ኢትዮጵያ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከናጄሪያ ጋር ትፋለማለች

September 16, 2013

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሚያደርገውን የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከናይጄሪያ ጋር እንደሚያደርግ ዛሬ በወጣው ድልድል መሠረት ታወቀ። ቀድሞም በርከት ያሉ የስፖርት ተንታኞች ኢትዮጵያ ከናይጄራ ጋር እንደሚደርሳት ሲገምቱ ነበር።

ኢትዮጵያ ወደ ዓለም ዋንጫ ለማለፍ 180 ደቂቃዎች ብቻ የቀሯት ሲሆን በነዚህ 180 ደቂቃዎች ናይጄሪያን ካሸነፈች የብራዚል መሄጃዋን ትኬት ትቆርጣለች።
በብራዚል በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ አፍሪካን ወክለው 5 ቡድኖች የሚሄዱ ሲሆን ኢትዮጵያ አንዷ ለመሆን የመጀሪያውን ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ከኦክቶበር 11 እስከ 15 ባለው ጊዜ እንደምታደርግ ይጠበቃል። የመጀሪያውን ጨዋታ በአዲስ አበባ ላይ በደጋፊያችን ፊት እንደማድረጋችን ናይጄሪያን በሰፊ የጎል ልዩነት ካሸነፍን ጨዋታውን አዲስ አበባ ላይ ጨርሶ ወደ ናይጄሪያ መሄድ ይቻላል።

ብሄራዊ ቡድናችን የመልሱን ጨዋታ ከኖቬምበር 15 እስከ 19 በናይጄሪያ የሚያደርግ ሲሆን በሁለቱ ጨዋታዎች ድል ከቀናው ወደ ብራዚል አፍሪካን ከሚወክሉት 5 ቡድኖች ጋር ያቀናል።

በሌላ በኩል ለዓለም ዋንጫው ጥሎ ማለፍ ጋና ከግብጽ፣ ቱኒዝያ ከካሜሮን፣ ኮትዲቭዋር ከሴኒጋል፣ ቡርኪናፋሶ ከአልጄሪያ መደልደላቸውን የዘ-ሐበሻ የስፖርት ዘጋቢዎች ያገኙትን መረጃ ጠቅሰው ዘግበዋል።

Previous Story

Hiber Radio: ኢትዮጵያና ኤርትራ አንዱ የአንዱን መንግስት ለመጣል ተቃዋሚዎችን እየረዱ መሆኑ ተገለጸ

Next Story

በ6 ኪሎ አንበሳ ግቢ አንበሳ ሰው ገደለ

Go toTop