‹‹ህወሃት የራሱን ሰዎች በጊዚያዊ አስተዳደር ውስጥ ለመመደብ የማንንም ይሁንታ አይጠይቅም›› ዶ/ር ደብረጺዮን

August 22, 2024
ሐሙስ ነሐሴ 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ህወሃት የራሱን ሰዎች በጊዚያዊ አስተዳደር ውስጥ ለመመደብ የማንንም ይሁንታ አይጠይቅም ሲሉ የህወሃት ሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል አስታውቀዋል፡፡
በመቀለ ሳምንታትን ያስቆጠረው ፖለቲካዊ ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
ለሁለት ተከፍሎ ውዝግብ ውስጥ የገባው ህወሃት አባላቱ ጉባኤ ማካሄድ አለብን ወይስ የለብንም የሚለው ፖለቲካዊ ክርክራቸው ከፍ ብሎ ቀጥተኛ ወደሆነ የስልጣን ሽሚያ ውስጥ እንደገቡ ብዙዎች እየገለጹ ነው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በጊዚያዊ አስተዳደር ውስጥ የሚኖራችሁ ሚና በቀጣይ ምን አይነት ነው የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው የህወሃት ሊቀመንበር ደ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ህወሃት በጊዚያዊ አስተዳደር ውስጥ አባላቱን ለመመደብ ከማንም ፍቃድ አይጠይቅም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ይሁን እንጂ በጉዳዩ ላይ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር መወያየት ያስፈልጋል ያሉት ሊቀመንበሩ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር አሁን ላይ በህወሃት ውስጥ ውክልና ስለሌለው ጊዚያዊ አስተዳደሩን የመምራት አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡
ቀስ በቀስ ልዩነታቸው እየሰፋና ፖለቲካዊ መካረራቸው እየበረታ የመጣው ሁለቱ ቡድኖች እርስ በእርሳቸው እየተወቃቀሱና ሹም ሽር እያከናወኑ ቀጥለዋል፡፡

አዲስ ማለዳ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“ዘርይሁን – 13″ የሚል ስያሜ የተሰጠው የጦር መሳሪያ ማምረቻ የምርምር ማዕከል አቋቁመናል!” -ፋኖ አስረስ ማረ

Next Story

የአማራ ፋኖ ተጋድሎዎች ከሰሞኑ | የአማራ ፋኖ ተጋድሎዎች ከሰሞኑባህርዳር ከባድ ፍንዳታ ስብሰባው በድንገት ተበተነ |, ፋኖ ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት እየገሰገሰ ነው‼️

Go toTop