ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በመጠጥ ቤት ታዳሚዎች ላይ በተከፈተ የእሩምታ ተኩስ 19 ሰዎች ተገደሉ

July 10, 2022

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ቀጠና እና በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙ ሁለት መጠጥ ቤቶች ላይ በደረሱ የእሩምታ ተኩስ ጥቃቶች 19 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ ።

በጆሃንስበርግ ሶዌቶ መንደር ፣ በሚኒባስ ተጭነው የመጡ ጥቃት አድራሾች በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ በመዝናናት ላይ በሚገኙ ሰዎች ላይ የእሩምታ ተኩስ መክፈታቸውን ተከትሎ 15 ሰዎች ተገድለዋል ።

በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ላይ በምትገኘው ፣ ፒተርማሪትዝበርግ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሌላ መጠጥ ቤት ውስጥ ደግሞ ሁለት ሰዎች ካለ ልዩነት በዚህ በነበሩ ሰዎች ላይ ተኩስ ከከፈቱ በኃላ በነበረ የተኩስ ልውውጥ 4 ሰዎች ተገድለዋል፣ 8 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ።

ፖሊስ ጥቃቶቹ ተያያዥ ስለመሆናቸው ለመናገር ጊዜው ገና መሆኑን ጠቁሞ፣ ተመሳሳይነታቸውን ግን ማጤኑን አስታውቋል-። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ ተጠርጣሪ እንደሌለ ተገልጿል። ሁለቱ ጥቃቶች የደረሱት ፣ ሀገሪቱ ከአፓርታይድ ዘመን ተላቃ ዴሞክራሲን መከተል ከጀመረችባቸው ሶስት አስርት ዓመታት ወዲህ ፣ በእጅጉ የከፋ ነው በተባለ የኃይል ጥቃቶችን እና አለመረጋጋት ሰደድ መመታት በቀጠለችበት ሰዓት ነው።

ባለፈው ሀምሌ ወር ላይ በእጅጉ የተንሰራፋ አመጽ፣ ዘረፋ ፣ በእሳት ማጋየት እና የመሰረተ-ልማት እና ኢንደስትሪ ተቋማትን ባወደመ ጥቃት ወቅት 350 ሰዎች ሞታዋል።በኮቪድ 19 ዳፋ በተፈተነችው ሀገር በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል ። ዘገባው የኤ ኤፍ ፒ ነው።

VOA

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የመንግስትን ከባድ ሴራ ተጋለጠ | ለአማራው ጥብቅ መልዕክት | ታላቅ ንቅ*ናቄ በመላው ሃገሪቱ | መከላከያ ሰበር | የይልቃል ከፋለ ቅሌት በባህር ዳር

Next Story

የቃብትያ አድህርዲ መንገድ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አብይ ኮሚቴ

Go toTop