በ6 ኪሎ አንበሳ ግቢ አንበሳ ሰው ገደለ

September 16, 2013

መንግስታዊው ራድዮ ፋና እንደዘገበው በአዲስ አበባ በአንበሳ ግቢ የአንበሶች ማቆያ ማዕከል ውስጥ ዛሬ ከጠዋቱ 1:30 ላይ የሞት አደጋ ተከሰተ።

አደጋው የተከሰተው አቶ አበራ ሲሳይ የተባሉት የአንበሶቹ መጋቢ የአንበሶቹን ማደሪያ እያጸዱ ባሉበት ወቅት ከጥንቃቄ ጉድለት ባልተዘጋው በር የገባው ቀነኒሳ የተባለው አንበሳ ለህልፈተ ህይወት ዳርጓቸዋል።

የግለሰቡን ህይወት ለማትረፍ በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ የግቢው ሰራተኞች ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካ መቅረቱ ለማወቅ ተችሏል።

የሟች አስከሬን ከአንበሶቹ ማደሪያ ወጥቶ ለምርመራ ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወስዷል።

ተመሳሳይ አደጋ ከዚህ በፊት በ19 89 ዓ.ም መከሰቱ የሚታወስ ነው።

ምንጭ ራዮ ፋና

Previous Story

ኢትዮጵያ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከናጄሪያ ጋር ትፋለማለች

Next Story

የኛ ነገር፤ ከኔ ማእዘን፤ ክፍል 14 (ከተክለሚካኤል አበበ)

Go toTop