ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ፣ በበቀል ስሜት ደም እንዳይለገስ የከለከሉ የመንግሥት አካላትን አወገዘ!! July 14, 2022 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን የሚውለውን የልደት በዓሌን በማስመልከት ላለፉት ረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በመገኘት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ ደም በመለገሰ ሰብአዊ ተግባር ለምትፈፅሙ የልብ አድናቂዎቼና ወዳጆቼ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፤ በዘንድሮው ደም የመለገስ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ባልተገባ ሁኔታ ለገጠማችሁ መጉላላት የተሰማኝን ኅዘን ስገልፅ ይህን ፍፁም ሰብአዊ ሕይወት የማዳን መርሐ ግብር በተገቢው ሁኔታ እንዳይከናወን ክልከላ ያደረጉ መንግሥታዊ አካላትን በጥብቅ በማውገዝ ነው። በተጨማሪም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት መልካም ምኞታችሁን በተለያየ መንገድ ለገለፃችሁልኝ ክቡራን ወገኖቼ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። ፍቅር ያሸንፋል ቴዎድሮስ ካሣሁን ( ቴዲ አፍሮ) Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story ዕንቅፋትን አለማንሳት ለሞት መመቻቸት ነዉ፡፡ Next Story የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት እውነታዎች (ከታሪክ፣ ከሕግ እና ከስነ ሕዝብ ምህንድስና አንጻር)