ሰልፉ የአብይ አህመድን መንግስት ከመደገፍ ይልቅ ወደ ተቃዋሚነት ተለወጠ

December 18, 2024

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች አገዛዙን የሚቃወሙ ሰልፎችን አካሄደ።
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
ታሕዛስ 9/2017 ዓ.ም

የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተቆጣጥሮ በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች መካከል በተወሰኑት ላይ አገዛዙን ስርዓት የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ እያካሄደ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓትም የአረመኔው አብይ አረመኔያዊ ተግባር የሚቃወም ሰልፍ በቀወት ወረዳ ራሳ ተሬ ፣ በጣርማበር መዘዞ፣ በኤፋራታና ግድም/ኤፌሶን አላላ ፣ መንዝ ወገሬ ፣ አንኮበር አልዩአምባ ፣ ተጉለት ሳሲት እንዲሁም መራቤቴ አውራጃ ሚዳ መራኛ ሬማ ላይ ጨካኙና ጨፍጫፊውን የአብይ አህመድ ስርዓት እየተወገዘ ይገኛል።

አገዛዙ በተለያዩ የአማራ ከተሞች የጠራው ሰልፍ እየከሸፈ የተመለከትን ሲሆን ሕዝብን በማስገደድ ድጋፍ ማግኘት እንደማይቻል በተጨባጭ የታየበት ሆኗል። በተለይ በሸዋ ቀጠና የተጠራው የአገዛዙ ሰልፍ የህልም ምኞት ሆኖበት የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ኦፕሬሽናል ቡድን በሰጠው ማስጠንቀቂያና በወሰደው የጥቃት እርምጃዎች ደብረብርሃን ሸዋሮቢት፣ መንዝ ሞላሌና ፣መሀልሜዳ በአገዛዙ ሊደረግ የታሰበው ሰልፍ ተበታትኖበታል ።
ከአማራ ሕዝብ ልብ ውስጥ የወጣው የአብይ አህመድ አገዛዝ የሕዝብ ድጋፍ አለኝ ለማለት በተለያዩ የአማራ ከተሞች ንፁሃንን በማስገደድ ሊያስወጣው ያሰበው ሰልፍ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በተቆጣጠራቸው ቦታዎች በተቃውሞ ሲቀየር በተቀሩት ቦታዎች በሰርጅካል ኦፕሬሽን አገዛዙ ዕቅድ እያከሸፍንበት እንገኛለን።
ተስፋ የማይቆርጠው አገዛዝ የተበተነበትን ሠልፈኛ ለመሰብሰብ ስምሪት ወስደው ቤት ለቤት አሰሳ በሚያደርጉ 3 የሚሊሻ አባላት ላይ እስካሁን እርምጃ ተወስዷል። በተጨማሪም ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡት ላይ ለከተማ ኦፕሬሽን በተዘጋጀው ስውር ቡድን የማያዳግም እርምጃ መውሰዳችንን እንደምንቀጥል እየገለፅን ሕዝባችን ከቤቱ ባለመውጣት ራሱን እንዲከላከል ስንል መልዕክታችን እናስተላልፋለን።
የሕዝብ ድጋፍ በፖለቲካ ድለላ አይመጣም!
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት?

2 Comments

  1. እናንተዉ እያስፈራራቹ እና እየገደላቹ ጨፍጫፊዉ እና ገዳዩ አብይ ነዉ ስትሉ አይነፋም።ይህን ያልኩት ከፃፋቹት ማስጠንቀቂያ ተነስቼ እንጂ የትኛዉም ወገን የለዉበትም።ለህዝቡ ግን ነፃነቱን ስጡት።

  2. John አብይ አልገደልኩም አላለም ምነው ደነጋገጥክ እነሱም ለህዝቡ ብለው እንዳንተ አገልግለው መኖር ሲችሉ በጫካ በበረሃ ያለ እንቅልፍ እየታገሉ ነው በተለያየ ምክንያት ድጋፍ ባትሰጣቸውም ለህሊናህ ስትል ዝም በል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በግርግር 5 ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ ቅርጥፍ አድርጎ የበላው የትናትናው የቲቪ ሪፖርተር ያዛሬው ሚሊኒየር የግሩም ጫላ አስቂኝ ቃለ ምልልስ

Next Story

ዘመነ ካሴ “አሸንፈናል” እና ሰልፉ | ደብረፅዮን “ለአዲስ ትግል ተዘጋጁ ” |”ፋኖ ወደ መንግስትነት….ብልጽግና ወደ ሽፍታነት” አርበኛ አስረስ

Go toTop