በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተለያዩ የፌደራል ተቋማት ሰባት አዳዲስ ሹመቶች መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በዚህም መሰረት
አቶ ኃይላይ ብርሀኔ ተሰማ፦ የጠቅላይ ሚስትሩ ብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒትር ዴኤታ
ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ፦ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚነር፣
አቶ ሳንዳኮን ደበበ፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
ወይዘሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር
አቶ ተመስገን ጥላሁን፦ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር
አቶ ሙሉቀን ቀረ፦ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር
አቶ ገብረመስቀን ጫላ፦ የኢትዮጵያ ካይዘን አንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡
በተያያዘ ሌላ የሹመት ዜና በሶማሊላንድም አዲስ የኢትዮጵያን ቆንስላ መመደባቸው ታውቋል፡፡ ሸበሌ ሚዲያ የተሰኘው የሶማሊያ ጋዜጣ እንደዘገበው በሃርጌሳ የተሾሙት አቶ ሸምሰዲን አህመድ ሮበሌ ሲሆኑ ቀደም ሲል በጅቡቲና በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን የሰሩ ናቸው፡፡ በሶማሊላንድ ለበርካታ አመታት የኢትዮጵያ ቆንሲላ ሆነው የቆዩት አቶ በርሄ ተስፋዬ የነበሩ ሲሆን አቶ በርሄ ወደአዲስ አበባ ከተጠሩት በርካታ ዲፕሎማቶች አንዱ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=3DhpJfLazkE&t=397s