ከቦጋለ አበበ
ካሜሩናዊው ኮከብ ሳሙኤል ኤቶ አፍሪካ የዓለም ዋንጫን የማንሳት አቅም እንዳላት ገለፀ ። ኤቶ አፍሪካ የዓለም ዋንጫን የማሸነፍ አቅም እንዳላት የገለፀው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በጊኒ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ነው።
አራት ጊዜ የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋቾች ማዕረግን የተጎናፀፈው ኤቶ ጊኒን በጎበኘበት ወቅት ለጋዜጠኞች እንደተናገረው አፍሪካ የዓለም ዋንጫን ማሸነፍ የሚችሉ ተጫዋቾች አሏት።ይሁን እንጂ ከአቅም ጋር በተያያዘ ተጫዋቾች ብዙ ስላልተሰራባቸው ዋንጫውን ማንሳት አልቻሉም።
እንደ ኤቶ ገለፃ አፍሪካውያን ተጫዋቾች ትኩረት ተሰጥቶ ከተሰራባቸው አህጉሪቱ ማግኘት ያልቻለችውን ዋንጫ የማታነሳበት ምክንያት አይኖርም።«አፍሪካ የዓለም ዋንጫን የምታሸንፍበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም» በማለት ኤቶ አስተያየት መስጠቱን የዘገበው ሱፐር ስፖርት ነው።
ኤቶ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ህልሟን እንድታሳካ ባለሀብቶች በአህጉሪቱ የማዘውተሪያ ስፍራዎችና ለስፖርቱ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ኢንቨስት ማድረግ አለባቸው ብሏል። እሱም በአፍሪካ እግር ኳስ መዋዕለ ንዋዩን ለማፍሰስ እንደሚፈልግ ገልጿል።
« በሌላ ሀገር የማፈሰውን መዋዕለ ንዋይ እዚህም ልሰራበት እፈልጋለሁ፤እዚህ የመጣሁበት ዋነኛ ምክንያትም ይኽው ነው» በማለት ኤቶ ጊኒ ላይ በእግር ኳስ ኢንቨስት እንደሚያደርግ አሳውቋል። ወደ ጊኒ የሄደበት ዋነኛ ምክንያት በሀገሪቱ ለሚገነባው የወጣቶች የስፖርት አካዳሚ ድጋፍ ለማድረግ ነው።
በጊኒ የተገነባውንና ሃምሳ ሺ ሰው የመያዝ አቅም ያለውን ኖጎ ስታድየም ጎብኝቷል።ጊኒዎች የጀግና አቀባበል ያደረጉለት ኤቶ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንትና ሚኒስትሮች ጋር ውይይት ማድረጉም ታውቋል።
በአሁኑ ወቅት ለሩሲያው ክለብ አንዚማካቻካላ በመጫወት ላይ የሚገኘው ኤቶ ወጣቶችን በእግር ኳስ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ለማፍራት በትውልድ ሀገሩ ካሜሩን ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል።
ሳሙኤል ኤቶ የአፍሪካን እግር ኳስ ለመቀየር እየሠራ ነው
Latest from Same Tags
![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2014/04/colesterol.jpg)
health: ስለኮሌስትሮል ሊያውቁ የሚገባዎት 6 ነገሮች
6. ኮሌስትሮልን በጥቂቱ ኮሌስትሮል የሁሉም እንስሳት ህዋሳት አካል የሆነ የማይሟሟ ነጭ የቅባት አይነት ሲሆን በበርካታ የሰውነት ተግባራት ውስጥ ቁልፍ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ሆርሞን ዝግጅት ውስጥ
![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2013/04/nega_sebhat.jpg)
የአብርሃ ደስታ የሰሞኑ ምርጥ ዘገባዎች
የህወሓት የኮብልስቶን ፖለቲካ (መቐለ) ======================== የመቐለ ወጣቶች (የዩኒቨርስቲ ምሩቃን) ተደራጅተው በኮብልስቶን ስራ ለመሳተፍ ቢወስኑም የህወሓት መንግስት ሊያስሰራቸው እንዳልቻለ ገለፁ። ወጣቶቹ በኮብልስቶን ስራ ተሰማርተው ስራ
![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2013/09/General-Gezae.jpg)
ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብሰበው ስዊድን ገቡ
(ዘ-ሐበሻ) የጦር ሃይሎች የሎጂስቲክስ ዋና ሐላፊ የነበሩት ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብስበው ስዊድን መግባታቸውን አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ባስተላለፈው መረጃ አመለከተ። አብርሃም ገዛኢ ከሃገር የወጡት
![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2013/08/samuel-eto.jpg)
Sport: ሳሙኤል ኤቶ ቸልሲ ገባ
(ዘ-ሐበሻ) አንዴ ይወጣል አንዴ ይቀጥላል በሚል ሲያወዛግብ የነበረውን የማን.ዩናይትድ አጥቂ ዋይኒ ሩኒን “በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ቸልሲ መግባት አለምግባቱን እንዲያሳውቅ” የቸልሲው አለቃ ሆዜ ሞሪንሆ
Sport: የጎደለው ሊቨርፑል
ብሬንዳን ሮጀርስ በሊቨርፑል ባሳለፉት የመጀመሪያው ዓመታት ደጋግመው የሚሰነዝሩት አስተያየት ነበር፡፡ ‹‹እንደ ቡድን በመከላከል ረገድ መሻሻል ይገባናል›› ይሉ ነበር፡፡ ‹‹እንደ ቡድን›› የሚለው ቃል መላው ቡድኑን