Sport: ሳሙኤል ኤቶ ቸልሲ ገባ

August 29, 2013

(ዘ-ሐበሻ) አንዴ ይወጣል አንዴ ይቀጥላል በሚል ሲያወዛግብ የነበረውን የማን.ዩናይትድ አጥቂ ዋይኒ ሩኒን “በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ቸልሲ መግባት አለምግባቱን እንዲያሳውቅ” የቸልሲው አለቃ ሆዜ ሞሪንሆ የጠየቁ ቢሆንም ለሩኒ ያቀረቡት የ24 ሰዓት ገደብ ሲያልቅ ወዲያውኑ ካሜሩናዊውን አጥቂ ሳሙኤል ኤቶን አስፈርመዋል።
የቀድሞው የባርሴሎና ኮከብ ሳሙኤል ኤቶ በቸልሲ ከረዥም ዓመታት በፊት ጀምሮ ሲፈለግ የነበረ ቢቆይም ዝውውሩ እስካሁን ሳይሳካ ቢቀርም አሁን ግን ተጫዋቹ ወደ እርጅና እየተጠጋ ባለበት ጊዜ ከሩሲያው ክለብ አንዝሂ ማካቻካል አስፈርሞታል።

ከ እንግሊዝ ሚዲያዎች አካባቢ ከቃረምናቸው መረጃዎች እንደተረዳነው ቸልሲ የሳሙኤል ኤቶን ስምምነት በነጻ ዝውውር የፈጸመ ሲሆን ውሉም ለአንድ አመት የሚቆይ ይሆናል። ሳሙኤል ኤቶ ወደ ሩሲያው አንዚ ማካቻካላ የተዛወረው በ€21ሚሊዮን ሲሆን ዓመታዊ ደሞዙ ደግሞ €10ሚሊዮን ነበር። አሁን ከቸልሲ ምን ያህል እንደሚያገኝ የተቃረመ ነገር አላገኘንም።

Previous Story

የኢሕአዴግ ወታደራዊ ትጥቅ ማምረቻ ፋብሪካ ተቃጠለ

Next Story

በፍቼ በአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የደረሰ ድብደባ

Latest from Same Tags

የአብርሃ ደስታ የሰሞኑ ምርጥ ዘገባዎች

የህወሓት የኮብልስቶን ፖለቲካ (መቐለ) ======================== የመቐለ ወጣቶች (የዩኒቨርስቲ ምሩቃን) ተደራጅተው በኮብልስቶን ስራ ለመሳተፍ ቢወስኑም የህወሓት መንግስት ሊያስሰራቸው እንዳልቻለ ገለፁ። ወጣቶቹ በኮብልስቶን ስራ ተሰማርተው ስራ
Go toTop

Don't Miss