዛቸዉን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ ተናግረዋል፡፡
–
የሰንሻይን ኮንስትራክሽን አደጋ የግንባታ ደኅንነት ጥያቄ አስነሳ
ቅዳሜ ታኅሳስ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ከሰንሻይን ኮንስትራክሽን ሕንፃ ላይ የወደቀ ሠራተኛ መሞቱ የግንባታ ደኅንነት ጥያቄዎችን በድጋሚ ቀሰቀሰ፡፡ አደጋው የደረሰው መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገነባ ትልቅ ሕንፃ ላይ ሲሆን፣ ሃያት ዲጀንሲ ሆቴል ከሚገነባበት አጠገብ መሆኑን ሪፖርተር በሥፍራው ተገኝቶ ታዝቧል፡፡
መለሰ አበራ የተባለ የ34 ዓመት ሠራተኛ በሕንፃው ላይ በሥራ ላይ በነበረበት ወቅት ወድቆ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ይህ በከተማይቱ ለግንባታ ደኅንነት የሚሰጠውን ትኩረት አናሳነት ያሳያል የሚሉ ተቃውሞዎች እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል፡፡ በቅርቡ ልጅ እንደተወለደ የተነገረው መለሰ ከሕንፃው እንደወደቀ ሕይወቱ አልፏል፡፡
በኢትዮጵያ የግንባታ ደኅንነት ሕግ ወጥቶ ተግባራዊ የተደረገ ቢሆንም፣ በተለይ በአዲስ አበባ የዚህን ሕግ ድንጋጌዎች ባለመከተልና የመንግሥት ቁጥጥር አናሳ በመሆኑ ተደጋጋሚ አደጋዎች ይደርሳሉ፡፡
–
የምርጫ ቦርድን እንደገና ለማቋቋም የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ::
የጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የህግና ፍትህ አማካሪ ጉባኤ የዲሞክራሲ ተቋማት ጥናት ቡድን በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተፎካካሪ ፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ከዘርፉ ምሁራንና እና ከመንግስት ሃላፊዎች ጋር ዛሬ በተወያዩበት ወቅት እንደገለጹት ለምክክር የቀረበው የምርጫ ቦርድን መልሶ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅም 36 የሚሆኑ አንቀጾች የተካተቱበት ነው::
የውይይቱ ዋና አላማም በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ግብአት መሰብሰብና ሊያሰራ የሚችል አዋጅ እንዲሆን ማስቻል ነው ተብሏል።
–
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የቀድሞ እና የአሁን ከፍተኛ ባለሰልጣናት በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራልም የቀብር ስነ ስርዓታቸው ተፈጽሟል፡፡
ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በሚሊኒየም አዳራሽ የተደረገ የስንብት መርሐ-ግብርን በመጠኑ በቀጣዩ ቭዲዮ እናስቃኛችሁ::
–
የሞያሌ ከተማን ካለፈዉ ሮብ ጀምሮ ያወከዉ ግጭት ጋብ ማለቱን የዞኑ ባለሥልጣናት አስታወቁ። የገሪና የቦረና ታጣቂዎች ባደረጉት ግጭት 41 ሰዎች ተገድለዋል፣84 ሺሕ ሕዝብ ተፈናቅሏል።ግጭቱ የቀዘቀዘዉ መከላከያ ጦር ጣልቃ ከገባ በኋላ ነዉ ተብሏል:: በሌላ በኩል የአካባብቢው ነዋሪዎች ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል:: ግጭት እንዲቆም እንዲሁም ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ጠይቀዋል::
–
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሰምተናል::
–
ከአማራ ክልል ውጭ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ደህንነትን ለማስጠበቅ፣ በሚኖሩበት አካባቢ ውክልና እና ድምጽ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚሰራ መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገ የበይነ መንግስታት ጽህፈት ቤት ማቋቋሙን የአማራ ክልል አስታወቀ።
–
መንግስት ከስድስት ወራት በፊት ያወጣው የምህረት አዋጅ ሊጠናቀቅ 9 ቀናት ብቻ ስለቀሩት፤ አዋጁ የሚመለከታቸው ግለሰቦች በቀሩት ቀናት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አሳሰበ።
https://www.youtube.com/watch?v=fXAfFeqRafs&t=192s