በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በዜጎች ላይ የመጠለያ ቤታቸውን በማፍረስ በተወሰደው እርምጃ ህጻናት፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች፣ የስኳር ህመምተኞች ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን በተጠለሉበት የሀይማኖት ተቋማት በመገኘት ማረጋገጡን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ።
https://www.youtube.com/watch?v=9_PNwyW18Qg
ተቋሙ በአስተዳደሩ በእርምጃው ተፈናቅለው የተጠለሉትን ዜጎች ትናንት በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ በስፍራው ተገኝቶ ተዘዋውሮ እንደተመለከተ ጠቅሶ፤ ተዘዋውሮ በተመለከተባቸው ድንኳን ውስጥም ከመንግስት ምንም ነገር አቅርቦት አለመኖሩን፤ ነገር ግን ህዝቡ ተባብሮ እየመገበ ያለበትን ሁኔታ ተመልክቻለሁ ብሏል።
በተከሰተው ድርጊት አዝኛለሁ ያለው ተቋሙ፤ የድርጊቱ መንስኤና ውጤቱ ከሚያስገኘው ፖለቲካዊ ትርፍ የሚፈጥረው የመልካም አስተዳደር ብልሽትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እጅግ ያሳስበኛል ብሏል።