ከፋፋዮች አማራን የማዳን ኢትዮጵያን የመታደግ ትግል አታደናቅፉ

September 24, 2023
የሃገራችን ውስብስብ ፖለቲካ ቀዳሚውን ከተከታዩ መሰረታዊን ከመለስተኛው ማገናዘብ እያቃተው ዘመናትን ቢያስቆጥርም በጌታ ትልቅ ድጋፍ ህዝባችን ክፉዎችን እያዋረደ ነው::
 እሸቱ ጮሌ ሃይሌ ፊዳ ሰናይ ልኬ ንግስት እዳነ አክሎግ ቢራራ ይሰቀሉ  ብለን በተሳተፍንበት ያልበሰለ የጀብድኝነት የተማሪው ትግል የነበሩ ስህተቶች ዛሬ አይደገሙ ማስተዋል ጥበብ ይሙላብን:
ዶክተር እክሎግ ቢራራ የሚያደርጉት ትግል በተለይ አማራን መታደግየሚደነቅ ነው:: ሆኖም ግን በእባይ ጉዳይ ሁላችንም ግድ እንደሚለን እየታውፕቀ በዚህ ወቅት ከግድብና ሃገራዊ ልማት በላይ የክቡር የሰው ዘር በተለይ በዘረኞች ኢላማ ተደርጎ ነፍጠኛ ጦረኛ በሚል ሃሰተኛ ትርክት በእትዮጲያ አፍራሽ ሃይሎች ሻቢያ ወያኔ ኦነግ ብልጽግና የተባባሰውን ተከትሎ የሚጨፈጨውን አማራን ልመታደግ ትግሉ በተባበሩት መንግስታት የሰው መብት ኮሚሽን በተቀባይነት የብልጽግና ግፈኛ መንግስት በሚሞግትበት ለህዝብ ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂነት እየተመከረ ባለበት ሁኔታ ይህን ነቀፋና መካሰስ በአፋጣኝ ማስቆም ይኖርብናል::
aklog birara 1
aklog birara 1

ዶክተር እክሎግም እንደለየለት ቀውስ ምንደኛ ፕሮፌሰር አለማየሁ ሳይሆን እንደመልካም ሃገር ወዳድ ምሁር ለተፍጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቀው የቀጠሉትን ህዝባዊትግል ይግፉበት ጭፍን ነቃፊዎችና ከፋፋዮች ታቀቡ ዋናውን የሚታረደውን አማራ መታደግና ኢትዮጵያን የማስቀጠል ትግል አታደናቅፋ::

ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው
(ትንቢተ ሆሴዕ 4:6) ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።
ሞረቴው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአቢይና ጓደኞቹ በሽታ ከሌሎች ይለያል! – ይነጋል በላቸው

Next Story

የፋኖዎች ጎንደር መግባት እድምታዎች

Go toTop