የፋኖና የኦሮሙማ ነፍጠኞች ሚዛን ያጣ ንጽጽር ሲገመገም – በፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው

December 11, 2022

 ከሚድ ዌስት አሜሪካ  ዲሰምበር
11/2022

በትውልድ ሃገራችን ኢትዮጲያ  በነአብይ ለማና ገዱ የተጀመረውን  የኢትዮጲያ  ተሃድሶ በማማን  የሚታመንባቸውን ታላቆች ከቪዥን ኢትዮጲያ እስከ  ስመጥሩ መንፈሳዊ መሪዎች ድረስ ሰምተን ሚኖሶታ ድረስ አብይን ለመቀበል  የሄድንባቸው ቀናቶች ከቶ አይረሱም::

ሚኒሶታን  የደራሲያን ማህበር መስራች  አማረ ማሞ በላንጣቸው ከስራ ያሰወገዷቸው ቄስ ጉዲና የጀመሩት የኦሮሙማ ማህበር አድጎ ጎልምሶ በነአብይ አቀባበል ላይ የኦሮሞ ባንዲራ ብቻ መድረኩን ይቆጣጠር ዘንድ ዘፈኑም ኦሮምኛ ብቻ ይሆን ዘንድ የነበረው ትእይንት ለዛሬው ምስቅልቅል አሰቃቂ የወገኖቻችን መታረድ መፈናቀል ሂደት መንገድ ጠራጊ መሆኑን በሂደት ተረዳን:: ከዚያ ስንሰባ መልስ” ኢትዮጲያ ሱሴ” ተቀይሮ” ኦሮሞ ሱሴ” መሆኑን ያረጋገጥን ሲሆን ከአጣዬ ጀምሮ በነለማ ቅንብር ሿሿ ተደርጎ ከኤርትራ በረሃ የገባው ኦነግ በዳቦ ስሙ ሸኔ በአማሮች በጉራጌዎችና በገሙዎች ላይ ይፋ ጭፍጨፋውን ቀጥሎ ለዛሬዋ ሰቆቃዊት ኢትዮጲያ ደርሰናል::

ከሰሞኑ በሚኒሶታ በዲሲ የሚገኙ ከወንጌላዊት ተገንጥለው ወጥተው የኦሮሞ ወንጌላዊት ሉተራን ወዘተ ያሉትን የተለያዩ ዩቱቦች በመቀባበል በቀለ ገርባና ጃዋር መሃመድን በዋቢነት በመጥቀስ “

ፋኖ በወለጋ ህዝባችንን ጨረሰ” የሚል የአዞ እንባ ያቀርባሉ::

ለመሆኑ ሽመልስ አብዲሳ በመቶሺዎች በልዩ ስልጠናና ትጥቅ ያሰለጠናቸውን ብዙሃኑ በትክክል ወደ OLA  የገቡትን በቁጥር ፋኖዎቹ በልጠው ነው ወይንስ ልክ እንደ እስራኤሎቹና  አረቦቹ በቁጥር አነስተኛው ብዙሃኑን  አቸንፎ ነው?  ይህን የምጠይቀው መልሱ ጠፍቶኝ ሳይሆን ሰሞኑን የሚነዛውን “ፋኖ ወለጋ ህዝባችንን ጨፈጨፈ” የሚለውን ሃሰተኛ ትርክት ለመመከት ነው::  በትክክል ጄነራል አሳምነው በብቃት ለማሰልጠን ሲጀምር “ብሩን በወታደራዊ ወጭ ፈጃችሁት”  ብሎ አብይ አህመድ ሲያግድ ከዚያም የእርስበርስ መቃቃራቸውን ተጠቅሞ ያመነመነው የአማራው ልዩ ሃይል ወያኔን መመከት ያቃተው በወኔ ተንቀስቅቅሶ ከአፋር ነብሮች ጋር አብይን የደገፈው ፋኖ ዛሬ ውለታው “ኢመደበኛ ያልሆነ” በሚል ጅማሮ መሪዎቹንማሰር ማሳደድ ለመሆኑ በይፋ የሚያትን ነውና ለኦነግ የገበራችሁት የኦሮሞ ልዩ ሃይል ሰላማዊ ህዝባችንን ኦሮሞውን ጭምር የሚፈጄውን በፋኖ ማሳበብ ማላከክ ቀሽም ፕሮፓጋንዳ መሆኑን በመግለጽ ከቤንሻንጉል ነጻ አውጭ ጋር በተደረገው አይነት ከሁሉም ታጣቂ ጋር ስምምነት ተፈጥሮ ሃገሪቱን ሁሉም ብሄረሰቦች ያካተተ ብሄራዊ መከላከያ ይመሰረት ዘንድ ምክሬን እሰጣለሁ::

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በአዲስ አበባ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ

Next Story

ጭራቆች የሚፈጥሙትን የዘር ፍጅት የማይቃወምና የማይታገል በዝምታ ፍጅቱን እንደ ደገፈ ታሪክና ትውልድ ሲዘግበውና ሲረግመው የሚኖር ነው! –

Go toTop