የሮብአም ጥፋት በአብይ አህመድ አይደገም ታላቆች ገስጹ

September 18, 2023
በአለም ታሪክ ቀደምት ከሆኑትና የሰው ዘር መነሻዋ የቀድሞው አለምአቀፍ ማህበር ሊግኦፍ ኔሽን የቀጣዩ የተባበሩት መንግስታት መስራቾች በመህን በሰላም ማስከበር ዘመቻ በኮንጎ በኮርያ በሶማሌና በሩዋንዳ ንቁ ተሳታፊ ቅኝ ተገዥነትን በጥበበኛው እጼ ምኒልክ አመራር ያላስተናገደች ሃገሬ ኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳስበኛል::
ባለፉ ጊዜያት በምክክር ሊፈቱ የሚገባቸው የባድመ በቅርቡም የትግራይ  ጦርነቶች ጠባሳ ሳይሽር በዚህ ወቅት የአማራ ክልል ተብሎ በሚጠራው ኢመደበኛ ያልሆነ ታጣቂን ትጥቅ ለማስፈታት በሚል የሚካሄደው ወረራ አመራር ሰጭ ዶክተር አብይ አህመድ አካሄድ የመጽሃፍ ቅዱሱ ሮብአም ቀጥታ ግልባጭ መሆኑን በጎ ህሊና ያለው የቅዱሳን መጽሃፍት/ኪታብ ተንታኝ ሁሉ ይረዳዋል::
ይህን በግልጽ የሚታይ ግድፈት እንደቀደሙት የኢትዮጵያ የእምነት ቆራጥ አባቶች የገሰጹትን አቡነ አብርሃምና ባልደረቦቻቸውን እያመሰገንኩ ሌሎቹም የእምነትና የማህበረሰብ መሪዎችና ታላቆች ድምጻቸውን ያሰሙ ዘንድ በትህትና ጥሪዬን አቀርባለሁ::
በሃገራዊ እርቅና ሰላም ጉባኤ በሽግግሩ  ወቅት ንቁ ተሳታፊ ለነበረችው የራሴው ወንጌላዊት የቀድሞ መሪና የወቅቱ በውጭ እማካሪ ለሆኑት ይህን ጥሪ ሳቀርብ በግዮኑ ሃገራዊ እርቅ ወንጌላዊት ትሳተፍ ዘንድ ሃሳቡን ያቀረቡ ዛሬ በህይወት የሌሉት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት እቶ መስፍን ልሳኑ እንደነበሩ የነገሩኝን ለወቅቱ መሪዎችና ለህዝባችን መልካም ምሳሌነታቸውን ማሳወቅ እፈልጋለሁ::
በኦነግ ትግል የቆዩትና በዚህ መሰል ሃገራዊ እርቅ የሚተጉት የአባጅፋር ልጅና ባልደረቦቻቸው ይህን በጎ ስራ ይቀጥሉ ዘንድ ማሳሰቢያዬ ይድረስልኝ ሁላችንም ፈጣሪን በመማጸን

ኢትዮጵያን እናድን::

ቻፕሊያን ኤዲ/አደፍርስ ሃብቴ መካሻ
የማህበረሰብ ክሚኒቲ መሪና የግጭት እፈታት አማካሪ
(2ኛ ዜና መዋዕል 10 8) እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ነገር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ባለፉት ሁለት ቀናት ከ20 በላይ አከባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ሆኑ፥ በድሮን ጥቃት ሰላማዊ ዜጎች ተገደሉ

Next Story

አማራ ቃል ግባ! – በላይነህ አባተ

Go toTop