ይድረስ ለሚመለከተው

January 18, 2023


የሚጫወት የፖለቲካ ገበጣ
ገጣባ፣ አንኮላ፣ ባዶ ሌጣ
እንደ እስስት ተለዋዋጭ
ለምዕራብ-ምሥራቅ አሽቃባጭ፣
ትናንት ግፋ በለው ጦረኛ
ዛሬ የሰላም ዘብ ሃገርተኛ
ሃኬተኛ፣ አገዳዳይ ዓይን አውጣ
ተገለባባጭ የወሬ ሞጥሟጣ
ዘር-ጎሳ-ብሄረሰብ መዝግቦ
በህገ-መንግስት ደንግጎ ገድቦ
ሃገር በክልል ሰነጣጥቆ ከፋፍሎ
ግላዊ ዜግነትን መንጥሮ ጥሎ
ሰው በሃገሩ መጤና ባዕድ በሆነበት
ተፈናቅሎ በየቦታው ሲንከራተት
በዚህ ዓይነት ሃገር እንዴት ይገነባል?
ከቶስ ይህ “ልማት“ ምን ይባላል?
የጎሳ እልቂት መች ቆመና
አባራ እንጂ መች ከሰመና?
ያ ነው ማጠየቂያው፣  መጠይቁ
የዕንቆቅልሹ ዕንብርት ወርቁ::
***************************
ፈ.ፉ. (16 Jan 2023)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ሕገ-መንግስቱን ለማሻሻል ለሚደረገው ሕዝባዊ ውይይት ይጠቅማሉ የምንላቸው ሐሳቦች (ከተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን)

Next Story

ፍትህ ለክቡር ታዲዮስ ታንቱ፡፡ እውቀት ይስፋ ድንቁርና ይጥፋ ይህን ይላል የኢትዮጵያ ተስፋ (ቀ ሃ ስ)

Go toTop