በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ የነበሩ 4 የሕዝብ ማመላለሻና አንድ የጭነት ተሸከርካሪዎች መታገታቸው ተሰምቷል

June 24, 2022
ተሳፋሪዎቹ ከደራ ወረዳ ጉንዶ መስቀል ከተማ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳሉ መታገታቸው የተገለፀ ሲሆን እገታው የተፈፀመው በሂደቡአቦቴ ወረዳ ወዘሚ በሚባል መንደር ነው።
የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ውብሸት አበራ አራት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችና አንድ የጭነት መኪና መታገታቸውን አረጋግጠዋል።
የመንግስት የጸጥታ ኃይል ወደስፍራው መሄዱን ያነሱት አቶ ውብሸት እስካሁን 230 ሰዎች ከእገታው መለቀቃቸውን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በተሸከርካሪዎቹ ውስጥ ምን ይህል ሰዎች እንደተሳፈሩ ከጉንዶ መስቀል መረጃ እየሰበሰቡ እንደሆነ ያነሱት ገልፀው፤ የተለቀቁ ቢኖሩም አሁንም የታገቱ እንዳሉ ማወቃቸውን ተናግረዋል።
እገታው የተፈጸመው መንግስት ሸኔ እራሱን ደግሞ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን እንደሆነም ነው የገለፁት። ተሸከርካሪቹ የታገቱበት አካባቢ በብዛት ቡድኑ የሚንቀሳቀስበት ነው ብለዋል።
ከደራ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ያሉ የሕዝብና የጭነት ተሸከርካሪዎች ከነ ተሳፋሪዎቻቸው መታገታቸው ተገለጸ
የደራ፣ ፍቼ አዲስ አበባ መንገድ ለስምንት ወራት ተዘግቶ ነበር
እገታው የተፈጸመው ከፍቼ 28 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው ተብሏል
አሁን በእገታ ላይ ያሉ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀዋል።
የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የታገቱት ሰዎች ጨለንቆ እንደተወሰዱ ገልጸው በስፍራው መንግስት “ሸኔ”፤ እራሱን ደግሞ “የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት” ብሎ የሚጠራው ቡድን #ማሰልጠኛ እንዳለው ገልጸዋል።
የኦሮሞ ክልል አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ይህንን ጉዳይ እንዳልሰሙና በአካባቢው ”ሽፍታ ይንቀሳቀስ ይሆናል” እንጅ ሌላ ችግር የለም ሲሉ ተናግረዋል።
የደራ ፍቼ አዲስ አበባ መንገድ ለ8 ወራት ያህል ተዘግቶ የነበረ ሲሆን አገልግሎት መስጠት የጀመረው በቅርቡ ነው ተብሏል።
አል ዓይን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ከአ.ህ.ኢ.ን በአማራ ወገኖቻችን ላይ ተጠናክሮ የቀጠለውን መንግስት መራሹን ሰቅጣጭ የዘር ፍጅት ወንጀል በተመለከተ የተሰጠ የአቁዋም መግለጫ

Next Story

በቃ በተግባር አዲስ የሽግግር መንግሥት ጥያቄና የተማሪዎቹ ጥሪ

Go toTop