የቀብር ሥነ ስርአቱ ነገ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀምም ነው ኮሚቴው የገለጸው፡፡
የቀብር ሥነ ስርዓቱን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ በአርቲስቱ መኖሪያ ቤት በሰጠው መግለጫ÷ ነገ በአርቲስቱ መኖሪያ ቤት እንዲሁም በወዳጅነት ፓርክ ከ6 ሰዓት ጀምሮ በመንግሥት ኃላፊዎች፣ በሙያ አጋሮቹ፣ በአድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ የአስክሬን ስንብት እንደሚካሄድ ገልጿል።
ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸምም ተናግሯል።
አርቲስት ማዲንጎ በትላንትናው ዕለት በድንገተኛ ህመም በህክምና ላይ እያለ ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
ከአርቲስቱ ህልፈት ጋር ተያይዞ እየወጡ የሚገኙ ሀሰተኛ መረጃዎችን ወደጎን በመተው ለአርቲስቱ ያለንን ክብር እናሳይ ሲልም የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ መልዕክት አስተላልፏል።
ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግስቴ / አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን