አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ቀዶ ሕክምና ተደረገላቸው

December 13, 2024
የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ
የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ

የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ በአንጀት ሕመም ትላንት የቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ በዚያው ዕለት ከሆስፒታል ወደ ማረሚያ ቤት መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገልጸዋል፡፡

ታካሚዎቹ በሆስፒታሉ ቆይተው ክትትል እንዲደረግላቸው እንዳልተፈቀደላቸው የገለጹት ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ፣ በመሆኑም ደም ከፈሰሳቸው በአስቸኳይ እንዲያመጧቸው ለማረሚያ ቤት ደብዳቤ ተጽፎ መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው መኮንን በበኩላቸው፣ በቀጠሮ እንዲመጡ እንጂ እዚያው ሆነው እንዲታከሙ ከሆስፒታል የደረሰን ጥያቄ የለም ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአዲስ አበባ አሜኬላዎች – Anchor Media ከገለታው ዘለቀ ጋር ህየተደረገ ውውይይት

Next Story

የፋኖና የአገዛዙ ጦር ከባድ ውጊያ / በላስታ የተፈጠረው አሳዛኝ ጉዳይ / “ከሃዲዎች ” ሌ/ጄኔራል ፃድቃን

Go toTop