በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አቀረቡ።
አምባሳደሩ በዚህ ወቅት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሀፊ አምባሳደር ሞሊ ፊ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ከዚህ ባለፈም የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ባዘጋጁት መርሐ ግብር ላይ ታድመዋል።
(ኢ.ፕ.ድ)