ሲግኒቸር ተዘጋ

February 4, 2018

(ዘ-ሐበሻ) ሲግኒቸር ለብዙ ኢትዮጵያዊያን እንግዳ ነው፡፡ እንኳን ለኢትዮጰያዊያን በሙሉ ለአዲስ አበቤውም ቢሆን ባዕድ ነው፡፡ ኧረ ለአራት ኪሎው መንግስትም ባዳ ነው፡፡ ሲግኒቸር የታደሉ ባለስልጣናትና ልጆቻቸው እንዲሁም አንዳንድ የቅርብ ሰዎች ሲጠቀሙበት የከረሙት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የሸራተን አዲስ ሆቴል ብቻ ቃል ነው፡፡ ለበርካታ አመታት እነ ተካ አስፋው፤ እነ መስፍን ባሪያው፤ እነ አበበ ባልቻ፤ የበረከት ስምኦን ልጆች፤ እነ አቦይ ስብሀት ወዘተ… ወዘተ በሸራተን አዲስ ሆቴል የፈለጉትን ተዝናንተው በልተውና ጠጥተው ምንም ሳይከፍሉ ይወጡ ነበር፡፡ የሚወጡት ደግሞ የተጠቀሙበትን ፈርመው ነበር፡፡ ይህ ስርአት በሸራተነኛ ሲግኒቸር ይባላል፡፡ የሲግኒቸር ፈቃጅ ሼህ አልአሙዲ ነበሩ፡፡ ወደ 79 ሰዎች የሲግኒቸር ተጠቃሚ እንደነበሩ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ ከያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ ግን ሲግኒቸር መዘራቱ ታውቋል፡፡ እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን አንዳንድ የሲግኒቸር ተጠቃሚዎች ወደሆቴሉ ጎራ ብለው ተጠቅመው ሲግኒቸር የለም ሲባሉ እየተነጫነጩም ቢሆን ከፍለው ሄደዋል፡፡

Previous Story

በፍራንክፎርት የኢትዮጵያዊያን የነፃነትና እኩልነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኅይል መግለጫ

Next Story

የሕሊና እስረኞቹን አንዷለም አራጌን እና እስክንድር ነጋን ጨምሮ 746 እስረኞች ሊፈቱ መሆኑ ተዘገበ

Latest from Same Tags

Go toTop

Don't Miss