ጠሚሩ አሁንም እንደዞረባቸው ሁሉ ላዙርባችሁ አመስጋኝ እንሁን በሚል “ስብከት” ከጠፉበት ተከስተዋል። ፓስተርነታቸው አገርሽቶባቸው ነው የተመለሱት።
ነቢዩ ያለውን ላስታውስ፦
“እጃችሁንም ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፥ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል። ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግን ተዉ፥ መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተሟገቱ።” ኢሳ ፩: ፲፭ – ፲፯።
ሌላም ልጨምር
“የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለምስጋና መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም። የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመሰንቆህንም ዜማ አላደምጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።” አሞ ፭: ፳፪-፳፬።
መጽሐፋችን የሚለው እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ – ከሕፃናት እና ከሚጠቡ አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ነው። መዝ ፰፡፪። ወዲህም የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ ልብ መንፈስ ነው፤ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም ይላል። መዝ ፶፡፲፯።
ሲጠቃለል
የኀጥአን መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፤ ይልቁንም በክፉ አሳብ ሲያቀርቡት አስጸያፊ ነው። ምሳ ፳፩፡፳፯።
ስለዚህ ጠሚር በአቋራጭ ለመበልጸግ እንዲሚያስቡት በአቋራጭ በእግዚአብሔር ለመሰማት የሚችሉበት ዕድል የለም። ታጠቡ ተብሏል። ዘልሎ ምስጋና የለም። እንዲያው ዙሪያ ጥምጥም ከሚለፉ ንስሐ ይግቡ ንስሐ እንግባ።
እጅዎ ላይ ብዙ ንጹሕ ደም ይጮኻል!!!
————————————————————————–
የአማራ ብልፅግና አመራሮች 6ተኛው የአማራ ክልል ኘሬዝዳንት በመሆን፣ ከኦሮሚያ ብልፅግና ሹመት ለመቀበል እሽቅድምድም ገጥመዋል።” – ፓስተር ደረጀ ከበደ
ፋኖ ሆይ በስምህ ብቻ ጀግና አልልህም። አማራ ሲታረድ የት ነህ? ወንድምህ ሲታፈን የት ነህ? የአማራ ብልፅግና ጥቅምህን አሳልፎ ሲሰጥ አንተ የት ነህ? ፋኖነት መንደር ለመንደር መሳሪያ ተሸክሞ መዞር አይደለም። ድረሱልኝ ለሚሉት አማራዎች መከታ ካልሆንክ፣ በግሌ ፋኖ ብዬ አልጠራህም። አማራን ለመታደግ ባለመስራትህ ቤትህ ድረስ መጥተው እየገደሉህና እያሰሩህ ነው። ዝም ካልክ ገና ይጫወቱብሃል።
ለአመፅ ተነሳ። በወሬ፣ በመግለጫ፣ በስብሰባ፣ ቃለ መጠይቅ ላይ በመንደንፋት ጠላት አይጠፋም። ጠላት የሚብረከረከው በጠንካራ ትግል ብቻ ነው። ውጭ ያለነው በፋይናንስ እንደግፋለን። በእየ ኢንባሲው ድምፅ እንሆናለን። መንግስታትን እናሳምናለን። አገር ቤት ያለኸው ፋኖ ቆርጠህ ውጣ፣ ጭቆናን እምቢ በል። ለወገንህ ለመሞት ጭምር በተግባር አስመስክር።
የፓርላማ ተመራጭ ሆነህ፣ በአብይ አህመድ ደሞዝ እየተከፈለህ እጅህን አውጥተህ ጥያቄ ስለጠየቅክ ጀግና አትባልም። አማራ የሚፈልገው ወንበር ላይ ተቀምጦ የሚደሰኩርለት ሳይሆን፣ መሬት ላይ ታግሎ የሚያታግለው ሰው ነው። ለተጨፈጨፉት አማሮች የህሊና ፆለት ይደረግላቸው፣ ባንዲራ ዝቅ ብሎ ይሰቀል ስላልክ አማራ አይድንም። አብኖች ከዚህ ማደንዘዣ ውጡ።
አዲስ አበባ የሚለው ስሟ ራሱ በቃሬዛ ላይ ነው ያለው። ሁሉንም ጠቀላለው ጨርሰውታል። የአማራ ብልፅግና ነው ፈርሞ የሰጣቸው።
የአማራ ብልፅግና አመራሮች 6ተኛው የአማራ ክልል ኘሬዝዳንት በመሆን፣ ከኦሮሚያ ብልፅግና ሹመት ለመቀበል እሽቅድምድም ገጥመዋል። ጉዳዩ ለተላላኪነት እኔ እበልጥ እኔ በልጥ ሆኗል። የአማራ ጀኖሳይድ፣ የወልቃይት፣ የራያ፣ የአዲስ አበባ ጉዳይ ለእነሱ ምናቸውም አይደለም።