ሰኔ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) ከትግራይ የመጡ የሽብር ቡድኑ ታጣቂ አባል እንደሆኑ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ በተለምዶ ቱሉ ዲምቱ ተብሎ የሚታወቀው አካባቢ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉ ተገልጿል።
በቁጥጥር ሥር የዋሉት
1ኛ. ዘመን ገ/እግዚአብሔር (የጥበቃ መምሪያ አባል የነበረ የፈንጂ ባለሞያ)
2 ኛ. ገ/ኪዳን ገ/ጻድቅ የቡድኑ ታጣቂ አባል ናቸው።
በተጠርጣሪዎቹ ላይ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራ መጀመሩን ያመለከተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት በፌስቡክ ገለጹ መረጃ በቀጣይ ውጤቱን እንደሚገልጽ አመላክቷል።