በቤንች ማጂ በተነሳ ግጭት ሶስት ተማሪዎች ቆሰሉ

April 22, 2013

በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሚዛን 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት በተነሳው ግጭት ሶስት ተማሪዎች መቁሰላቸውና ከሚያዚያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ ፡፡ እንደ ፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፃ ከሆነ ከሚያዚያ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ጀምሮ
በትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና አስተዳደር አካላት በተነሳ አለመግባባት ከፍተኛ እረብሻ በመፈጠሩ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ለረብሻው መንስኤው ለትምህርት ቤቱ ከአሜሪካ በተሰጠው የትምህርት ዕድል የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ተማሪዎች መካከል በተደረገው ውድድር ከሴቶች ተማሪ መድኃኒት ስታሸንፍ ከወንዶች ደግሞ በጀመሪያ
ተማሪ ጌታመሳይ ማሸነፉ ከተጠቆመ በኋዋላ በተደረገ የውጤት ማጣራት ሂደት ተማሪ ዮሐንስ ማለፉ መለጠፉ ነው፡፡
ይህንንም ተከትሎ በተለይ የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ በወንዶች ተማሪ ዮሐንስና ተማሪ ጌታመሳይ ውድድር ላይ የውጤት አሰራር ስህተት በመኖሩን በተማሪዎችና በትምህርት ቤቱ መምህራንና አስተዳደር አካላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መማር ማስተማሩ ሂደት መቋረጡ ተጠቁሟል፡፡
በመጨረሻም በተደረገው የውጤት ማጣራት መሰረት በውድድሩ ያለፈው ተማሪ ዮሐንስ መሆኑንም ምንጮቻችን አስታውሰዋል፡፡

Previous Story

ዶ/ር ነጋሶ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲን ከአንድነት ያባረርነው በብቃት ማነስ ነው አሉ

Next Story

ኢሕአዴግ በምርጫው በደረሰበት መደናገጥ የ5 ለ1 ጠርናፊዎቹን መገምገም ጀመረ

Go toTop