ቃርያን የመመገብ የጤና ጥቅሞች በጥቂቱ (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

February 8, 2023
ቃርያ አብዛኛውን ጊዜ ምግብን ለማጣፈጥ የምንጠቀምበት ሲሆን እንደሃገራችን ባሉ ቅመማ ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን በሚመገቡ ሀገራትም ይዘወተራል።
ቃርያ በቫይታሚን ሲ፣ቢ6፣ኤ፣አይረን፣ኮፐር እና ፖታሲየም የበለጸግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፋይቶኑትሪየንት ማለትም ካሮቲን፣ ሉቲየን ዚያዛንቲን በውስጡ ይዟል።
✓ ቃርያን የመመገብ ጠቀሜታዎች
1. ቫይታሚን ኤ ዋነኛ ከሚባሉ ቃርያ ውስጥ ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች ስለሆነ እና ለአይን ጥራት እና ጤናማነት ከፍተኛ ሚናን ስለሚጫወት ቃርያን መመገብ ጠቀሜታን ይሰጣል።
2. ቃርያ በቫይታሚን ሲ እጅግ የበለጸገ በመሆኑ ቆዳችንን ጤናማና የሚያበራ እንዲሆን ያደርጋል።
3. በሽታን የመከላከል አቅምን ማዳበር።
4. የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል።
5. ጉንፋን፣ሳል፣እንዲሁም የሳንባ ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው።
6. ለአጥንት ጤናማነት እና ጥንካሬ እጅግ ጠቃሚም ነው።
7. ለሰውነታችን ጠቃሚ ያልሆኑ ንጥረነገሮችን በማስወገድ እና የፋይበር ምንጭ በመሆን የሆድ ድርቀትን ይከላከላል።
8. ቃርያን የሚመገቡ ሰዎች የቆዳ መሸብሸብ እንዳይኖራቸው እንዲሁም ቶሎ እንዳያረጁ ያደርጋል።
እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!
ጤና ይስጥልኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የነነዌ 3ኛ ቀን ጸሎተ ምሕላ በተለያዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት

Next Story

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፍጹም ኃይማኖታዊና መንፈሳዊ የሆነ ሱባኤያቸውን በሰላም አጠናቅቀዋል።

Go toTop