በሱዳን አሸባሪው ህወሓት ያሰማራቸው ታጣቂዎች እየከዱ ነው

August 2, 2022
የአሸባሪው ህዋሓት ወቅታዊ አቋምና አካሄድ ግራ ያጋባቸዉና ቡድኑ በሱዳን ያሰማራቸው ታጣቂዎቹ በሚስጥር ያደርጉት የነበረዉን ክህደት በአደባባይ አድርገዉ መክዳታቸውን ቀጥለዋል።
በሱዳን በተለያዩ አካባቢዎች ከሚንቀሳቀሱ የህወሓት ታጣቂዎች የሚከዱ አባላት ቁጥራቸው መጨመሩን የገለጹት የኢፕድ ምንጮች፤ በአንድ ቀን በአማካኝ እስከ 200 ታጣቂዎች እየከዱ መሆኑን ለመረጃዉ ቅርበት ያላቸዉ እነዚሁ ታማኝ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት በአንድ ጊዜ ብቻ 180 የሚሆኑ የቡድኑ ታጣቂዎች ከተባሰቡበት አከባቢ በመጥፋት በሱዳን ሀምዳይት ወደሚገኝ የቀይ መሰቀል ካምፕ መግባታቸውን ምንጮች ገልፀዎል።
ከነዚህም መካከል አንዳንዶቹ ከዚህ በኋላ መጨረሻ የሌለውን የህወሃት የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ በመተው ባገኙት አጋጣሚ የእርሻ ስራ፣ የጉልት ስራ፣ ትናንሽ ንግዶች እና ሌሎች ራሳቸውን ለመለወጥ የሚያስችል ስራ ላይ ተሰማርተው ኑሯቸውን ለመምራት እንቅስቃሴ ጀምረዋል ነው ያሉት የኢፕድ ምንጮች።
(ኢ.ፕ.ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“ ሞት አይቀርም ፤ ሥም አይቀበርም ። “ እና  ለሥማችሁ ሥትሉ ፤ ተመሥገን ደሣልኝን እና ታዲዎስ ታንቱን ፍቷቸው

Next Story

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

Go toTop