በአዲስ አበባ ሕዝብን ሲቀሰቅሱ የነበሩ 5 ሰዎች ታሰሩ

August 23, 2013

“እኔ በአዋጅ ሳይሆን በትዕዛዝ ነው የምመራው፤ እሰር የሚል ትዕዛ ደርሶኝ አስሬያቸዋለሁ”

– የፖሊስ አዛዥ

የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)

(ዘ-ሐበሻ) የፊታችን እሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም (ኦገስት 25 ቀን 2013) በአዲስ አበባ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መ.ኢ.አ.ድ/ ዋና ጽ/ቤት 33ቱ ፓርቲዎች ለጠሩት ህዝባዊ ውይይት የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የፓርቲዎቹ አባላት በህገወጥ መንገድ መታሰራቸውን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት አስታወቀ።

እንደ ዘገባው ከሆነ በቅስቀሳው ላይ ከነበሩት ወገኖች መካከል
1ኛ አቶ ደመላሽ፣
2ኛ. አቶ አብርሃም ፣
3ኛ. አቶ አታላይ በለው፣
4ኛ. አቶ እዮብዘር
5ኛ. አቶ መላኩ መሰለ
የተባሉት አባላት የቅስቀሳ መከናውን ከያዘው ሹፌርና ረዳት ጋር ታስረዋል፡፡
የፓርቲዎቹ አመራሮች አባሎቻቸው ወደታሰሩበት 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ አቅንተው እስሩ ህጋዊ አለመሆኑን አዋጅ በመጥቀስ ቢያስረዱም በስፍራው የነበሩት የፖሊስ አዘዥም “እኔ በአዋጅ ሳይሆን በትዕዛዝ ነው የምመራው፤ እሰር የሚል ትዕዛ ደርሶኝ አስሬያቸዋለሁ” የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘገቧልል።

Previous Story

ሕዝባዊ ስብሰባ በሲያትል በአካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

Next Story

Sport: ሙስሊም ተጨዋችና እግርኳስ

Latest from Same Tags

‹‹በትግራይ ግጭት የተካሄደው የምርመራ ሪፖርት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት አግኝቷል›› – ዶክተር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ጋር በጣምራ በትግራይ ግጭት ላይ ያካሄዱት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ሪፖርት ዓለም

Sport: ሳሙኤል ኤቶ ቸልሲ ገባ

(ዘ-ሐበሻ) አንዴ ይወጣል አንዴ ይቀጥላል በሚል ሲያወዛግብ የነበረውን የማን.ዩናይትድ አጥቂ ዋይኒ ሩኒን “በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ቸልሲ መግባት አለምግባቱን እንዲያሳውቅ” የቸልሲው አለቃ ሆዜ ሞሪንሆ
Go toTop

Don't Miss