ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር በዘርፉ እየተካሄዱ ባሉ የለውጥ ሂደቶች ዙሪያ ተወያዩ።
https://www.youtube.com/watch?v=bmsf7vBqDX8
የዘርፉ ማሻሻያ የፋይናንስ ተቋማቱን አቅም በመገንባት የበለጠ ተፎካካሪና ብቁ ሆነው ምጣኔ ኃብትን ለማሳደግ ያላቸውን ሚና በማጠናከር ላይ ያተኩራል። ውይይቱ ትኩረት የሰጠባቸው ነጥቦችም፤
1. እስካሁን ድረስ በፋይናንስ ዘርፍ የተደረጉት ለውጦች
2. በዘርፉ ውስጥ የፖሊሲ፤ የአሠራር ሂደትና የአስተዳደር ማነቆዎችን መለየት፤
3. የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር የፋይናንስ ዘርፉን ሚናዎችና ኃላፊነቶች መለየት እና
4. የመንግስት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ዘርፉ የሚጫወተው ወሳኝ ሚና ናቸው። ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር የተደረገው ውይይት ለአገር አቀፍ የመንግስት የልማት ፕሮጀክቶች ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ በመስማማት ተጠናቋል።