በሐዋሳ ከተማ ከትናንት በስቲያ በከተማዋ በኢትዮጵያ ትቅደም ትምህርት ቤት የተደራጁ ወጣቶች የግቢውን አጥር…

January 13, 2019

በሐዋሳ ከተማ ከትናንት በስቲያ በከተማዋ በኢትዮጵያ ትቅደም ትምህርት ቤት የተደራጁ ወጣቶች የግቢውን አጥር በመስበር ሁከት ለመፍጠር ያደረጉትን ጥረት የፖሊስ ሀይሉ እና ህብረተሰቡ ባደረገው ርብርብ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን እና ተጠርጣሪዎችን ማሰሩን ፖሊስ አስታወቀ::
https://www.youtube.com/watch?v=bmsf7vBqDX8

“የእኚህ ፀረ ሰላም ሀይሎች አላማ ከውጭ ተደራጅቶ ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ በመግባት ሁከቱን ተማሪዎች የፈፀሙት በማስመሰል የግጭቱን ቅርፅና ይዘት ሌላ መልክ እንዲኖረው በማስመሰል የግል ፍላጎታቸውን ማሳካት እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።” ያለው ፖሊስ ሆኖም የአካባቢው ህብረተሰብ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ እና በስፍራው ከነበረው የፀጥታ ሀይል ሌላ ተጨማሪ ሀይል በማጠናከር ሁከቱን ሊያባብሱ የሚችሉ የጦር መሳሪያዎችን ሳይቀር ፖሊስ በቁጥጥሪ ስር ሊያውል ችሏል። በዚህ የተቀናጀ የፖሊስ እና የህብረተሰቡ ጥረትም ቱርክ ሰራሽ 12 ሽጉጦች በሁለት ግለሰቦች እጅ መያዝ ተችሏል።

በተመሳሳይም ፖሊስ በሁከቱ ግንባር ቀደም በመሆን ሲመሩ ነበሩ ያላቸውን 36 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢው ምርመራም እያደረገ ይገኛል።” ሲል ፖሊስ በመግለጫው ገልጿል::

Previous Story

የአማራና ሕወሓት ያደራጀው የቅማንት ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ

Next Story

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር በዘርፉ እየተካሄዱ ባሉ የለውጥ ሂደቶች ዙሪያ ተወያዩ

Go toTop