![](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/03/Abiy-Ahmed-Liar.jpg)
በስብሰባው ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ አቶ አዲሱ አረጋ፣ የፌደራል ኮሚሽነሩ ደምመላሽ ገ/ሚካኤል እና ሌሎች ተገኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ጉዳይ በ2010 ዓ.ም ለተከሰተው ለውጥ ምክንያት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ፣ ይህም ቢሆን ባለፉት አራት ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ ከከተማዋ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እስካሁን ማግኘት አልቻለም ብለው አማረዋል፡፡
ለዚህም ጥሩ ማሳያ ሰሞኑን የተካሄደው የኮንዶሚኒየም እጣ ነው ብለዋል፡፡ “እጣው ባይሰረዝ ኖሮ በኦሮሚያ ትልቅ ተቃውሞ ይነሳ እንደነበር እናውቃለን” ብለዋል።
እንደሚታወቀው፣ አብዛኛው የእጣው ተጠቃሚ ኦሮሞ መሆን ይገባዋል የሚል ቅስቀሳ ውስጥ ውስጡን እየተደረገ ይገኛል። እጣው የወጣ ዕለትም በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦህዴድ/ኦነግ/ሸኔ ያደራጃቸው ቄሮዎች በመኪና ተጭነው ወደ ከተማዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ጭፈራቸውን የከተማው ህዝብ በትዝብት ተመልክቶታል።
![](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/07/Addis-Aba-condo.jpg)
ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ክልል በከተማዋ ውስጥ ያለውን የአስተዳደር፣ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ቁመና ለማሳደግ እስካሁን የተሰራው በቂ አይደለም ብለው አማረዋል፡፡
በጥቅሉ፣ ተሰብሳቢዎቹ አዲስ አበባን የኦሮሚያ አካል የማድረግ እንቅስቃሴው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠው መለያየታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዘገባው—- ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ
https://twitter.com/ZemenuYA/status/1550607740179038211?s=20&t=wpjfcnFQXOKTsprMyXEIsQ
የመወደድ ርሃብ
የመወደድ ጥማት
ከአፋፉ ላይ ገፍቶ
ያቺን አገር ናጣት
ሁሉ ስለራሱ
ሁሌ እየመሰለው
መስታወት ፊት ቆሞ
ሌላ ‘ማይታየው
ወይ በስደት ቢሆን
ወይም በጦርነት
አልያም በችግር
በአፈና ባርነት
በነዚህ ሁሉ ውስጥ
መልኩ ‘ሚያስጨንቀው
የራስ ምስል ባርያ
ምንገዴው ሰው ማነው?!
Anania Sorri